Back to Front Page

ኮረና Vs ብልጽግና

ኮረና Vs ብልጽግና

ሁለቱንም  አልወድ ... እኔንም  አይወዱኝ
አልወዳቸውም  እኔ ... በጣም  ነው  የሚያስፈሩኝ
... ስራዬን  ካልሰራሁ ... ካልተጠነቀኩኝ
ድቁስቀስ  አድርገው ... መሬት  ነው  የሚከቱኝ

ግን  ይሄ ...
ብልጽግና  የሚሉት ... አገሬ  ውስጥ  ያለው
ትግራዋይ  በመሆኔ ... ጫና  የሚያሳድረው
ልዑላዊ ሀገርን ... በመሸጥ  ላይ  ያለው
አገር  የገነቡትን ... እስር  ቤት  የሚያጉረው
ያልተደመሩትን ... ከስራ  ያባረረው
እነሱ  የሰሩትን ... ከ  ኢሱ  ጋር  ሚመርቀው
ህዳሴ  ግድቡን ... ቁም  ነገር  የማይሰጠው
ዋና  ኢንጅነሩን ... ሆን  ብሎ  ያጠፋው
ሌላው  የሰራውን ... የሚያንኮታኩተው
ቤተመንግስት  አድሶ... ሰለጠንኩ  የሚለው
ዶክተር  ፕሮፌሰሮችን ... በንቀት  የሚያየው
...ግን  እሱ  ራሱ ... ዶ/ር  ነኝ  የሚለው
ብሄርን  ከብሄር ...ማጋጨት  የሚወደው
የሚጠራጠረው ... ንጉስ  ነኝ  የሚለው
አፍሪካን  አግልሎ ... ወደ  አረብ  የዞረው
ያገራችን  ጀግኖች  ተገድለው ...

ዝም  ጭጭ  ያለው
አገር  እየሸጠ ... በባዶ  የሚያቅራራው
ታዲያ ...
ብልጽግና  ከኮረና ... ምንድነው  የሚለየው ?

ለኔ ...
... ብልጽግና ... ትንሽ  ይለያል  ከኮረና
ኮረና  ሰይጣኑ... ዘርን  የማይለየው
የአለምን  ህዝብ ... ጭንቅ  ውስጥ  ያስገባው
ሁሉንም  የሚጠላ ... ለማንም  የማያዳላው
ድሀ  ሆነ  ሀብታሙን ... ማንንም  የማይወደው
ጥቁርን  ከነጩ ... በቀለም  የማይለየው
ትልቁ  አላማው ... የሰው  ዘርን  ማጥፋት ነው ።

ስለዚህ ...
አጥፊና  ቀባሪውን ... ኮረናን  እፈራለሁ
ዶ/ር …ፕ/ር ... ገበሬን  አይመርጥም
የአገር  መሪ  ብሎም ... ይቅርታ  አያደርግም
የሰው  ዘር  የተባለ ... ህይወት  ያለው  ፍጡር
ወንድና  ሴት  ሳይል ... ትንሽ  ትልቅ  ሳይቀር
ማጥፋትና  መቅበር ነው ...
ዘረ  አልባው ... ቫይረስ ።
ምረጥ  ግን  ብትሉኝ ... ሁለቱም  ኪሳራ  ነው ።

ኢዮብ ከጮማ እምኒ

03-28-20

Videos From Around The World

 

Back to Front Page