Back to Front Page

የ፻፶ ዓመት ግፍ

የ፻፶ ዓመት ግፍ

 

ሙሉጌታ በሪሁን

ከሃገረ ካናዳ

06-22-20

Email mba1277@gmail.com

 

 

የመቶ ሃምሳ ዓመት የአማራ ሊህቃን ግፍ ፤ የትግራይ ሃገረ መንግስትጋህድ ሊያደርግ ይችላል ።ወደ ዋናው ርእሴ ከመግባቴ በፊት ፡ በአንዲት የአለማችን አገር የተፈፀመው ዘይቤያዊ አነጋገር ልጥቀስ ይህም ለኛ ለኢትዮዽያዊያን ችግራችን ከወዴት እንደሆነ ይጠቁመናል የሚል እምነት ስላደረብኝ ነው።

የዚህች አገር ሕዝብ ለረጅም አመታት ፍትሃዊ ፣ ቅን መሪ ከማጣታቸው የተነሳ ምርር ብለው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑት ። እንዲህም ብለው አምላካቸውን ለመኑት ፤ ፈጣሪ አምላካችን ሆይ ፣ ምነው ? ምነው ? ከዚህ ሁሉ ጥበብህ አንድ ለኛ የሚሆን መሪ አጣህሳ ? 

 

እባክህን አምላካችን እንደ በጎ ፈቃድህ ሆኖ ፡ ለኛ የሚሆን መሪ ስጠን ፣ በማለት ምርር ብለው አልቅሰው ለመኑት ። ፈጣሪ አምላክም፡ የነገሩት የማይረሳ ፣ የለመኑት የማይነሳ ፤ ስለሆነ ችግራቸውን ካዳመጠ በኃላ ፣ በሉ ይሁን ችግራቹህና ፍላጎታችሁን ሰምቻለሁ ። ጥሩ መሪ ለዛውም ለናንተ የሚሆን አግኝቼላቹህአለህ አላቸው ። እነሱም በደስታ እየፈነደቁ የታለ ? አሉት እሱም ቀበል አረገና ይመጣል , ያው ከአሜሪካን አገር እስኪመጣላቹህ ታገሱ አላቸው ። ህዝቡም ደነገጠ ፣ ምነው ? በማለት ፣ ከእንግሊዝ አገር ላርግላቹህ እንዴ ? ብሎ ቢድጋሚ ጠየቃቸው ፣ ከህዝቡ መልስ የለም ካልወደዳችሁት ችግር የለም ከጣልያን አደርግላቹህለህ  እንግዲህ አለና እቅጩን ነገራቸው ።

 

Videos From Around The World

በዚህ ግዜ ከሕዝቡ ማሃል አንዱ አዛውንት ብድግ ብለው ፣ ፈጣሪ አምላካችን ሆይ ፣ እኛ የለመንህ ከዚህ ከማሃላችን እንጂ ፣ ከውጭ የማናውቀው ሰውማ በፍጹም አያስተዳድረንም ። ብለው ቁጭ ከማለታቸው በፊት ከህዝቡ የቀለጠ ጭብጨባ አጀባቸው ። እግዚአብሄርም በሁኔታቸው ተገርሞ ፣ ህዝቦቼ ሆይ ! ለጠየቃችሁኝ ጥያቄ ተገቢውን መልስ ብዬ ያመንኩበትን ሃሳብ አቀረብኩኝ ፣ በሌላ ዜጋም አንመራም አላችሁኝ ። ዋናው የመሪ ማጣት ችግር ምክንያቱኮ እናንተ እራሳቹህ ጥሩ መሪ ማፍለቅ ስላልቻላቹህ ነው ። እናንተ ያላፈራቹህት መሪ እኔ ከየት ላምጣላቹህ አላቸው ይባላል ። ውሃና እውነት እያደር ይጠራል አሉ ፡ ኢትዮዽያ በውሸት ትርክት የተገነባች ሃገር ነች ሲሉ ግራ ይገባኝ ነበር ፣ አሁን ግን ነገሮች ሁሉ እንደ ማለዳ ብርሃን ጥርት እያሉ መታየት ጀምረዋል ። 

 

በኔ የእድሜ ዘመን ፣ በመጠኑም ቢሆን የኢትዮዽያ ታሪክ ተምሬያለሁኝ ፣ የተለያዩ መጻህፍቶችንም አንብቤለሁኝም ። ከዚህ ሁሉ የተረዳሁት እውነታ ቢኖር ፨ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል ፨ የሚለውን የእንግሊዞች አባባል ትክክለኛነት ፣ ማረጋገጤን ነው ። ከኢትዮዽያ የታሪክ ደራሲያን ፡ ያስተዋልኩት ተጨባጭ ነገር ፣  የፅሁፍ ድርሳናት ታሪክ ይዘግቡና የታሪኩ ባለቤትነትን አድበስብሰዉት ያልፋሉ ። ወይንም ኢትዮዺያዊነት በምትለዋ ጭምብል ሸፋፍነዋት ያልፋሉ ። ይህች አባባል ደግሞ የአማራ ልሂቃን  ለአማርኛ ተናጋሪዎች በምትጥም ቀመር ፣ አንድ ሃገር ፤ አንድ ቛንቛ ፤ አንድ ሃይማኖት ፤ በሚል የጠቅላይና የአግላይ ኢትዮዽያዊነት ከዘመነ ምሊሊክ እስከ ዘመነ ደርግ ኖረንባት ፣ በዘመነ  ህ.ወ.ሓ.ት ኢህአዲግ ፣ አንቅረን ተፍተናታል ።  

 

ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች አገር ነች ። አለቀ ፤ ከዚህ ውጭ የሃገሪቱ እጣ ፋንታ መበታተን ብቻ ነው ፨

 

ዐረ ለመሆኑ በኢትዮዽያ ውስጥ ያላቹህ ሙሁራን ነን ባዮች ፣ ይህች እናንተ ነግቶ እስኪመሽ ድረስ  ውዲቷ ሃገራችን እያላቹህ በቃላት የምታሞካሿት ኢትዮዽያ ፡ እየፈራረሰች እያያቹህ ፣ የናንተ እውቀትና ትምህርት፡ ለዚህች ደሃና ፥ ምስኪን ሃገር ካልበጀ ምኑን ተማራቹህት ? ነው ወይስ አማራ የማይገዛት ኢትዮዽያ ትበታተን ? እስኪ ከተዛባው የታሪክ ፡ ሽለላና ፣ ፉከራ በሬ ወለደ ፤ ሁሉም የኛ ፤ የስግብግብ ትርክታቹህ ፡ በመጠኑ ልጥቀስ። አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል አሉ ። ትእግስት ፍራቻ አይደለም ፤ ሳንወድ በግድ እራሳችን እንድንከላከ ገፋችሁን ፣ አሁን ግን ወደኃላ ማለት የለም። 

 

   ፩ኛ እኛ ኢትዮዽያዊያን ቀደምት የሰው ዘር መፍለቂያ ነን ትላላቹህ ፣ ለዛ የታሪክ ባለቤት የአፋር ህዝብ ምን አረጋቹህለት ? እንደ ኢትዮዽያዊነቱ የረባ መንገድ ፣ ንጹህ የውሃ መጠጥ፣ ህክምና ወዘተ በቅጡ ያላገኘ ህዝብ በታሪኩ ግን እናንተ የቱሪዝም ገቢ ትሰበስቡበት አላቹህ ። ይህች ነች የናንተ ኢትዮዽያ !

 

  ፪ኛ ሃገራችን ኢትዮዽያ የ፫፼ሺ(3000) ዘመን የታሪክ ባለቤት ፤ እያላቹህ የውሸት ትርክት፡ ከመፍጠር፣ በታሪክ የትምህርት ካሪክለም ስርአታቹህ ለዛ የታሪኩ ባለቤት የሆነው ትግራዋይ አክሱማዊ ህዝብ ፤ ምን አይነት የታሪክ ባለቤትነት ሰጣችሁት ? ምንስ ክብር ሰጣችሁት ? በኢትዮዽያ ባህልና ቅርስ ሚኒስተር ስታስተዋውቁ ፣ ከጎንደርና ላሊበላ እኩል ፣ አክሱምን ሽፋን ትሰጣላቹህ እንዴ ?  ከምኒሊክ ፣ ሃይለ ስላሴ እስከ ደርግ የትግራይ ሕዝብ እንደ እምቢተኛና አማጺ ህዝብ ተቆጥሮ ከማንኛውም ሃገራዊ እድገቶች ተገልሎ በትምህርት፣ በጤና ፣ በመስተዳደራዊ በደሎች ተጠፍንጎ ፣ ከመሰቃየቱ ባሻገር በምኒሊክ ውሳኒ ከክፋይ አብራክ ወንድሙ ከሆነው የኤርትራ ህዝብ ሆን ተብሎ ተለያየ ። በመቀጠልም ሃይለ ስላሴ ፡ ከእንግሊዞች ጋር በመተባበር፣ በማይጨውና፣ በራያ ህዝብ ፡ በአውሮፕላን ቦምብ እንደ ውጭ ጠላት ደበደበን ። ያሁሉ አልበቃ ብሎ ፣ ደርግ በጠራራ ጽሃይ በሓውዜን ከተማ ለገበያ የወጣን ፪፼፭፻  (2500)ህዝብ ላይ የቦምብ ናዳ አወረደበት ። ለምን ? ኢትዮዽያዊ ስለሆነ ? ወይስ ያ ህዝብ አጥፍተህ ታሪኩን ለመውረስ ? ደረቅ የድንጋይ አገር ፣ ርሃብተኛ ፣ እያላቹህ ህዝቡን በስነልቦናው እየጎዳቹህ የትግራይ ህዝብ ታሪክ ፣ ባህል ፣ ቛንቛና ፣ ፊደል የባለቤትነት ህልማቹህ ለማሳካት ፤ ያልፈነቀላችሁት ድንጋይ ፣ ያልሸረባችሁት የክፋት ሴራ የለም ።  ግን የትግራይ ህዝብ ፈራሄ እግዚአብሄር የሚያጠቃው ህዝብ እንደመሆኑ ፣ ሁሉን ነገር አይቶ እንዳላየ ችላ እያለ ለ፩፻፶  (150)አመት ቻለ ፤ አሁን ግን ከወላጆቹ ለየት ያለ ፣ በእውቀትና ፣ በዘመናዊ ቴክኖለጂ ፣ የታጠቀ ወጣት ፣እንደ ወላጆቹ ፡ የራሱም የማይሰጥ ፤ የሰውም የማይመኝ ፤በትርክት ሳይሆን ፤ በጭብጥ የሚያምን ፤ ምክንያታዊ ወጣት የፈራበት ዘመን ላይ ስለደረስን ፤ ለታሪካችን ፣ ለባህላችን ፣ ለቛንቛችን ፣ ለፊደሎቻችን ፣ ለዘመን መቁጠርያ ቀመራችን ፣ ለያሪዳዊ ማህሌታችን ፣ በአጠቃላይ ለትግራዋይነት መገለጫችን ፣ ለክብራችን እንደ ዓይን ብሌናችን ተንከባክበን በዓለም እራሳችንን የምናስተዋውቅበት ግዜ ላይ ደርሰናል ።

  

፫ኛ ስለ ጀግንነት ትንሽ ልበል ፣ በርግጥ የተጋሩ ታሪክና ፣ ጀግንነት ፤ ከልደተ ክርስቶሰ በፊት ዘመናት ያስቆጠረ ቢሆንም ፡ ከንግስተ ሳባ ወዲህ የነ አፄ ካሌብ ፣አፄ ገብረ መስቀል ፣ አብርሃ ወ አጽብሃ ፣ ንጉስ ባዜን  ወ ዘ ተ ፤ ሳንጨምር ከ፻፳፭ (125) ዓመት ዘመነ መሳፍንት ወዲህ ያለው የኢትዮዽያ አመሰራረት እንመልከት። 

     

አፄ ቴዎድሮሰ ፤ 

እንደ ኢትዮዽያዊያን ወግና ባህል ፡ ልጅ ሲወለድ የሚጠራው በወላጅ አባቱ ነው። ይህ ከጥንት እስከ ዛሬዋ እለት የምንጠቀምበት ባህላዊ አጠራራችን ነው ። አፄ ቴዎድሮስ ደግሞ ከትግራዋይ አባታቸው ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ እና  ከእናታቸው ወይዘሮ ትሻል ፤ ቛራ ውስጥ ተወለዱ ። ታድያ የአፄ ቴዎድሮስ ታሪክ ሲወራና ፣ ሲተረክ የአባታቸው ሳይሆን ፣ ቅማንት እናታቸው የኮሶ ሻጭ ልጅ እየተባሉ ፣ መሆናቸው ብቻ ነው። ለምን  ? አባት የላቸውም  ? የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ፣ ልዑል አለማዮህ ቴዎድሮስ ፣ ከወይዘሮ ጥሩወርቅ ዉቤ ፣ የደጃዝማች ውቤ ሃይለማርያም ከትግራይ የዘር ግንድ ስለሚወለድ ታሪኩ ተድበስብሶ ብዙም አይወራለትም ። አሁን አሁንማ የአፄ ቴዎድሮስ የማንነት መብት ወደ ቅማንት በመዛወሩ ስማቸው በአማራ ሊህቃን እንደድሮ አይደለም።  

   

አፄ ዮውሃንስ

 አፄ ቴዎድሮስ የጀመሩትን የኢትዮዽያ ምስረታ ፣ አፄ ዮውሃንስ ቀጥለውበት ኤርትራ ፣ ትግራይ ፣አፋር፣ በጌምድር ፣ወሎ ፣ጎጃም ፣ ሽዋ እንዲሁም የተወሰኑ የኦሮሞ ጎሳዎችን አጠቃለው ፡ የየአከባቢው ንጉሶች በመሾም ፣ አፄ ዮውሃንስ ፡ ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮዽያ ሆነው ከማስተዳደርም በላይ ፣ ከውጭ የመጡትን የውጭ ወራሪ ሃይሎች ፤ ማለትም ግብፆችን፣ጣልያኖችን ፣ማህዲስቶችን ፡ በዶግዓሊ ፣ በሰሃጢጥ፣ በጉራዕ ፣ በመተማ ድል በማድረግ የሃገራቸውን ዳር ድምበርና የግዛት አንድነት፣ በክብር ጠብቀውና አስጠብቀው ፣ ለኢትዮዽያ ሃገራቸው አንገታቸውን ሰጥተዋል ተሰውተዋል። 

 

በአማራ ሊሂቃን የድል ዲስኩር ፣ ዘለው ስለ አድዋ ድል ይቦጠረቃሉ ፤በጣም የሚያሳዝነውና የሚያሳፍረው ደግሞ ፤ ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሃገር ወራሪ ጣልያንን አድዋ ላይ ድል የተጎናፀፈች ይላሉ ።ለተቀረው የኢትዮዽያ ህዝብ በርግጥ የመጀመርያው ድል ነው ። ለተጋሩ ህዝበ አግአዚያን ግን ነጭንና አረብን ድል ማድረግ ከነ ዘመነ አፄ ካሌብ ግዜ ጀምሮ እነ ንጉስ ኤዛና እና ሲዛና በድል አድራጊነታቸው ከየመን እስከ ሞቓዲሾ ማዳጋስካር ድረስ ይታወቁ ነበር ።

 

በአማራ ልሂቃን አስተሳሰብ የትግራይ ጀግንነት በኢትዮዽያ ታሪክ ከሚፃፍ ኢትዮዽያ እስከወዲያኛው በችግር ሰቆቃ ብትማቅቅ ይመርጣሉ ። እኔ ምለው የአማራ መሳፍንት ለምን ዶግዓሊን ፣ ስሃጢጥን ፣ ጉሯዕን መጥቀስ አይወዱም ? ምክንያቱም የተጋሩና ፧ የተጋሩ ብቻ ስለሆነ ነው ።  ለዚህም ነው በውሸት ትርክት የተሞላው የኢትዮዽያ ታሪክ ፣ ለበለ ታሪኮቹ ፣ መመለስ ያለበት። የትግራይ ታሪክ እየተድበሰበሰ ፣ የተዛባ የአማራ ትርክት ወድ መስመሩ ለመመለስ ፣ ማጋለጥ ፣ በማስረጃ መሞገት ያለብን ጊዜው አሁን ነው ። በርግጥ ከ፻ (100)አመት በላይ የተካሄደብን ተንኮልና ፣ ደባ ቀላል ባይሆንም ፤ አሁን ለደረስንበት ደረጃ ለመድረስም ቀላል የማይባል የሂወትና ፣ የአካል መስዋእትነት ከፍለንበታል ፡ ፷፭ሺ (65,000) የሂወት ፤ ፻፳፭ሺ  (125,000)የአካል ፤ መስዋእትነት ተከፍሎበታል ክብር ለሰማዕታቶቻችን ይሁን ።

 

ለማጠቃለል ያህል ፤ እነዚህ ሁለት ንጉሶች ፡ማለትም አፄ ቴዎድሮስና አፄ ዮውሃንስ ፬ኛው በጊዜያቸው የቻሉትን ያህል ለሃገራቸው ሰርተው ፤ ለሚወዷት ኢትዮዽያ ሂወታቸውን ገብረዋል በኢትዮዽያ ታሪክ ትልቅ የማይሻር አሻራ ትተው  አልፏል። 

          

አጼ ምኒሊክ 

በርግጥ ታሪክ እንዳበጁት ይበጃል ሆኖብን ፣ ደራሲያን የገዢው መደብ ዝናን በማንቆለጳጰስ፣  በማሸርገድ ፣ ዝናቸውን ከመገንባት ባሻገር እውነቱን ፈልፍሎ የማውጣት ጥረት አይታይባቸውም ። ከኛ ደራሲያን ይልቅ ፡ የውጭ ደራሲያን ፡ሚዛናዊንትና ፡ ተአማኒነት ይታይበታል ፣ ለምሳሌ ጀምስ ብሩሰ፣ ሪቻርድ ፖንክረስት ፣ሃጋይ ኢርልች ራስ አሉላ ከ፼፰፻፸፭ እስከ ፼፰፻፺፯  ወዘተ በተለያዩ ወቅት የፃፉትን መጥቀስ ይቻላል።  

ስለዚህ ወደ ታሪክ አዘጋገባችን መለስ ብለን ስናጤነው ፡ ሁሉም በየፊናው ስለሚጽፈው ፡ ለሁሉም የሚያስማማ ታሪክ የለንም ። አማራ ፡ የአማራን ታሪክ እያጎላ ሲፅፍ ፣ተጋሩም ከዚህ ባልተናነሰ መንገድ መሄዳችን ሊያስኮንነ አይችልም ። ፍርዱ መሬት ላይ ባለ ተጨባጭ ሁኔታ ይረጋገጣል ።

 

እንግዲህ አፄ ምኒሊክ ፡ ከአፄ ዮውሃንስ የተረከቧትን ኢትዮዽያ ፡ ስንመለከታት ከነበራት ቅርጽ አንሳና ገዝፋም እናያታለን ። አንሳ ስንል ፤ ባህር አልባ ሆና ማለታችን ነው ። እንዴት ከተባለ ጅቡቲ ለፈረንሳይ ለ፻  (100)ዓመት የኾንትራት ውል ተሰጠች ፤ ኤርትራ ደግሞ በውጫሌና በፈረስ ማይ ውል ከመረብ ምላሽ ለጣልያን እንደገፀ በረከት ተሰጠች ። ይህ ነው ሀቁ እሬት እሬት እያለንም ቢሆን መቀበል ግድ ይለናል፤ የአማራ ፖለቲከኞች ፤የአብየን እከክ ፣ ለእምየ ልክክ ፤ ትርክታቸውን የምንፋለመው በእንደዚህ አይነት ፍልሚያ ይሆናል ።

 

በመቀጠል ወደ ቅድመና፣ድህረ አድዋ ጦርነት ስንመለስ ደግሞ ፣ የጣልያን ወራሪ ጦር ፡ መረብን ተሻግሮ ገብቶ ለ፯ወር ያህል የትግራይ ህዝብ ገትሮ ይዞታል ። ከዛም ሌላው የኢትዮዽያ ሃይል እንደደረሰ ተጠራርጎ ከተባረረ በኃላ ፤ በራስ አሉላና ፡ በባሻይ አውዓሎም ወታደራዊ ምክክር ፣ባሻይ አውዓሎም ፡ የጣልያን ጀነራሎችን የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ፨ የኢትዮዽያ ሰራዊት በባአል ጦርነት አያደርግም ፨   ብለው ሰራዊቱን መርተው ከራስ አሉላ ጋር ባዘጋጁት ወጥመድ ውስጥ አስገብተው የጦርነቱ ፍፃሜ  በኢትዮዽያ ድል አድራጊነት ተጠናቜል።እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው ፡ እያወራን ያለነው ስለ ሃገር ስለሆነ ፡ ሃገሪቱም መሪ ስለነበራት ፡ የድሉ ባለቤትም የሃገሪቱ መሪ እንደመሪ ይወደስበታል ። የአድዋ ድል የምኒሊክ የመሪነት ብቃት ነው ከተባለ ፤ ዶግአሊስ ? ስሃጢጥስ ?ጉራዕስ ? የአባይ ግድብስ ? ሁሉም የመሪነት ብቃት የጠየቁ አኩሪ የድል ውጤቶች ናቸው ። ሚዛናዊ ፍርድ ከዚህ ይጀምራል ።

 

አንተ ፣ አንቺ የኔን የቀደመውን የወላጆቼ ታሪክ ስታከብር ፣ ስታከብሪ ፣ እኔ፣ እኛ ደግሞ በፍቅርና በአክብሮት ፣ታሪካችሁን እናከብርላቹሃለን ።ይሄው ነው በተለይ የአማራ ሊህቃን ፡ የትግራይና ፤ የተጋሩ መሪዎች ፡ የአመራር ብቃት ፣ የሚታይ የሚዳሰስ ሆና እያለ ፡ ሃገሪቱ ለደረሰችበት እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ አድርገው እያሉ ፡ ይሄ የበሬ ወለደ ፣ እኛ ብቻ ፣ ባህሪያቸውን እስካልገቱ ፡ ከእንግዲህ በትእግስት መጠበቁ ፡ እንደ ተስፈኛዋ ቀበሮ ፡ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ፡ ብላ ስትከተለው እንደመዋል ይሆናል ።

  

ለሁሉም ልክ አለው ፣ የያንዳንዱ መሪ ድክመት ስንዘረዝር ግዜ ከማባከን ፣ መሪዎቻችን ከሰሩት ስህተት ተምረንበት ፤ በጀመሩልን ቀና መንገድ ምኞቶቻቸውን አሟልተን ፤ ለልጆቻችን የበለፀገች ኢትዮዽያን ማውረሱ ብልህነት ይመስለኛል ። ካልሆነ በ፳፩ኛው ክፍለዘመን ፣ በውሸት ትርክት የሚነዳ ሰው ፨ በስቶን ኤጅ ፨ ግዜ የሚኖር መሆን አለበት ።

 

ምኒሊክ ፣ ሃይለ ስላሴ ፣ደርግ ለትግራይ ህዝብ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል ፈጽመውበታል ። እንደ ሃገርም ኢትዮዽያን ጎድተዋታል፣የቻሉትን ያህል ደግሞ ሰርተውላታል ። በታሪክ ሁሉም ጉልህ የሆነ አሻራ እንዳላቸው ሁሉ ፣ የታሪክ ተጠያቂዎችም ናቸው ። ለዚህም እኮ ነው  አዋቂ ወላጆቻችን ሲተርቱ ፨ እምዬ ኢትዮዽያ እምየ አዶላ ፤ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ፨ ያሉት ። እነ ቴዎድሮስ ፣ ዮውሃንስ ፣ መለስ በየፊናቸው ሲሞቱላት ፤ እነ ምኒሊክ ፣ ሃይለ ስላሴ፣  መንግስቱ ሃይለማርያም ፣ ደግሞ ጥለዋት ይኮበልላሉ ይህ ነውሃቁ ። የአማራ ልሂቃን ግን የሰሩትን ወደ ጎን ትተው ፣ የፈረጠጡትን ፤ እስከ ዛሬዋ እለት እንደ ሃገር ገምቢዎችና ባለውለታዎች ታሪካቸው ሲያላዝኑብን ይውላሉ።

 

የህንን ፅሁፍ ለሞበጫጨር ያነሳሳኝም ፣ ይሄ ህዝብ ካለፈው ሰህተት መማር ይችላል ወይ ? በኔ የሂወት ዘመን ፡ በንጉሱ ህፃንም ስለነበርኩኝ ብዙ ቁም ነገር ያለው ነገር አላውቅም  ፣ የደርግን ቀይ ሽብር ግን አይቻለሁኝ ፤ የሰው ልጅ ጭንቅላቱ በጥይት ሁለት ቦታ ተከፍሎ ፣ ቀይ ሽብር ይፋፋም ብላቹህ ዘምሩ ብለው ሲያስፈራሩን ፣ እኔም የነገሩ አስከፊነት ባይገባኝም የወጣትነት ዘመኔ ያሳለፍኩትን, ያየሁትን, የሂወቴ መጥፎ ገፅታ  ልረሳው አልችልም ። አሁን ወደኃላ መለስ ብዬ ግዜውን ፡ ሳጤነው ይህን ያህል በሰው ልጅ መጨከኑ አውሬነት ይመስለኛል ። በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ ፡ ላለፉት ፳፯  (27)ዓመታት የጨለማ ግዜ ነበር። በማለት አብይ አህመድ የአሜሪካን ዳያስፖራ ለማስደሰት የተናገረውን ንግግር ስሰማ ፤ ጭራሽ የኢትዮዽያ ህዝብ በመግቢያዬ የጠቀስኴቸውን ህዝቦች መስሎ ተሰማኝ ። ህዝብ  ግዜና ዓመታት በጨመሩ ቁጥር ፡ የሰው ልጅ አስተሳሰብም ያድጋል ፣ ይዳብራል፣ ይጨምራል ። የሚል እምነት ቢኖረኝም ፣የኢትዮዽያ ህዝብ ግን እንደ ከብት ወደፈለጉት አቅጣጫ የሚነዳ ነው ብሎ ለማመን ቢከብድም ። በተለይ የአማራ ፖለቲከኞች በጎንደር በትግራዎት ላይ የፈፀሙት ግፍ ፣በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በሁለት ዶክተሮች የተፈፀመው ግድያ፣ ሻሸመኔ በአንድ ወጣት ላይ የተደረገውን ዘግናኝ ግድያ ፣ ከኢትዮዽያዊነት ባህል ያፈነገጠ ጭራሽ ስብአዊ ርህራሄ የጎደለው ድርጊት ስመለከት ፣ ኢትዮዽያዊነቴን ጠላሁት ። በትግራዋይነቴም ኮራሁኝ  ። የጨለማው ዘመን ጋህድ መሆኑም አየሁኝ  አሁን ከመቸውም ጊዜ በላይ ኢትዮዽያ የቁልቁል ጊዜ ፣ ጋህድ የሆነ የጨለማ መንገድ ጀምራለች ። እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው ቁም ነገር ማንም ስላለ ሳይሆን እኛ ተጋሩ ስላልን ነው ።

 

እዚህ ላይ የአማራ ሊህቃን፣ የአማራ ሚድያ ፣ የአማራ ዳያስፖራ በሚያሳዩት የትምክህት ፡ አመለካከትና ሁሉም የኛ ፣ የቅዠት አባዜ ላይ ፤ውሃ ልቸልስበት ወድጃለሁኝ ። ከላይ እንደጠቀስኩት አማሮች ፣ እነሱ የፈለጉት ፣ ወይም ከነሱ መሀከል የራሳቸው ዘር ፤ የፈለገውን ግፍ ፣ ክህደት ፣ አገር ማፍረስ ፣ ርሸና, ብዝበዛ ፣ ወ.ዘ.ተ ሲፈጽም ለሃገር እድገትና ፡ ለጽድቅ ነው ። ሌላው ከነሱ ዘር ውጭ ያለው ኢትዮዽያዊ ፤ የሚለፋው ፣ የሚደክመው ፤ የሰራው ፡ የገነባው ፡ አፍራሽና ለኢትዮዽያ የማይጠቅም በማስመሰል ጥላሸት ከመቀባት ውጭ ሌላ ሰራ የላቸውም ። ለምሳሌ እሩቅ ሳንሄድ ፣ አያት ቅድመ አያቶቻቸው ያላሰቡት ፣ ያልደፈሩትን ፣ የአባይ ግድብን  የደፈረውና በአካል ተገኝቶ የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ ስራውን ያስጀመረውን ጠ/ሚር መለስ ዜናዊ ። ለጥቁሮች ኩራት በመሆኑ ድፍን የአለም ጥቁሮች የደገፉትን የአለም የጤና ድርጅት መሪ ክቡር ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ኢትዮዽያን ወክሎ ለአለም ጤና ድርጅት ሲወዳደር, ከነጮቹ ተፎካካሪዎቹ በላይ የተቃወሙት የአማራ ሊሂቃንና የአማራ ዳያስፖራዎች ነበሩ። ለምን ? ካልን ትግራዋይ ፤ ወያናይ ስለሆነ ብቻ ።የአለም ጤና ድርጅት በወንጀል የሚጠረጠርን ሰው ለሃላፊነት አያቀርብም ። የኛዎቹ የአማራ ጉዶች ግን፡ ኢትዮዽያ ለነሱ በአማራዎች አስተሳሰብ ብቻ የተዋቀረች መሆን አለባት ። ከዚህ ውጪ ኦሮሞ ፣ ትግራይ ፣ሶማሌ ወላይታ ጉራጌ ወ.ዘ.ተ ለነሱ ትርጉም የለዉም ፤ ሌላው አቶ ተወልደ ገማርያምን ፣ የኢትዮዽያ አየር መንገድ ስራአስኪያጅን ተመልከቱ ።ድርጅቱን ከየት አንስቶ የት እንዳደረሰው ፣ የኢትዮዽያ ህዝብ የአይን ምስክር እያለ ፣ የውሸት ታሪክ እየፈጠሩ ህዝቡን ሊያሳስቱት ይሞክራሉ ።

 

ግን መዋረድ የለመዱ ውርደታሞች ፣ ስለሆኑ በሄዱበት ሁሉ ያፍራሉ ። ትግራዋይ ሰርቶ ማሳየትን እንጂ ዋሽቶ ፣መስሎ መኖርን አልለመደበትም ፨ ሌላው ከጀመርኩት አይቀር ቛቕ እስኪላቸው ልንገራቸው ፡ የአክሱም ሐወልትን በተመለከተ ይሆናል ፣ ይሄውም ሐወልቱን ጣልያን ከወሰደው በኃላ ሃይለ ስላሴ ካሳ እንዲሰጠው እና ነገሩን እርግፍ አድርጎ እንዲተው ካግባቡት በኃላ፣ ትልቅ ሆስፒታል እንዲሰራ ተወሰነ ። የሐወልቱን ካሳ ፣ሐወልቱ ከተወሰደበት ቦታ አክሱም ትልቅ ሪፈራል ሆሰፒታል ልስራ ሲል ጣልያን ፤ ሃይለ ስላሴ ግን ሆስፒታሉ በአዲስ አበባ የዛሬው ጥቁር አንበሳ ሆሰፒታል አሰርቶ ፣አክሱም ከተማ ደግሞ ፡ አሁንም ያለ ምንም ብዙ ለውጥ ያለውን ሆሰፒታል አሰራ። ይህ ነውሃቁ ፤ግን ትግራዋይ ላመነበት ማንኛውም ነገር እስከ ሂወት መስዋእትነት ስለሚከፍል ፤ ጠሚ መለስ ኢትዮዽያን መምራት በጀመረበት ግዜ ከእቅዶቹ አንዱ ፤ የትግራይ ንብረት የሆነው የአክሱም ሐወልት ወደ ቦታው በክብር ማስመለስ ነበር ። አደረገውም ፨  ሐወልታችን በመሬታችን ውስጥ ይገኛል ። ክብር ለትግራይ ልጆች ለሃገራቸው ውድ ሂወታቸው ለገበሩት ሰማእታት ይሁንልኝ ።

 

ዲሞክራሲ ሌላው የሄ የነ ብርሃኑ ነጋ ፡ ጥቅም ወዳለበት እያነፈነፉ ፡ ወደ ነፈሰው የሚነፍስ የአማራ ፖለቲካ ትንሽ ልበል ።ስም በመቀያየር ስልጣን የሚገኝ ቢሆን ኖሮ, ብርሃኑ ነጋ ከአንዴም አምስቴ የኢትዮዽያ መሪ በሆነ ነበር ። ጠ/ሚ መለስ እንዳለው የፖለቲካ ስልጣን እንካ ተብሎ አይሰጥም ። ታግለህ መስዋእትነት ከፍለህ ነው የፖለቲካ ስልጣን የሚገኘው ፤ እነ ብርሽም ሆኑ እነ አብይ አህመድ በጮሌነት ያገኙትን እድል እጃቸው ላይ እየተፈረካከስ ማየት እንደሚያሳፍር ነገር የለም ። ፅኑ አላማ ሲኖርህ እስከነ ስህተትህ ድክመቶችህን ጭምር በሂደት ይታረማሉ በማለት ህዝብ ይከተልሃል ። ህወሐት በአሁኑ ስአት ድፍን የትግራይ ህዝብ ከጎኑ ያሰለፈ የፖለቲካ ድርጅት ነው ።  ከሌሎች የፖለቲካ ፖርቲዎች የሚለየው ወያነ ፣ ሁላችን ተጋሩ ወያኔዎች ነን ፣  ሁላችን ጌታቸው አሰፋዎች ነን ።

 

እነ ብርሃኑ ነጋ ስለ ዲሞክራሲ ሲያወሩ ስሰማ ይገርመኛል ። እሱ በነበረበት ሃገር አሜሪካ እስር ቤቶቿ በጥቁሮች የተሞላባት ሃገር ውስጥ ኖሮ ትናንትና ጆርጅ ፍሎይድ ፣ ጥቁር በመሆኑ ነጭ ፖሊስ ሂወቱን ባሳለፈበት አገር ቤተሰብህና አንተ እየኖርክ ፤ ስለ ኢህአዲግ ህወሓትን አምባገነንነት ስታወራ ፣ ስታወሩ ታሳፍራላቹህ ። ሌሎችን ሲወነጅል ፤ የሰው ልጅ ያለ ምንም ጥፋቱ ሰለተቃወመ በጉድጏድ ውሰጥ ከ፲፰ (18)አመት በላይ በሚታሰሩባት ሃገረ ኤርትራ የጉንበት ፯ ድርጅት የጦር መሪ ሆኖ ከኢሳያስ አፈወርቂ ስልጠና እና ቡራኬ የተቸረው ስው ስለዲሞክራሲ ሲያወራ ግራ ይገባኛል ፤ ለማያውቅሽ ታጠኝ አለ ። ስለ የትኛው አለም ዲሞክራሲ ነው የምናውራው ? ስለ ራሻው ፑትን ?ሰለ አሜሪካው ዶናልድ ትራምፕ ?ሰለ ቻይናው ዢንግ ? ሰለ ሰሜን ኮርያው ፒንግያንግ ? ወይስ ስለ ከ፳ (20)ዓመት በላይ ስልጣናቸው እያራዘሙ ሙጥኝ ሰለሚሉት አምባገነን የአፍሪካ መሪዎች ።

 

ዲሞክራሲ ለአማራዎች ምንድነው ? የቅማንትን ህዝብ በጥይት መፍጀት ? የአገውን ህዝብ ማንነት መደፍጠጥ? የቤንሻንጉል መተከል ህዝብ በልዩ ሃይል መጨፍጨፍ ? ለትምህርት የመጡትን ንጹሃን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በድንጋይ ወግሮ መግደል ? ተዋልዶ ከብዶ የኖረውን ትግራዋይ ንብረቱን ዘርፎ ማባረር ? ታድያ ዲሞክራሲ ውስጣቹህን ሳታፀዱ ሁሉም የኛ ብትሉስ ማን ይፈልጋቹሃል ? ዲሞክራሲ ፣ ፍቅር ፣ ከራስ ይጀምራል ሌላውም እያየ ይከተላል ። ላለፉት ሁለት አመታት ስለ ኢትዮዽያና ኢትዮዽያዊነት፣ ስለህዝብና ህዝቦች ፣ ስለአማራና አማራነት ፣ ከሚበቃን በላይ አየን እኛ ተጋሩ የምንደክመው ፣ የምንለፋው ፣ የምንሞተው ለብልጣብልጦች ለከሃገር በፊት ሆዳቸውን የሚወዱ እስስቶች ፣ መሆኑ ዘግይቶም ቢሆን ገብቶናል ። የሚያኮራ ታሪክና ውጤታማ የሚታይ ፣ የሚጨበጥ ፣ ውጤትም አሳይተናል ። ማንም ሁን ማንም ለዚህች የአሁኗ ኢትዮዽያ ፣ ከትግራዋይ በላይ የለፋላት የደከመላት ፣ እንዲሁም የሞተላት የለም ። አስረግጨ እነግርሃለሁኝ ፨ እኔን መርታት የምትችለው በወሬ ሳይሆን ፣ ሰርተህ ፣ ቆጥረህ ስታወራርድ ብቻ ነው ። እስከ ዛ ድረስ ግን ለምርጫ እየተዘጋጀሁኝ ስለሆነ ግዜዬን አታባክንብኝ ።

        

     

 


Back to Front Page