Back to Front Page


Share This Article!
Share
አዲስ አበባ የማናት?

አዲስ አበባ የማናት?

በደምሴ አዱኛ 2-12-19

ጀዋር መሃመድ ከጥቂት ቀናት በፊት በ OMN ላይ ባደረገው ቃለ መጠይቅ አዲስ አበባ የኦሮሞ እንደሆነች ገልጿል፡፡ ይህን እውነታ፤ ማለትም አዲስ አበባ የኦሮሞ መሆኗን የሚቃወም ካለቄሮዎችን ትግላችሁ አላለቀምና ቀጥሉበት እንላቸዋለን እያለ ማሰጠንቀቂያም ጭምር በቃለ መጠይቁ ላይ አስተላልፏል፡፡ ቃለ መጠይቁ በሌላ የመገናኛ ሜዲያ ቢሆን ኖሮ ይህን ያህልክብደት አልሰጠውም ነበር፡፡ በራሱ መገናኛ በ OMN የተቀነባበረ በመሆኑ ጀዋር የአዲስ አበባን ጉዳይ ወደ ፊት ሊገፋ ቆርጦ የተነሳ ይመስለኛል፡፡ ሰሞኑን በብዙ ድረ ገጾችና ሜዲያዎች ላይበእንጂነር ታከለ ኡማ ላይ የሚነሱትን ተቃውሞዎች ዝም ለማሰኘት ያሰበም ሊሆን ይችላል፡፡ ስለታከለ አታውሩ፤ ስለታከለ ይቅርና ስለአዲስ አበባ እናንተ ማውራት አትችሉም አዲስ አበባ የኛናትና በማለት፡፡ ጀዋር አንድን ነገር ከጀመረ ሙሉ ሃይሉን በመጠቀም ይገፋባታል እንጂ ጀምሮ የማቆም ባህርይ የለውም።

Videos From Around The World

ጀዋር ከጊዜ ወደ ጊዜ ሀሳቦቹን ከጊዜው ሁኔታ ጋር ቢቀያይርም ዋና አለማው የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም ማስጠበቅ መሆኑን ያልገለጸበትና ይህን መሰረተ ሀሳብ የለቀቀበት ጊዜ የለም፡፡ ስለጀዋርሶስት ነገሮችን ብገልጽ የተሳሳትኩ አይመስለኝም፡፡ እነዚም፤

1፡) ጀዋር ችሎታና እውቀት አለው፡፡

2:) ጀዋር የኦሮሞን ህዝብ ፍላጎትና ብሶት ይረዳል፡፡

3:) ይህን የተረዳውን የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትና ብሶት ባለው ችሎታ አሳምሮና አጣፍጦ መልሶ ሲነግራቸው ከዳር እስከዳር ኦሮሞዎች ይሰሙታል፡፡ ይህም ነው ተሰሚነት እንዲኖረውያደረገው፡፡ ብዙ ተቃዋሚ ቢኖረውም ጀዋር በኢትዮጵያ ምድር ወደር የሌለው ሰሚና ተከታይ ያለው ሰው ነው። መላውን የኦሮሚያ ክልል መዞርና ከዳር እስከዳር በየቦታው የተሰቀሉ ፎቶዎቹን ማየት ብቻ በቂ ነው ጀዋር ተሰሚነት ያለው መሆኑን። ጀዋር ዋና አለማውን ወደፊት ከመግፋት በስተቀር በሌላ ነገር ጊዘውን አያባክንም። ለሚደርሱበት ክሶችና ስድቦች መልስ አይሰጥም። ለምሳሌ የኢሳት ሳተላይት ቲቪ ስሙን እየጠሩ ሲሰድቡት አንድም ቀን ስማቸውን አንስቶ አያውቅም። ራሱን ዝቅ አድርጎ ከእሳት ጋርም ሆነ ከሚከሱት ጋር ለመነታረክ አይፈልግም።

 

ጀዋር በትግላችን የነበረብንን ጭቆና ገርስሰን ጥለናል ይላል።  አሸንፈናል ይላል። በኔ አመለካከት ጭቆናው ይገርሰስ እንጂ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ተመልሷል ወይ? ተመልሷል የሚሉ እንዳሉ ሁሉአልተመለሰም የሚሉ ከግለሰብ አንስቶ እስከ ፖለቲካ ድርጅቶች ድረስ አሉ፡፡ እኔም አልተመለሰም ከሚሉት ወገን ነኝ፡፡ እንዲያውም የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ አልተመለሰም ባይ ነኝ፡፡ እኔ ለማየት የምፈልገውና የህዝቡ ጥያቄ ተመልሷል ማለት የምችለው  በመሬት አቀማመጥ እንጂ በብሄር ያልተከፋፈለች ኢትዮጵያን፤ ሰው በዜግነቱየተከበረባትን ኢትዮጵያ፤ የሁሉም ህዝብ ቋንቋ ባህልና ሃይማኖት እኩል የተከበሩባት  ኢትዮጵያን ስናይ ብቻ ነው፡፡ ይህ ጽኑ አቋሜ እና ፍላጎቴ ስለሆነም ነው ቀደም ሲል በኢትዮጵያ እስከ አሁን ድረስ የህዝብ ጥያቄ አልተመለሰም ያልኩት፡፡ አቋሜንና ፍላጎቴን ግን ብሄር ተኮር የሆነ ክልል በኢትዮጵያ ያስፈልገናል በሚሉት ላይ ምንም አይነት ተጽእኖ ማድረግ አልፈልግም፡፡አልቃወማቸውምም፡፡ እንዲያውም እደግፋቸዋለሁ፡፡ ባንቀዋመምና ብንደጋገፍ ነው አብረን በሰላም ለመኖር የምንችለው፡፡ መደገፍ መደጋገፍ ብቻ ሳይሆን ሀሳብ መሰጣጠትና መለዋወጥደግሞ የበለጠ ያቀራርባል ብዬ አምናለሁ፡፡

ስለሁሉም ክልሎች በዚች አጭር ጽሁፌ ማካተት ባልችልም ለጊዜው ስለ ትግራይና ስለኦሮሞ ክልሎች ያሉኝን ሀሳቦች ጣል ጣል ለማድረግ እሞክራለሁ፡፡ ሀሳቦቼ የሚያናድዱት ሰው ካለበንዴት ራሱን ከሚጎዳ ማንበቡን እዚሁ ላይ እንዲያቆም ሁለት ነጥቦችን አስቀድሜ እጠቅሳለሁ፡፡ ከነዚህም ነጥቦች አንደኛው  በኢትዮጵያ ክልሎች እንዲኖሩ ከተፈለገ ክልሎቹ በትግራይክልል ሞዴል መሆን አለባቸው፡፡ ሁለተኛው ነጥቤ ደግሞ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት፡፡

ሌላ ተጨማሪ ነጥብ የኦሮሞ ጥያቄ ሲሆን ይህም ጥያቄ አልተመለሰም ባይ ንኝ፡፡ በአጭሩ ለምን የትግራይ ክልልን እንደ ሞዴል የመረጥኩበት ምክኒያት ሥልጣንና የሥልጣን ክፍፍልበፌዴራልና በክልል መካከል ምን መሆን እንዳለበት የትግራይ ክልል በግልጽ ስለአሳየኝ ነው፡፡ አንድ ነገር ካለ አለ ነው ከሌላም ደግሞ የለም ነው፡፡ መሃል ላይ የሚዋልል ነገር የለም፡፡ አለወይንም የለም፡፡ ክልል ካለ ክልሉን የሚመለከቱ ህጎችና የሚወሰዱ እርምጃዎች በሙሉ በክልሉ እንጂ በፌዴራል ባለሥልጣን በስራ ላይ መዋል የለባቸውም፡፡ የክልሉ መንግስት ሥልጣንየበላይነት መኖር አለበት፡፡ ጣልቃ ገብነት መወገድ ይኖርበታል፡፡ ከለውጡ በፊት ኢህአድግ በክልሎች ጣልቃ መግባቱ ነበር የቄሮን የፋኖንና የኤጄቶዎችን አገር አቀፋዊ ንቅንቄ የወለደው፡፡ ያመደገም የለበትም፡፡ የፌዴራል ጣልቃ ገብነት በገደብ ይሁን፡፡ ሰዎች የተለያየ ምክኒያቶች ቢያቀርቡም በቅርቡ በፌዴራል መንግስት የተላለፈን ውሳኔ የትግራይ ክልል መንግስት አለመቀበሉየክልሉን ሥልጣን በግልጽ ያሳያል፡፡ ለዚህ ነው የትግራይን ክልል እንደ ሞዴል አድርጌ ያቀረብኩት፡፡

አዲስ አበባ የኦሮሚያ ነው ያልኩበት ምክኒያቶች ብዙ ናቸው፡፡ ቢጻፍ ከዳስ ካፒታል የሚበልጥ መጽሃፍ ይወጠዋል፡፡ በመጀመሪያ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ነው ሲባል በአዲስ አበባ የሚኖሩየሌሎች ብሄሮች ዜጎች በአዲስ አበባ መብት አይኖራቸውም ማለት አይደለም፡፡ ጸጉርን የሚያክል እንኳን መብታቸው መሸረፍ የለበትም፡፡ እንደ ማንኛውም ከተማዎች የከተማው ኗሪዎችመብታቸው የተጠበቀ መሆን አለበት፡፡ አንድ ሰው ኦሮሞ ስለሆነ ብቻ መብቱ ከሌሎች መብት የበለጠ መሆን የለበትም፡፡ የጸጉርን ስባሪ ታክል እንኳን፡፡ ታዲያ ሁሉም እኩል ከሆነ አዲስአበባ የኦሮሚያ አይደለችም ማለት ምን ትርጉም አለው?

በሌላ በኩል ብንመለከተው አዲስ አበባ የኦሮሚያ አይደለችም ከተባለ በኦሮሚያ ክልልና በኦሮሞ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ ያሳደራል፡፡

ቀደም ሲል ኢህአድግ አዲስ አበባን ከኦሮሚያ ክልል ያወጣው ትልቁ ምክኒያት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ደካማ እንዲሆን ነበር፡፡ ደካማ ከሆነ ተላላኪ ብቻ ይሆናል፡፡ አዲስ አበባ ከኦሮሚያክልል ከወጣች የአዲስ አበባ ኗሪ ኦሮሞዎች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ሊመረጡ አይችሉም፡፡ ግን የተማሩና ቢመረጡ ተላላኪ የማይሆኑ ናቸው፡፡ ተላላኪ ስል ምሳሌዎችን መናገር እችላለሁ፡፡ ስም ላለመጥራት ልቆጠብ ብዬ ነው እንጂ፡፡ የኢህአደግ ዋና አለማ ኦሮሞችን መከፋፈልና ማዳከም ነበር፡፡ እስከሻሸመኔ ድረስ የአዲስ አበባን ይዞታ ማስፋፋትና የኦሮሚያንክልልና ህዝብ ብዙ ቦታ ነበር መከፋፈል የፈለጉ፡፡ የቄሮዎችን እንቅስቃሴ የወለደው የማስተር ፕላኑ አዋጅ ኦሮሞዎችን ለመከፋፈል የተደረገ የመጀመሪያው እቅድ ነበር፡፡ ማስተር ፕላኑቢሳካላቸው ኖሮ ዛሬ ብዙ የኦሮሞ ክልሎችን እናይ ነበር፡፡ ማስተር ፕላኑንም ያጸደቁት እነዚያ ተላላኪ የነበሩ የክልሉ መንግስት አባላት ነበሩ፡፡ መላላክና ተልእኮውን ማስፈጸም ብቻ ነበርናስራቸው፡፡ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ብትጠቃለል ኖሮ ጠንካራና ኢህአድግን የሚቋቋም የኦሮሚያ መንግስት ይፈጠር ነበር፡፡ ለምሳሌ እንጂነር ታከለ ኡማ አዲስ አበባ ብዙ ጊዙበመኖሩ ነበር በግለሰብ አደባባይ ላይ ደረጃ አደባባይ ወጥቶ ማስተር ፕላኑን ያወገዘ፡፡ የሱ አይነቶቹ ከአዲስ አበባ ቢመረጡ ኖሮ ኢህአድግ ሃያ ሰባት አመት ይቅርና ሰባት አመት ባልገዛንነበር፡፡

 

ልድገመውና እኔ እምመኘው በመሬት አቀማመጥ ላይ የተመሰረተችና በዲሞክራሲአዊ ስርአት የምትተዳደር ኢትዮጵያን ማየት ነው፡፡ ክልል እስካለ ድረስ ግን አዲስ አበባ የኦሮሚያ መሆኗእውቅና ካላገኘች ለወደፊትም ጠንካራና የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም የሚጠብቅ መንግስት አይፈጠረም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ ኦሮሞ ነው ቤተመንግስቱንም ይዟል፡፡ ብዙ ለውጥንምአምጥቷል፡፡ ዲሞክራሳዊ ስርአትም እንዲሰፍን ከልቡ ተግቶ እንደሚሰራ አልጠራጠርም፡፡ ግን ይሳካለታል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ብዙ እንቅፋቶች አጋጥመታል ያጋጥሙታልም፡፡ ለምሳሌያህል የራያ ጉዳይ፤ የወልቃይት፤ የአዲስ አበባ የማንነት ጥያቄ ወዘተርፈ፡፡ የአዲስ አበባን የማንነት ጥያቄ ጀዋር ጀምሮታል፡፡ ጀዋር ጀመረ ማለት ደግሞ ቄሮ ቀጠለ ማለት፡፡ ምርጫውእየተቃረበ ሲሄድ የአዲስ አበባ የማንነት ጥያቄ እየተፋፋመ ይሄዳል፡፡ ለዚህ ጥያቄ አቢይ ምንድን ነው መልሱ? ሁሉንም የሚያረካ መልስ በተአምር አይመጣም፡፡ መልስ ከሌለውና በምርጫለማሸነፍ ከፈለገ ማሸነፍ የሚችለው ነጻ ባልሆነ ምርጫ ብቻ ነው፡፡ ዲሞክራሲ አፈር በላ ማለት ይሆናል።

በተለይም የአዲስ አበባ የማንነት ጥያቄ በኦሮሞ ህዝብ መልስ ካላገኘ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር የሚሆነው ከሰሜን ወይንም ከደቡብ ክልሎች የሚመጣ ይሆናል፡፡ ያም ማለትየአምናው መንግስት ወደ አራት ኪሎ ተመለሰ ማለት ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ትግሉን እንደገና ይጀምራል፡፡ የሌሎችም ህዝቦች ትግል እንደዚሁ፡፡

ስለአዲስ አበባ የማንነት ጥያቄን ለመረዳት የሌሎች አገሮችን ከተማዎች መመልከት አስፈላጊ ነው፡፡ ካናዳን ብንወስድ ኦተዋ የካናዳ ዋና ከተማ ነች፡፡ የኦንታርዮ ክፍለ ሃገርም ከተማ ናት።ምንም አይነት ስፔሻል ስታተስ የላትም፡፡ በኦተዋ ላይ ምንም አይነት የማንነት ጥያቄ አይነሳም፡፡ ለኦንታርዮ መንግስት ከኦተዋም ሰው ይመረጣል፡፡ ከጥዊት አመታት በፊት የኦንታርዮ ክፍለሃገር ፕሪሚዬር ከኦተዋ ከተማ ነበር፡፡ በኦሮሚያ ክልል ግን ማንም ከአዲስ አበባ መመረጥ አይችልም፡፡ ልክ እንደ ኦተዋ አዲስ አበባም የኢትዮጵያ ዋና ከተማ እንደሆነች የኦሮሚያ ክልልከተማም ብትሆን ምን ችግር ያመጣል? የኦሮሞን ህዝብ ለማዳከም ካልሆነ በስተቀር አዲስ አበባን ከኦሮሚያ መሃል መገንጠል ምን ጥቅም ለኗሪው ህዝብ ያመጣል?

ሌላው ምሳሌ ደግሞ ዋሺንግተን ዲሲ ነው፡፡ እንደሚታወቀው የተባበሩት የአሜሪካ መንግስታት ዋና ከተማ ቀደም ሲል ፊላዴልፊያ ነበር፡፡ በመሆኑም የደቡብ ዋና ከተማችን ራቀብን ስላሉ ዋና ከተማቸውን ወደ መሃል ማምጣት ስለነበረባቸውና ማንኛውም ስቴት የኔ ነው እንዳይል ዋሺንግተንን ከሚዋሰኑት ጥቂት ስቴቶች ቆርጠው ከተማዋን መሰረቷት፡፡ ዋሺንግቶን ትንሽመሬት ናት፡፡ ከቶሮንቶ ከተማ አትበልጥም በስፋት፡፡ ቢያሰፏት እንኳን የአንድ ስቴት መሬት ብቻ አይደለም የሚወሰደው፡፡ አዲስ አበባ እየሰፋ ሲሄድ የኦሮሞ ክልል መሬት ነው የሚቦጨቀው፡፡ተፈንቃዩ የኦሮሞ ህብረተሰብ ካሳ ይቅርና የአዲስ አበባ ኗሪነት መታወቂያ እንኳን አይሰጠውም፡፡ በግፍ ላይ ግፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሉታል ይህ ነው፡፡

አንድ የከተማ ኗሪ ግለሰብ በማንነቱ ጭቆና ካልደረሰበት የከተማውን የማንነት ጥያቄ አይጠይቅም፡፡፡ ለእለት ኑሮው ከመሯሯጥ በስተቀር፡፡ የአዲስ አበባን የማንነት ጥያቄ የሚጠይቁለስልጣን የሚሮጡ የፖለቲካ ሰዎችና ድርጅቶች ናቸው፡፡ እኛን የሚመስል ብቻ በከተማ ከኖረ በምርጫ እናሸንፋለን የሚሉ ብቻ ናቸው፡፡ የአስተሳሰብ ጉድለት ሆኖባቸው እንጂ መሳይ ሰውንብቻ አይደለም ሰው መሪውን የሚመርጠው፡፡ እኔ የተወለድኩበት ገጠር  መንገድ የለም፡፡ ጤና ጣቢያ የለም፡፡ እርግጠኛ ነኝ እነዚህን አሰራለሁ የሚል ሰው ከየትኛውም ብሄር ይወለድ ይህ ሰውእንደሚመረጥ፡፡  ኢትዮጵያውያን በሀሳብ የሚበልጥ እንጂ በዘር ብቻ ይመርጣሉ ቢሎ መገመት የኢትዮጵያን ህዝብ መናቅ ይሆናል። የበለጠ ሀሳብ ያለው ከሌለ ግን ሰው የሚቀርበውን ብቻ መምረጡ አይቀሬ ነው።

ሌላው እውቅና ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ አዲስ አበባ ፊንፊኔ ተብላ ብትጠራና ባለቤትነቱም እንዲታወቅለት ይፈልጋል፡፡ ራሴ ተጠቅሜ ሌላውን እጎዳለሁ ብሎ አያስብም፡፡ ፊንፊኔ የሚሉ የኦሮሞፖለቲከኞች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ነው፡፡ የሸዋ (ሳዋ) ኦሮሞን ከዳር እስከዳር ዞራችህ ብትጠይቁ  ሸገር እንጂ አዲስ አበባ አይሉም፡፡ የሚያውቋትም በዚያ ስም ብቻ ስለሆነ ነው፡፡እውቅና (recognition)በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ የካናዳ አገር የህንዶች እንደሆነ እውቅናው በህግ ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም የትም ቦታ ለየትኛውም አጀንዳ  ከሃያ ሰዎች በላይከተሰበሰቡ አጀንዳቸውን ከመጀመራቸው በፊት አገሪቱ የህንዶች እንደሆነች መግለጽ ህጋዊ ግዴታ አለባቸው፡፡  አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል እምብርት ናት ልብም ናት። ለኦሮሞ ህዝብ ገጠሩ ብቻ ይበቃል እምብርታቸውም ብትሆን ፊንፊኔ አትገባቸውም ማለት ለኦሮሞ ህዝብ የሚዋጥ አይደለም። ኦሮሚፋን የፌዴራል ቋንቋ ማድረግ ጎዶሎ አካልን ልብስ ማልበስ ብቻ ይሆናል ኦሮሚያ የአዲስ አበባ ባለቤትነት ሳይረጋገጥ። ያለአዲስ አበባ ኦሮሚያ ሙሉ አይደለችምና። በአዲስ አበባ የኦሮሞ ህዝብ መደራደር የለበትም። አዲስ አበባ ለድርድር የሚትቀርብ አይደለችም ለኦሮሚያ ክልል።  ስሟ አዲስ አበባ ሆኖ መቅረት አለበት እልላለሁ። አዲስ አበባ የአፍሪቃ መንግስታት ድርጅት መኖሪያ ቤት ስለሆነችና በዚያም ስለሚያውቋት ያለነሱ ፈቃድም ስም መቀየር አይቻልም።  በአጠቃላይ ኢትዮጵያከዚህ በታች ከተጠቀሱት ሶስት አይነት አገዛዝ አንዱ የሚከሰትባት አገር መሆኗ አይቀርም ወደድንም ጠላንም።

1፡) በመሬት አቀማመጥ ላይ የተመሰረተ ለአስተዳደር ለመገናኘትና ኢኮኖሚ እድገትን የሚረዳ ሰው በሰውነቱና በዜግነቱ የሚከበርበት፡ የሁሉም ባህልና ሃይናሞኖት የሚከበርበት፡ ቢያንስ ቢያንስ ኦሮምኛ አማርኛና ትግሪኛ የሃገሪቱ ብሄራዊ/አገራዊ የመገናኛ ቋንቋዎች የሚሆኑባትና ያለምንም ገደብ የዲሞክራሲ መብት የሰፈነባትና ህዝቦቿም አገራዊ ግዴታቸውን አውቀው በእኩልነት የሚኖሩባት ሆና የሚትገነባ ኢትዮጵያ

2፡) በብሄር ተኮር ላይ የተመሰረተ ክልል፡ ሁሉም ክልሎች ያለጣልቃ ገብነት የራሳቸውን ክልላዊ ህግ እያስከበሩና በአገሪቱም ህጎች ላይ የመወሰን ድምጽ ተሰጥቷቸው በእኩልነት የሚኖርባት ሆና የተገነባች ኢትዮጵያ። ገና ጅምር ላይ ያለ ቢሆንም የትግራይ ብሄራዊ ክልል እንደሞዴል ቢወሰድና ያን ሞዴል ማጠናከር አስፈላጊም ይሆናል።

 

3፡) አሁን ኢትዮጵያ ባለችበት ሁኔታ መቀጠል። በዚህ ከቀጠለች የህዝቦች መፈናቀል ይቀጥላል፡ የማንነት ጥያቄ ይበራከታል፡ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ብዙ አደጋ እየደረሰ ይሄዳል፡ አምባገነናዊ መንግስት ይመሰረታል፡ ጊዜአዊ የወታደር አስተዳደር በሚል ዘለአለማዊ ወታደራዊ አገዛዝ ስሩን ይሰዳል። ወደነበርንበት መመለስ ማለት ነው።

ምርጫዬ አንደኛው ሲሆን ሁለተኛውንም አልቃወምም። አበራና ካሳ፡ ቶሎሳ ወዬሳ እንዲሁም ቀልበሳ የናንተሳ?

 

 Demissie Adugna

dadugna@yahoo.com

 

Back to Front Page