Back to Front Page

በእውነት COVID-19 በኢትዮዽያ ምርጫ እንዳይካሄድ አሳማኝ ምክንያት ነውን?

በእውነት COVID-19 በኢትዮዽያ ምርጫ እንዳይካሄድ አሳማኝ ምክንያት ነውን?

 

Tidmek Tignen 05-08-20

 tidmektignen@gmail.com

 

እንደሚታወቀው የኢትዮዽያ ምርጫ ቦርድ ባለፈው ዓመት የምርጫ እንቅስቃሴው ዘገምተኝነት በመጠራጠር ከተለያዩ ወገኖች ስለምርጫ በሚጠይቁበት ጊዜ ያለምንም ስጋት አስፈለጊ  ዝግጅት እያደረኩኝ ነው በማለት እየገለፀ እንደነበርና ከመቶ ሚልዮን በላይ ለሆነው የኢትዮዽያ ህዝብ በተስፋ ሲያስጠብቀው እንደነበር ለሁሉም ግልፅ ነው ። ከኢትዮዽያ የምርጫ ሂደት ወጣ ባለ መልኩ ሲንቀራፈፍና ክልክ በላይ ሲያዘግም እንደነበር ነፃ ህሊና ያለው ሰው የሚገነዘበው ጉዳይ ነው ። በዚሁ ዓመት እንኳን ካየን የተለያዩ አሳማኝ የማይመስሉ ምክንያቶችን እየጠቃቀሰ የምርጫ ጊዜው እየገፋው እንደመጣ ፣ ኢህአዴግ በህጋዊ መንገድ ሳይፈርስ እንዲሁ ብልፅግና የሚባል ፓርቲ በወራሽነት መቀበሉ ፣ በሌሎች አንኳር የምርጫ ጉዳዮች ላይ ከማተኮር ይልቅ በጆሃር መሓመድ ላይ አላስፈላጊ አጀንዳና ምልልሶች ማድረግ ፣ ወ.ዘ.ተ. ስናይ የምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ያለመሆን የሚያመላክቱ ብዙ ትዝብቶች ብህዝብ ላይ እንዳሉ ያስረዳል ።

Videos From Around The World

የምርጫ ቦርድ ገና ሲንቀራፈፍ በነበረበት ጊዜም የፖለቲካ ፓርቲዎችን ሳያሳትፍ እንዲሁ እንዳሻው ለህዝብ በማይመች ወቅት ምርጫው ከግንቦት ወደ ነሃሴ በማራዘም በክረምት እንዲካሄድ መወሰኑ ፣  ባጠቃላይ በርካታ የፈፀማቸው ተግባራት ሲታይ የምርጫ ቦርድ ምርጫ ለማካሄድ ገና ከጅምሩ ፍላጎት እንዳልነበረው ያሳያል ። በህገወጥ መንገድ የህዝብ ተወካዮች ወንበር ተቆናጦ  ያለው ብልፅግና ያሚባል ፓርቲ በህዝብ ተቀባይነት እንደሌለው ፣ ምርጫ ቢደረግም በዝረራ እንደሚሸነፍ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ በተቻለ መጠን የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር በስልጣን እንዲቆይና ለማራዘም ሲል የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም ። ስለዚህ ምርጫ ላለማካሄድ ትንሽም ትልቅም ፣ የረባም ያልረባ ምክንያት በውል ሳይለይ የመጣለትን አጋጣሚ ተጠቅሞ ምርጫውን መሰረዝና እንዳይካሄድ ማድረግ ሁነኛ ስልቶቹ እንደሆኑ ማንኛውም ነፃ ህሊናና አስተሳሰብ ያለው ሰው የሚገነዘበው ጉዳይ ነው ። ታድያ ይህ በህገወጥ መንገድ ስልጣን ይዞ ያለ  ፓርቲና የምርጫ ቦርድ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ይመስል ያለ በቂ ምክንያት የተወሰኑ ዜጎች በ COVID-19 ተጠቅተዋል በማለት ምርጫው ማካሄድ እንደማይችል ገና ለገና ሲያሳውቅ የምርጫ ቦርድ ምርጫው እንዲካሄድ ፍላጎት እንዳልነበረው በግልፅ የተረጋገጠበት ሁኔታ ነው የሚያሳየው ።

በ COVID-19 ምክንያት ምርጫ መሰረዝ ካለው የዓለማችን የምርጫ ሂደቶችን ስንመለከትና አሁን በኢትዮዽያ ያለው ተጨባጭ ሁኔታ ስናገናዝበው ጭራሽ ውሃ የሚቋጥር ምክንያት አይደለም ። በዓለማችን በአሁን ጊዜ እንደምናየው በርካታ አገሮች ከኢትዮዽያ በCOVID-19 የተጠቁ የዜጎች ብዛት በብዙ ሺ የሚበልጡ እንኳን ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ምርጫ እያካሄዱ ይገኛሉ ። ለምሳሌ ደቡበ ኮርያ ከወሰድን ኢትዮዽያ ምርጫው እንዳይካሄድ በ 15 April 2020 ባሳወቀችበት ጊዜ  በCOVID-19 የተጠቁ ከ 10000 በላይ ለህልፈት የተዳረጉ ደግሞ ከ200 በላይ እያለ ምርጫ አካሂዳለች ።  ኢትዮዽያ ምርጫ እንደማታካሂድ በገለፀችበት ጊዜ ግን በCOVID-19 የተጠቁ ዜጎች ከ50 በታች ና ለህልፈት የተዳረጉ ደግሞ 3 ነበሩ ። ታድያ በዚህ ወቅት በCOVID-19 የተጠቁ ብዛት በተነፃፃሪ ስለ ምርጫ ማካሄድና አለማካሄድ ለመወሰን እዚህ ግባ የማይባል መጠን እያለ የምርጫ ቦርድ ለምን በብርሃን ፍጥነት ምርጫ ማካሄድ እንደማይችል ገለፀ ። ይህንንም ቅድም እንደተገለፀው በተጨማሪ የምርጫ ቦርድ ምርጫው እንዲካሄድ ፍላጎት እንዳልነበረው በግልፅ የተረጋገጠበት ሁኔታ ነው የሚያሳየው ። ምርጫው የተቋረጠው እንዲሁ  በCOVID-19 ምክንያት ነው ተብሎ ለኢትዮዽያ ህዝብ ማሞኘት የጊዜ ጉዳይ ይሆናል እንጂ ቦርዱና አበሮቹ ከተጠያቂነት አያመልጡም ። በህገወጥ የተወካዮች ምክርቤት ወንበር ተቆናጠው የሚገኙት የብልፅግና አባላትም ህጋዊ ስልጣን የሌላቸው በኢትዮዽያ ጉዳይና በህገመንግስታችን ላይ እየተረማመዱበት ይገኛሉ ።    

እስቲ በምርጫ ቦርድ አስተያየት ለማየት እንሞክር ። ከ 50 በታች በCOVID-19 በተጠቁበት ጊዜ ምርጫው ማካሄድ አልችልም ካለ

·       በምርጫ ቦርድ አስተሳሰብ የተጠቂው ዜጋ ቁጥር ስንት ሲሆን ነው ምርጫው ማካሄድ የሚቻለው?

·       በምርጫ ቦርድ አስተሳሰብ የተጠቂው ዜጋ ቁጥር የሚፈለገው መጠን የሚደርሰውስ መቼ ነው?

·       የ COVID-19 በጣም እንደሚስፋፋ ወይም በቁጥጥር ስር እንደሚውል በዚህ ወቅት እንዴት ሊያውቅ ቻለ?

·       ወ.ዘ.ተ.

እነዚህን ጥያቄዎች የምርጫ ቦርዱ በውል ቢያያቸው ቢያንስ ለውሳኔ ባልቸኮለ ነበር ።ግን ከጅምሩ ቦርዱ ምርጫው እንዲካሄድ ፍላጎት ስላልነበረው ምርጫው ሊካሄድ የሚችልበትን ኣማራጮች የማየት ዕድል በቦርዱ ዝግ እንደነበሩ መረዳት ይቻላል ።

ባጠቃላይ ምርጫው በህገወጥነት የመንግስት ስልጣን ይዞ ያለ ብልፅግና ፓርቲና በ ምርጫ ቦርዱ ምርጫው እንዲካሄድ ስላልተፈለገ እንጂ COVID-19 ምክንያት ሆኖ አይደለም ።  

 

ታድያ ምን ተፈልጎ ነው ምርጫው ላለማካሄድ የሚደረገው ሩጫ ካልን በተለይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ግልፅ እየሆነ የመጣው ጉዳይ ስናይ በህገወጥነት የመንግስት ስልጣን ይዞ ያለ ብልፅግና ፓርቲ ከሌሎች የአሃዳዊ ፖለቲካ አራማጆች ከፍተኛ ቁርኝት እንዳለው ነው። እነዚህ አሃዳውያንም በተቻላቸው የብሄር ፖለቲካና በብሄር የመደራጀት መብት ለመከልከል ይህንን የኮሮና ጊዜ እንደ በጣም ጥሩ ዕድል በመጠቀመ ህጎች ፣ አወጆች በማፅደቅ ብሎም ህገ መንግስት ማሻሻል በሚል አባዜ የብሄር ብሄረሰቦች መብት መድፈቅ ና ሌላ ህገ መንግስት ማዘጋጀት የሚል አጀንዳ ለማስፈፀም ነው። ይህንን ለመፈፀም ብልፅግና ፓርቲ በስልጣን ለመቆየት የግድ ስለሚሆንበት COVID-19 እንደ ምክንያት ውሃ ባይቋጥርም ለስልጣን ማራዘሚያ እስከተጠቀመበት ጊዜ የምክንያታዊነት ነገር ለብልፅግና ጉዳዩ አይደለም። 

 

አንዳንድ ፖለቲከኞች በየዋህነት ይሁን በሌላ በተለይ በብሄር የተደራጁ ፖለቲከኞች እንዲሁ ጭልጥ ብለው  በ“COVID-19 ምክንያት ምርጫ ማካሄድ አይቻልም” ሲሉ ይደመጣሉ ። በትክክል ካየነው ግን ይህንን ሃሳብ በጭራሽ ማስተጋባት የለባቸውም ። ይህንን በስልጣን የመቆየት ከፍተኛ ፍላጎት በህገወጥነት የመንግስት ስልጣን ይዞ ላለ ብልፅግና ዕድሜውን በማራዘም ህግመንግስቱን በአሀዳውያን ፍላጎት ለመቅረፅ ዕድል መስጥት ስለሆነም ነው ። በተጨባጭ አመክንዮ COVID-19 ከምርጫ ጋር በማዛመድ ካየነው ምናልባት ህዝብ መአዳረሽ ሰብስቦ ያለህን የፖለቲካ ፕሮግራም ለማሳመንና ማስረፅ እንደተፈለገው ላይከወን ይችላል ። ይህንን ችግርና ሌሎች ተዛማች ችግሮች ግን የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም ማቃለል ይቻላል እንዲሁም ምርጫ ካካሄዱ አገሮችም ምርጥ ተሞክሮ መውሰድ ይቻላል ። በድምፅ አሰጣጥ ጊዜ ግን ህዝቡ ወጥቶ የፈለገው የሚመርጥበት ጊዜ አንድ ቀን ስለሆነች መራጩ ህዝብ ተራርቆ በቀላሉ ሊፈፅመው የሚችል ጉዳይ ነው ። እንኳን ለዚች የምርጫ አንድ ቀን ይቅርና የእለታዊ ተግባሩ በጥንቃቄ እያከናወነ ያለበት ሁኔታ ነው እያየን ያለነው ።

 

ስለዚህ የምርጫ ቦርዱ ምርጫ ማካሄድ አይቻልም ስላለ ብቻ ይህንን ሃሳብ እንደወረደ ወስዶ በተለይ በብሄር ፐለቲከኞች ማስተጋባት ከኡነትና በነፃ ህሊና ሚዛናዊ አስተሳሰብ የራቀ ነው ። እንደ ፖለቲካ ፓርቲ አሁን ማራገብ ያለባችው ሃሳብ ምርጫው በከፍተኛ ጥንቃቄ መካሄድ አለበት የሚለውን ይመስለኛል ። ይህንን ካልሆነ ግን ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎች ክልሎች በህገወጥ ወይም ህዝብ ባልመረጠው ቡድን የሚተዳደርበት ሁኔታ ስለሚፈጠር ፣ ይህንን ህገወጥ መንግስትም እንኳን ለፖለቲካ ፓርቲዎች ጉዳይ ሊጨነቅ በየጊዜው አዋጆችንና ህጎችን በየጊዜው እያወጣ የዴሞክራሲ ምህዳሩን ከማጥበብ አልፎ ዜጎችን በተለያየ ማንገድ ወደ ማሸበር ፣ ማፈን ፣ ማሰር ፣ መግደል ፣ ወ.ዘ.ተ. የመሳሰሉ አምባገነናዊ ተግባሮቸ የሚጠመድ እንደሚሆን ከባህሪው በቀላሉ መረዳት ይቻላል ። ይህንን አምባገነናዊ ስርዓት ደግሞ የማንኛውም አምባገነን መንግስት ባህሪ ስለሆነ በየትኛውም በአምባገነን ስርአት የሚመራ አገር እየተተገበረ ያለና ከዚህ በፊትም የነበረ እንደሆነ ታሪክ ያሳየናል ።

ስለዚህ የኢትዮዽያ ተቋዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች ለራሳችሁና ለህዝባችሁ ስትሉ አሁን በህገወጥነት የተወካዮች ምክርቤት የሙጥኝ ያለው ብልፅግና ፓርቲ ጠንካራ አቋማችሁን ብታሳዩ የትም ሊደርስ አይችልም ። አምባገነን መሪ ከአመባገነን መሪ ይወዳጃል ።  አምባገነን መሪ ከዴሞክራሲያዊ መሪ ግን በባህሪና በስርዓት በብዙ ስለሚለያዩ ግንኙነታቸው ሸካራ ነው። በአገራችንም የህገወጡ መንግስት መሪ ምንም የምርጫ ጭላንጭል ከማታውቀው ኤርትራ ና ከአለም ቁጥር አንድ አምባገነን መሪ ተወዳጅቶ የኢትዽያን ክብር መሬት ያስላሰ ብችኛ የዘመናችን ኢትዽያዊ ባንዳ ቢባል ያንሰዋል እንጂ አይበዛበትም  ።

 

አሁን በፌደራል በመንግስት ስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ እውነት እንነጋገር ከተባለ ህገወጥ ስለሆነ ባስቸኳይ የህዝብ ወንበር መልቀቅ ያለበት ይመስለኛል ምክንያቱም በህዝብ አልተመረጠም ። ማንገራገር ሳያስፈልገው ሁሉም የፖለተካ ፓርቲዎች ተሰባስበው አገር  መምራት ይገባል ። ይህ ፓርቲ እንደ ማንኛውም ፓርቲ ረድፉ ይዞ ሁሉም ለፖለቲካ ፓርቲዎች የተስማሙመበት ኣሻጋሪ በኣጭር ግዜ ምርጫው እስኪካሄድ መምራት አለበት የሚል አመለካከት ትክክለኛና ወቅታዊ ይመስለኛል።

 

ቸር እንሰንብት !!!

 

 

Back to Front Page