Back to Front Page


Share This Article!
Share
አላወቅነውም እንጅ

አላወቅነውም እንጅ

አላምነው ገ/ማርያም 3-5-19

ልዩና ብርቅዬ አዝርዕትና እንስሳት በኢትዮጵያ መገኘቱ ምሁር ሊጠኑ ሰውም ሊያስጠና ነውና ኢትዮጵያን ት/ቤት ኢትዮጵያውያንን አሰተማሪ ያደርጋቸዋል። በቅዱስ መጻሕፍት መጠቀሷና ሊግ ኦፍ ኔሽን (League of Nation) ከመሰረቱ ሃገሮች አንዷ ሆና የአፍሪካ ማዕከል መሆኗም ተደማጭነቷ። ይህልዩ ምልክትና ኩራት ብቻ ሳይሆን ፀጋውን የማስተዋወቅ ግዴታና ሃላፊነት እንጅ። ማዶ ለማዶ የቃላት ድንጋይ ከመወራወርና ጥላቻ መርዝ ከመረጨት ልዩነትን በውይይት መፍታት እንጅ። በቀደምቶች ሙያና ጀግንነት ከመኩራራት እራስን አሳውቆ ትውልድ ሰወቅ እንጅ። በትንሽ በትልቁ መፋተግ ለአንድነትና ፍቅር መቆም እንጅ።

 

Videos From Around The World

ታዲያ ይህን ማድረግ ለምን ተሳነን ብዬ ራሴን ስጠይቅ የመንግሥታት መገለባበጥ በፈጠረው ዳዳ ሰር የገባው የጥፋት ሃይ ተግባር ሆኖ አገኘሁት። አዎ! የሃገራችንን የመንግሥት መገለባበጥ (ለውጥ) በቅርብ ተከታትያለሁ። መገለባበጥ ስል ደራሽ ውሃ ድንገት ደርሶ ሁሉንም እያገላበጠ ወስዶ ባዶ እንደሚያስቀር የመንግስታት መገለባበጥም በድንገት ተከስቶ ልማትና ግንባታ አጥፍቶ ለድህነት፤ ርሃብ፤ ልመናና ስደት አዟሪት ዳርጎናልመዘዙም የመጣው ሁሉ ሥልጣን መያዝ ከቻለ እኛስ በሚል ሁሉም ፖለቲካኛ ማድረጉ። ተፈናቃዩ፤ ድርቁ፤ አየር ለውጡ ፖለቲካ ትርምሱ የጊዜ ጉዳይ እንጀ አዟሪቱ ነገም አለእነዚህ ችግሮች ደግሞ በሁሉም ሃገር ይደርሳሉ ግን ስለሚዘጋጁ አይለምኑምአላወቅነውም እንጅ እኛም እኮ በድርቅ ለሚጎዱ እንስሳት የክረምት ሣር በደቦ አጭደን በመከመር እንታደጋቸው የሚል ሪፖርት አለን። ለድሃም መንግሥት ጎተራ ይስራ ገበሬው በመህር አንዳንድ ቁና እህል አከማችቶ ሲችግር ተከፋፍሎ አለያም በወቅቱ እዬተሸጠ በአዲስና ተጨማሪ እህል እዬተተካ የምግብ ዋስትና ይረጋገጥ ድህነትም ይቀረፍ የሚልም እንደዚሁአጠፉት እንጅ ሪፖር በኢህአዴግ ጊዜ ተተግብሯልአሁን ግን መዘጋጀቱ ቢቀር አንወያይምም።

 

መለስ ብዬ ሳዬው በመሣፍንቱ ስርዓት ራስ፤ ፊታውራሪ፤ ቀኛዝማች፤ ግራዝማች በሚል ተሿሹሞ ከእሱ ሌላ ሃላፊ፤ የበላይ፤ ባለሙያ የለም። በፊለፊት ባያደናቀፍ ሳው ያሳምጻል፤ አሉባልታ ይነዛል፤ በወሬና ውሸት ያሸብራል። የውጩን እንጀ ስለሃገ አልተማረም በሚል የምሁር ሹም አይቀበልም። ግድ ከሆነ ከመሣፍንቱ ያነሳ መጠሪያ ይሰጠዋል ወይንም ምክትል ይሆናል። ግን ስርአቱ አካባቢውን ባህልና ወግ ስለሚጠብቅ ይደመጣልይድገፋልም። እናም በወቅቱ የጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ/ገዥ የወሎ ጠቅላይ ግዛት እንደራሴ፤ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እንደራሴ፤ የሐረር ጠቅላይ ግዛት እንደራሴ ይባላል። ምክንያቱም ጃንሆይ እንደእኔ አድርጋችሁ ተቀበሉት ማለታቸው ነበርተቀብለውታልም። ያለበለዚያ አሰራሩን አዘምኖ ለልማትና እድገት ቀርቶ ለአመራርም አሰቸጋሪ ነበር። አሁን ግን አመራርና አስተዳደሩን በህዝብ ባህል፤ ወግና ፍላጎት ሳይሆን በስመ ምሁር አድርገን ተተራምሰን ሃገርና ህዝብ ማተራመሱን ተያይዘነዋል

የመሣፍንቱ ስርአት ዛሬ መጠሪያውን ኢንጅነር፤ ዶክተር፤ ፕሮፌሰር ብሎ አዋቂም፤ አመራርም፤ ሃላፊና ፖለቲከኝም እኔ ብቻ ያላል እንጅ አንድም የህብረተሰቡን ባህል፤ ችሎታና ፍላጎት በሙያው አያካትትም አለያም እንደ ሌላው ዓለም ባለሙያ በዕውቀትና ችሎታው በዓለም ታውቆ ሃገር አያሳውቅምበዚህም አይቆጭ። ለምሳሌ በስፖርቱ ብዙ አፍሪካውያን ኳስ ጨዋታ ሳያውቁ የታላቁ ሰው ይድነቃቸው ተሰማ ልጆች አውሮፓ ተጫውተው አኩርተውናል። ዛሬ ግን አፍሪካውያን ኳስ ተጫውተው በሚሊዮን እየቆጠሩ ወገን ይረዳሉ። ጀግናው አበበ ቢቂላ በሩጫ ለጥቁር ወጣት ፈር ቀዶ አኩርቶናል። የአምስትና አሥር ሺህ ሜትር ጀግኖቻችን በምቾት የሰለጠነን ሯጭ ሁሉ አስከትለው ገብተዋል። አሁን ግን ወሬና ፖለቲካ ተወጥረን ሌሎች እንደንቃለን። በዕውቀትና ሙያ እንደ ቡና ውሃ ማሽቆልቆላችንና የዓለም መሣቂያ መሆናችንንም አላወቅነውከልማትና ዕድገት ይልቅ ማጣፋት ዕውቀት፤ ሙያና ልምድ ስለማይጠይቅ ተመችቶን መጠፋፋቱን ተያይዘነዋል!

በመንግሥት ግልብብጦሽም የንጉሡ አገዛዝ ከውስጥ ተቦርቡሮ ደርግ ሥልጣን ሲይዝ ሥራና ሠራተኛ ተግዳሮትና የሥልጣን ክፍፍል ሳያውቅና ሳይዘጋጅ እንደ ጎርፍ ስለመጣ በጥፋት ሃይሎች እጅ ወደቆ ወደ ጥፋት መርተውት ባለዲግሪውን ሁሉ ከሚኒስቴር መ/ቤ እያፈናቀለ የአውራጃ አስተዳዳሪ ሲሾም ነባሩን አስኩርፎ ብዙ ጠላት ፈጠረ። ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያምን ያለሕግ ዕውቀትና ሙያ ከመምህርነት መርማሪ ኮሚሽንነት ክቧቸው ስም የሚያስጠራ ተግባር ሳያከናውኑ ሊያልፉ ነው። ከድጡ ወደማጡ እንዲሉ ይባስ ብሎ መኮንኖችን የለውጥ ሐዋርያ ብሎ አሰተዳዳሪ ሲያደርግ የነበረውም ፈረሰ አዲሱም ተፈረካከሰ። ያለ ጥናት ግብርና ሚ/ርን አደራጃለሁ ብሎ በብዙ መቶ የሚቆጠር ሠራተኛ ለዓመት ያለሥራ ደመወዝ ከፍሎ ሃገር አክስሯልየጥፋት ሃይሉም ታዋቂና ባለሙያ እንዲወነጅል አድርጎታል። ለምሳሌ እውቁ ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ ሰው በራሃብ እያለቀ የነብር ግልገል ያሳድጋል በሚል አሉባልታ ተወንጅሏል። ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌን እመጫት በሸማ ሕጻን አቅፋ የሳሉትን የባህል ቅርስ የዘውዱን አገዛዝ አሞገሰ በሚል ምቀኝነት ነበር። አሁንም ሙያተኞች ለኢህአዴግ ሠራችሁ ተብለው እንዲያስተባብሉ ተደርጓልቀደም ሲል ሆዳሞች ይሏቸውም ነበር። ቅናትና ምቀኝነት እንጅ ጠያቂ ማን ነው? ተጠያቂስ? ሳይከካ ተቦካ እንዲሉ አዲሱን አስተዳደርም ገና ከጅምሩ ለሰላምና ለወጣቱ ሥራ ፈጠራ የተጠራበትን ሃላፊነትና ግዴታ ሳይወጣ ተቋማት ማሻሻል በሚል ስርአቱን እንዲያመሰቃቅለው አድርገውታል

በዚህም ያለው አሰራ ሳይጠናና ፖለቲካውና ፖለቲከኛው ሳይለይ ተቋማት ማሻሻል በሚል ሹም ሽርና የምርጫ ቦርድ ለውጥ ተጧጡፏል። አዝማሪው፤ ምሁሩ፤ ጋዜጠኛና ተዋናዩ ሁሉ ፖለቲከኛ በሆነባት ሃገር ምላሽ አይሆንም። ግን ፖለቲከው አይደለም ችግሩ የሌላው ዓለም ባለሙያ እኛ ሲረዳ ያለመታፈሩ እንጅ አንዲት የሰሜን ወጣት ፖለቲካ ትርምሱ ገርሟትፖለቲካ አይበላ ያለችውን የምዕራቡ ዓለም ጋዜጠኞች የቴሌቪዥን ፕሮግራም ሠርተውበታል። ዘፋኞቻችን በዬመንደሩ ሲፖተልኩ ቦብ ጎልዶፍና መሰሎቹ ረድተውናል። ለተሻለ ኑሮ ስምና እድሜ ለውጦ ፈረንጅ ሃገር እየኖረ እራሱን የህዝብ ተወካይ ያደረገ ፖለቲከኛም በየማድቤቱ ያቅራራል። አሁንም በዋናነት ሃገር ቤት ውስጥ የሚያተራምሰው እሱ ነው። በቅርቡ ሃገር ቤት ሲግተለተል ለዓለም ግልጽ ያደረገው የፖለቲካ ስብስብ እንጀ የህክምና ዶ/ር፤ የእርባታና ልማት ባለሙያ ወይም ኢንቬስተር አይደለም። እናም ችግሩ ምርጫ ቦርድ፤ እርስ በርስ መሿሿም፤ ፖለቲከኛ ወይም ዳር ላይ ቆሞ የሚተች ሳይሆን ፖለቲካ የሚያዘምን፤ ህብረተሰብን የሕይወቱ ባለቤት የሚያደርግ፤ ድህነትን የሚዋጋ፤ ለዕድገትና ብልጽግና የቆመ ተቋም እንጅ። በሃገራችን ሁሉም ነገር ፖለቲካ ሆኖ ምህዳሩ ጠበበ እየተባለም ይቀለዳል። ምህዳሩ ከጠበበ ሰው በሙያው የማይሰማራው? ሰው በፖለቲካ እንጅ በሙያው የሚያሠራ ወኔ የለውም ልበል?

ይልቅንስ የሌሎችን እንደ ገደለል ማሚቶ ከማስተጋባት ተደራጅቶ ለማደራጀት፤ ሕዝብ አውቆ ለመታዎቅ፤ ባለፈ ከመወነጃጀል ችግርን አጥንቶና አሰጠንቶ ፖለቲካውን ያጎለብቷል። ዲሞክራሲ እንደ ጸበል ወይንም ማደበሪያ ሕዝብ ላይ የሚበተን አይደለምና ዲሞክራሲ እናመጣለን የሚለውን ማላዘኛ ትታችሁ የሕዝብን ግንዛቤ አበልጽጉ። ሕዝብን እወቁት እሱም ይወቃችሁ እንጀ እናውቅልሃለንን እኪሳችሁ አሰቀምጡት። ተቃዋሚዎችም ፖለቲከኛ ሆናችሁ የተሻለ አመራር ለማምጣት ከሆን መንግሥትን የሚመጥን ተጠሪ ገንቡ። ለምሳሌ መንግሥት ለተለያዬ አመራር 20 ሚኒስቴሮች አሉት። እናንተም በዚህ ልክ ከሠራተኛ፤ ባለሙያ፤ ምሁሩ፤ አርሶና አርብቶ አደር መልምላችሁ ተጠሪ ሰይሙ። ተጠሪውም ድጋፍ ሰጭ ኮሚቴና ንኡስ ኮሚቴ ሰይሞ ሥራና ሃላፊነት ቢያከፋፍል ስለሥራ ይማሯል፤ ተግዳሮት ይለዩያል፤ የተበላሽ አሰራር ያሻሽሏል፤ የመንግስት ጉድለት ይጠቁሟል፤ ችሎታን ንጸባርቋል። ከሁሉም በላይ ለ60 ተቃዋሚ ተብዬ 20 የሚኒስቴር ተጠሪ ለማግኘት 1200 መመልመል ስለማይችል የፓርቲ ቁጥሩ ቀንሶ ጥራቱም ይሻሻላል። አንዱ ተጠሪ ሁለት ሚኒስቴር እንኳን ቢወክል 600 ተጠሪ ያስፈልጋል። ይህም ኮሚሽኖችን፤ ክልል አሰተዳደሮችንና ተዋረድ አመራር ሳይጨምር እንጅ ለሃገሪቱ ተቋማት ሁሉ ተጠሪ ማግኘት አይቻልም ብቻ አይደለም አይሞከርምም። ተጠሪና ኮሚቴም እኮ የራን ዕውቀት፤ ልምድ፤ መለስተኛ ድጋፍም ያዞ ይመጣልበምርጫ ማግሥትም ሚኒስቴርና አስተዳደር ው። ሌላው ፓርቲዎች የአመራር ተቋም እንኳን በአግባቡ ሳይኖራቸው ግንባር ይፍጠሩ እየተባለ ይቀለዳል። ካልተካካድን የሥራ ከፍፍልና የበላይ የበታች ምደባ ባህል የለንምና ጨራረሷታ እንጅ ምንም ተቋም አይገነቧትም። መንግሥትም ድርድር የሚለውን ቧልትና መመሪያ ከተቃዋሚ ተብዬው ስብስብ ከመቀበል ይልቅ ባለሙያ አሰባስቦ ነገ በምርጫ አሸንፌ መቶ ሚሊዮን ሕዝብ እመራለሁ የሚል አካል (ስብስብ) ሊኖረው የሚገባ ደጋፊ/አባል ዝርዝር ከነፊርማው፤ የሚሰበስበው የቁሳቁስና የገንዘብ ልክ፤ የሚኒስቴር ተጠሪ፤ የሚሸፍነውን አካባቢ በአጭር፤ መካከለኛን ረዥም ጊዜ ለይቶና አሰጠንቶ እንዲያቀርብ የሚያደርግ መመሪያ ያስነድፍ። በዚህም የፖለቲከኛው ቁጥር ቀንሶ ጥራትም ይኖረዋል፤ ፖለቲካውም የተግባር እንጅ የወሬን ጎሣ አይሆንም።

ሌላው ምርጫው ከሚቀጥለው ዓመት የማይተላለፍ ከሆነ ተቃዋሚዎች አልተደራጃችሁምና አንድም በአጥፊ እጅ ወድቃችሁ ሁሉንም ታጠፋላችሁ አለያም ትርምስና ጫጫታ ይሆናልና ለሥልጣን ብቻ አትወዳደሩ። ለተወሰነ መቀመጫ ሆኖ በሚቀጥለው ጊዜ መቀመጫ ለመጨመር፤ ለመጠናከርና መረብ ለመዘርጋት አቅዳችሁ ተወዳደሩ። ከምራችሁ ከሆነ ተቋ ማዘመንና ማጎልበትም ፖለቲካ ስለሆነ ያለዝግጅት ቀርባችሁ ብታጉመተምቱ ተደጋግሞ እንዳዬነው የራሳችሁን ልምድ ብቻ ሳይሆን የወደፊቱን ፖለቲከኛ ዕድልም ትሰብራላችሁ

መንግሥትም ምረጫው በሚቀጥለው ዓመት ሆኖ ሥር ነቀል ለውጡ ትርጉም የለውምና አንድም በምርጫ ያተኩር አለያም ምርጫውን ያራዝም። ምክንያቱም የተሿሚው ልምድና ብቃት ራሱ የሚያደርሰው ጥፋት ሳያንስ በአዲስ ተመራጭ መተካት ተጨማሪ ጥፋት ነውና። ሹም ሽሩም በሕዝብ ጥያቄ ሳይሆን በትውውቅ ስለሆነ ትብብር ይነፍጋልና ችግር አለበት። ሹመቱም ያለወካይ ተወካይ በመመራረጥ ነውና ከክልል፤ ዞኑ፤ ወረዳ፤ አርሶና አርብቶ አደሩ አያቀራርባችሁም። ያለፉት ስርዓቶች የሚወቀሱት እኮ ሹመት በሕዝብ ሳይሆን በባለሥልጣን ሆኖ ነው። አሁን ያለነው ደግሞ የሕዝብ አዎንታና ግብአት ወሳኝ በሆነበት 21ኛው ክፍለ ዘመን 2011 ዓ.ም. ነው። ስትሙም ህብረተሰቡን ሳታውቁት፤ ኑሮውን ሳትኖሩ፤ ፍልጎቱን ሳትጠይቁና ተወካዩን እንኳን ሳታካትቱ ነውና ሥልጣን እንጀ ሕዝባዊነት ይጎላችኋል። እዚህ ላይ የግድ ሕዝብን ሁኑ ባይባልም ባህሉን ኑሮና ፍላጎቱን የተገነዘበ አካል በመካከላችሁ ይኑር ነው። በጠረንጴዛ ዙሪያ ስትታዩም 80% የሃገሪቱን ህብረተሰብ ክፍል ያቀፈውን አርሶና አርብቶ አደር የሚመስል ቀርቶ የሚቀራረብም የለባችሁምና እንዴት እንደምትመሩት ያጠያይቃልበመሆኑም የሃገሪቱ መሠረት በሆነው ልማት ስትወያዩም ይሁን ባለሙያ ስታወያዩ አትታዩም። ዛሬ እኮ እኛ እራሳችንን ካልመገብን እንደ ዱሮው እርዳታ የለምና የፖሊታከውን ተጋባር ሲሶውን ለልማት የሚያውል አካልና አሰራር ቢኖራችሁ? ይህም ሥራ ፈጣሪና ልማታዊ ለሆነ ሕዝብ አይበዛበትም ቢያንሰው እንጅ!

ኢትዮጵያዊ ሥራ ፈጣሪ ነው ሲባልም፤ የደጋ ሴት ቤት ካፈራው ቆንጥራ ፈጭታ ቆላ ወስዳ የቆላ ሴት ወተት ገፍታ ባወጣችው ቅቤ ለውጣና ከተማ ሸጣ ለዓይኗ ኩል፤ ለቅቤዋ ቁኒ፤ ለእጅና እግሯ ጉሽርጥና እንሶስላ ገዝታ ታጌጣለች። በሌላ ጊዜ በገንዘቡ ዶሮ ገዝታ እያረባች እንቁላልና ሥጋ ሸጣ ኑሮዋን ትደጉማለች። ለዚህ ነበር ያኔ አንድ ዶሮ ሽልንግ ከስሙኒ (75 ሣንቲም) እንቁላል አሥሩ በአንድ ብር፤ በአምስት ሣንቲም የአህያ ጆሮ የሚያክል ፓስቲኒ ይቀረደድና በአንድ ብር ከሽልነግ (1.50) ቁርጥ ይጎመድ የነበረው። ያኔ እንደዛሬው ሰው ለሥራ እንጅ ለወሬ ጊዜ ስላልነበረው ሥራና ገቢን እንዲህ ፈጥሯል። አባዎራም መህሩን ሰብስቦ ቀደም ሲል በበቅሎ ከዚያ በጭነት መኪና በኋላም በአውቶቡስ ከፋ፤ ሲዳሞና ሐረር ተጉዞ ጥሬ ገንዘብ በእጁ ለሌለው ቡና አምራች ሲለቅም ከአራት አንድ ይከፈላል። አራት እግር ወይም አራት ጆንያ ቡና ለቅሞ አንድ እግር ወይም አንድ ጆንያ ቡና ይወስዳል። ያንን ለፈልፋይ ኩባንያ ሸጦ ገንዘቡን በኪሱ ቡናውን በጆንያ ይዞ ለበልግ እርሻ ይመለሳል። ልጅ የሚድረም ጥሎሹን እግረ መንገዱን ከከተማ ሲገዛ ጊዜና ወጭ ይቆጥባል። አንዳንዱ ቡና አመራች መንፈሱ የወደደውን ሰው ቤተሰብህን አምጣና እዚህ ኑር ብሎ መሬት ቆርጦ ሰጥቶ ካኖሯቸው ብዙዎች ቡና ላኪ፤ ባለሱቅና ባለቡና ቤት በመሆን የልጅ ልጅ አይተው ኖረዋል። ሌላው ገበሬ መህሩን ሰብስቦ ግማሹ ወንጅና መተሃራ ሄዶ ሸንኮር አገዳ ቆረጦና ክፍያውን ቋጥሮ ለመህር ይመለሳል። ሌላው አሳይታ፤ ዱፕቲ፤ ገዋኔ፤ አሚባራና አምባሽ ጥጥ ይለቅማል። ያኔ አንድ ድርጅት እስከ 5000 (አምስት ሺህ) ሠራተኛ ይቀጥራል። ክፍያውም ሠራተኛም እንዳይጎዳ ድርጅትም እንዳይከስር ለመጀመሪያው ዙር ለቀማ ለኪሎ 10 ሣንቲም፤ ሁለተኛው ዙር ለኪሎ 25 ሣንቲም ለሶስተኛው ዙር 50 ሣንቲም ነበር። ምክንያቱም በመጀመሪያ ዙር ዛፉ አልፎ አልፎ እንጅ በቁመቱ ልክ ስለሚያፈራ ከአንድ ዛፍ ከሶስት ኪሎ በላይ ሲለቅም ከአሥር ዛፍ 30 ኪሎ ለቅሞ ብር 3 በቀን ያገኛል። በሁለተኛው ዙር ዘግይቶ ከሚፈነዳው ዛፍ በቀን ከ 10 ኪሎ በላይ ስለማይለቅም ክፍያው ይጨምራል። በሶስተኛው ዙር መቃረም (ማጣራት) ሲሆን በቀን ከ 6 ኪሎ በላይ ስለማይለቅም ክፍያው እንደገና ይጨምራል።

የዛሬን አያድረገውና የልማቱ መስፋፋትና የክፍያው ፍህታዊነት የወቅቱን ኢትዮጵያውያን የላቀ ችሎታ ከማሳዬቱ በላይ በወቅቱ ሃገራችን የአፍሪካ ዳቦ ቅርጫት ተብላ የአለምን ትኩረት በመሳቧ ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉት ከፍተኛ የልማት፤ ጥናትን ምርምር ተቋማት ኢትዮጵያ ውስጥ ነበሩ፡ -

ሀ) Chilalo Agricultural Development Unit (CADU) 1967 በስዊድን መንግሥት የተቋቋመ የእርሻ ምርምርና ማስፋፊያ ድርጅት በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር አርሶ አደር ሕይዎት ለውጦ አሁን ምልክቱም ጠፍቷል። የተገኘው ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ሙያና ልምድም አልተጠቀምንበትም።

ለ) Wolamo Agricultural Development Unit (WADU) 1969 የአለም ባንክ ከ $ 35 ሚሊዮን ዶላርና 7 የምዕራቡ ዓለም ባለሙያ ለወላይታ አውራጃ መድቧል። ምክንያቱም መሠረተ ልማቱ ተዘርግቶ ስለነበር በማስቀጠል ኢትዮጵያን ለሶስተኛው ዓለም ሃገር ሞዴልና ት/ቤት ለማድረግ ነበር። ደርግ ሲገባ አሁን በሃገራችን እንደሚታዬው ጥፋት የአውራጃው ወጣት አወደመው። ከዚያም በ1984 በረዶና ነፋስ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ የአዋራጃውን ሰብል አጥፍቶት ቦብ ጎልዶፍ አረንጓዴው ርሃብ green hunger በሚል እርዳታ ለምኖበታል። የምትለመን ሃገር ስትለምን ሌላ ምን ይባላል? አሁንስ ያለፈው ጥፋት ቢደገም እንደነቃለን ወይንስ ካለፈው ተምረን ለችግራችን መፍትሄ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንሰራለን?

ሐ) International livestock center for Africa (ILCA) July 1974 የኢትዮጵያን ከብት ሃብት አጥንቶ ለማሳደግና ለአፍሪካም መማሪያ ለማድረግ ሲቋቋም ማዕከሉ በበግና እንስሳት ሃብታቸው በሚታዎቁት ደብረ ብርሃን፤ ባቲና ወልድያ ነበር። ጥፋት እንጀ ልማት ስለማይሆንልን ተቋሙ በ1994 ከ International Laboratory for Research on Animal Diseases ጋር ተዋህዶ ናይሮቢ ተዛወረ። አያስቆጭም?

ባናውቀወ እንጀ በዚህ ሥራ ፈጣሪ በሆነ ህዝብና የዓለም አቀፍ ተቋማት ማዕከል በሆነች ሃገርም ተለምኗል። ስረዓቱም ተወግዟል። ታዲያ የኢህአዴግ ግንባታ ቢጠፋና እሱም ቢወገዝ ምን ይደንቃል? የአሁኖቹም ባለሥልጣናት አላወቁትም እንጅ የሚገሰግሱት ወደዚያው ነውና ስህተ እንዳቢያንስ ብንወያይ? ሞኝ ሴት ባሏን ጎዳሁ ብላ ብልቷን በስለት ወጋች እንዲሉ ጥፋት የሚጎዳው አጥፊውን ሳይሆን ለልማቱ ዕድገትና መስፋፋት መስዋዕትነት የከፈለውንና ደጋፊውን ነውና ከዳር ቆሞ ከመመልከትና የነቀፋ ስለት ከመሳል እጅ ለእጅ ተያይዘንና ካለፉት ጥፋቶች ትምህርት ወስደን ለማስተካከል መረባረቡ እንደሚበጀን ልንገነዘብ ግድ ይላል!

 

ኢትዮጵያዊ በተፈጥሮው አስተማሪና ሥራ ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን ኢንቬስተርም በመሆኑ በንጉሡ ጊዜ ባለሃብቶች በመገናኛው ዘርፍ ወሎ ፈረስ፤ ማሞ ካቻ፤ ቦጋለ ብሩ፤ መኮንን ነጋሽ፤ ሐጂ አብዱ፤ ጎሽ፤ በሚል መጠሪያ አውቶቡሶች ከውጨ በማስገባት በድጎማ ከሚንቀሳቀሰው አንበሳ አውቶቡስ ጋር ተፎካክረው ሕዝብ አገልግለዋል። ግን የጥፋት ሃይሎች ስለባ ሆነው ዛሬ ምልክታቸው የለም። አሁንም የሚጋዩት አውቶቡሶችና የጭነት ማጓጓዧዎች በውጭ ምንዛሬ የገቡ የግለሰብ ናቸው። አላወቅነውም እንጅ ከለውጥ ጋር ተያይዞ የሚጠፋው የሕዝብና ሃገር ንብረት ካለፈው ተምሮ ያለማረም መሆኑን ከዚህ ሊማሩ ግድ ይላል!

 

ኢህአዴግም እንደ ደራሽ ውሃ አልሚና አጥፊን ሳያጠናና ሳያውቅ ስለመጣ እንደ አሸን ከፈሉና ንጉሡንና ደርግን ከቦርቦሩ የጥፋት ሃይሎች እጅ ላይ ወድቆ የህዝብን ራስን በራስ የማስተዳደር ዋስትና የሆነውን ፌደራሊዝምን ወደጎሣና መሣፍንታዊ አሉባልታ ለውጠው ለጥፋት ተጠቀሙበት። ቢሆንም በንጉሡ ጊዜ ኢትዮጵያ በኮሪያና ኮንጎ ሠላም ጥብቃ የሠራችው ታሪክ በደርግ ቢጠፋም ኢህአዴግ በሩዋንዳ፤ ዳርፉር፤ ሶማሊያና ደ/ሱዳን በመድገም የኢትዮጵያን ለዓለም ሠላም ዘም መቆም እንዳረጋገጠ መካድ አይቻልም። እንደ ንጉሡ ጊዜ ልማትና ግንባታ ኢህአዴግም በኤሌትሪክ መስመር ዝርጋታ ከራሳችን አልፈን ለጎረቤት ለመሸጥ መሠረት መጣሉም እንደዚሁ። በመንገድና ባቡር ዝርጋታም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በማረጋገጥ ላይ እያለ በጠ/ሚኒስቴር ሃይለማርያም ሲተካ እሱም በጥፋት ሃይሎች እጅ በመውደቁ የሃገርን ሥራ ፈጣሪነት፤ ልምድና ሙያ ማበረታታት ይልቅ በባለ ዲግሪ እንዲያንበሸብሸው አድርገውት ሲያሸበርክ ንጉሡን፤ ደርግንና ኢህአዴግን ይገዘግዝ የነበረው የጥፋት ሃይል እንደገና በዶ/አቢይ እንዲተካ አደረገው። እሱም እንደ ሌሎቹ ሳይደራጅ፤ ሥራና አሰሪን ሳይለይና የህብረተሰቡን ወግና ባህል ሳያገናዝብ ስለመጣ በጥፋት ሃይሎችና የዘመኑ መሳፍንቶች (ባለዲግሪ ታፔላ) እጅ ላይ ወድቆ ሁሉንም ያገለባብጠው ይዟል።

 

የለውጡ አመራሮች ሁሉ ሥልጣን ሲይዙ ተቋማትና መመሪያ ላይ ይዘምታሉ። ለምሳሌ ደርግ ርዳታ ስተባበሪያና ቋቋሚያ ኮሚሽንን (እማማኮ) ሲመሠርት የሃገርን ሙያ፤ ዕውቀትና አቅም አሰተባብሮ አደጋን እንዲቋቋም ነበር። የልማት ድርጅት ሲያደርው ሁሉም ተበላሽ። ኢህአዴግ ደጋ ከላከልና ግጁነት ሚሽን (አመዝኮ) ሲለው ሃላፊዎቹ እራሳቸውን የልማት ተቆጣጣሪ አድርገው ሾመው ልማት አጠፉበት። አሁን ደግሞ የሔራዊ ደጋ ጋት መራር ሚሽን (ብአስአኮ) ተብሎ በሚሊዮን የሚገመት አርሶ፤ አርብቶና ነግዶ የሚኖር ህብረተሰብ ተፈናቅሎ በእርዳት የመንግሥት ካዝና ያራቁታል እንጀ ድጋፍ አያስተባበረም። መፈክራቸው ደግሞ ለውጡን ነቅተን እንጠብቅ፤ ካዝናው ባዶ ነው፤ ጭቆና ተወገደ፤ የተበዳይ እንባ ደረቀ፤ ፍጹማዊ ነን ይላሉ። ግንባታና የህብረተሰብ እድገት ደረጃ ስለሚያጣጥሉ ሁሉም ይጠፋና ጊዜ ሲደርስ እነሱንም ይዞ ይጠፋል። ህብረተሰቡን ያውቁለታል እንጅ ችሎታውን፤ አቅሙንና ፍላጎቱን ጠይቀው የሕይዎቱ ባለቤት አያደርጉትም። እናቴ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፤ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ ተብሏልና ባለሙያ፤ ሠራተኛና ምሁር መወንጀልንም መመሪያ ያደርጋሉ እንጅ ነገ በእኔ ያውቁም። በአንፃሩ የጥፋት ሃይሎች ውጥረትና ትርምስ ስርዓቱን ይገረስሰዋል በሚል የቂል ዕምነት ይደሰታሉ። ሕዝብ ኖሮው ሲተጓጎል እጅ ለእጅ ተያይዞ እንደመርዳት ከዳር ቆመው የሚረዳውንም ያከላክላሉ። ግን መቼና እንዴት ነው ይህ በለውጥ ስም የሚመጣ የጥፋት አዟሪት በቃን የምንለው?

እናም አሁን ያለንበት ጊዜና ሁኔታ ኢትዮጵያውያን መለስ ብለን ለምንድ ነው የሰው ልጅ መገኛ የሆነች፤ የዳቦ ቅርጫት የተባለች ሃገር በዓለም አቀፍ መድረክ የሚታዎቅ ባለሙያ የሌላት ብለን ልንጠይቅና መልስ ልናገኝ ይገባል። ምክንያቱም ሌላው አፍሪካዊ በሚኖርበት ሃገር በሙዚቃ፤ ስፖርት፤ ፊልም፤ ፖለቲካ፤ እራሱን አሳውቆ ሃገርና አህጉሩን ሲያስጠራ እኛ የለንበትም። በዚህም አናፍርም። እራስን ለማንቆለጳጰሡ ግን ተወዳዳሪ የለንም። ብናውቀው ይህንንም እንደ በጎ ነገር ለልጆችና ልጅ ልጆቻችን እያዎረስን ነው። በዚህ መቀጠሉም እንደ ሃገርና ሕዝብ ለመኖራችን አደጋ ነው

በእርግጥ በርካታ ኢትዮጵያውያን በትምህርት፤ ልማት፤ ወጣቶች ድጋፍ፤ ጤና፤ መገናኛ ብዙሃን፤ ወዘተ ወገን ለመርዳት ሞክረዋል። አንድ ወቅት ስለሽ ደምሴ (ጋሼ አበራ ሞላ) በአለቤ ሾው የእሁድ ፕሮግራም በድህነታችን አልቅሷል። በዚያው ሰሞን አዲስ አበባ ፒያሳ ጎማ አቃጥለው እዬሞቁ አላፊ አግዳሚውን ሳንቲም የሚጠይቁ ወጣቶችን አሰባስቦ መንገድ እንዲያጸዱ፤ መናፈሻ እንዲያስጌጡና የማታ ትምህርት እንዲከታተሉ አደረገ። በመገናኛ ብዙሃን ይህንን የተከታተሉ የክልል ወጣቶች የጋሼ አበራ ሞላ እንባ ፈሶ አይቀርም በሚል መፈክር ሰባራ እንስራ እዬከረከሙ አፈር ሞልተው አበባ ተክለዋል፤ አደባባይ ከልለዋል በአዝርዕት አስጊጠዋል። ተግባሩን በገንዘብ፤ ሰው ሃይልና ሙያ ከመደገፍ ይልቅ ዶክተሮች ከሹም ጋር ተመሳጥረው ተመሳሳይ ድርጀት በማቋቋም አጠፉት። በሌላ በኩል በሃገር ቤት የአስተዳደ መሰናክ በውጭ ሃገር ደግሞ ዛሬ አሸነፍን ብለው ጮቤ የሚረግጡት ባለሥልጣን ይበላዋል፤ ልማት ከድል በኋላ፤ መጀመሪያ ስርአቱ ይፍረስ፤ በሚል ቅስቀሳ እንቅፋት መሆናቸውንም ልብ ይሏል!

ከሁሉም አሰከፊው የጥፋት ሃይሎች ለውጡ በሚከፍተው ቀዳዳ አንዱ የገነባውን በአዲሱ ያስፈርሳሉ። ሌላው እንደገና ሲገነባ እሱንም እንደዚያው። በንጉሡ ጊዜ የተገነባውን ልማት በደርግ አሰጠፉት። እንደገና ኢህአዴግ በመገንባት ያለውን በአመጽና ግልብብጦሽ አሁን እያስጠፉ ነው። ለምሳሌ በመነቃቃት ላይ የነበረው ቱሪስት ዘርፍ ዛሬ ቀዝቅዞ ሃገር በማስተዋወቁ፤ ሆቴል፤ ማጓጓዣ፤ አስተናጋጅና ውጭ ምንዛሬ ላይ ተጽእኖ አሳድሯል። ለማገገምም ዓመታት ይወስዳል። ዓለም አቀፍ ግንኙነቱም ተጠምዟል። በቀዝቃዛው ጦርነት ዲፕሎማቶቻችን የአሜሪካንን ቦይንግ አይሮፕላን ቦሌ ላይ የሶቪዬትን ነዳጅ ማጣሪያ አሰብ ላይ ተክለው የኢትዮጵያን ነፃ ሃገርነት ከማረጋገጥ በላይ ከማንም የማትወግን ብቸኛ ሃገር አድርገዋታል። ግን ደርግ ሶቪዬት ጉያ ተወሸቆ የምዕራቡ ዓለም ሲሸሸው የአፍሪካን ሕብረት የተመኙ አፍሪካውያንን መለስ ዜናዊ አሳፋሯቸዋል። አሁንም ሁሉም አጋርነታችንን ማሳዬት ይልቅ ቻይናን አግልለን አሜሪካ ጉያ ልንወሸቅ ይዳዳናል። ቻይና ደግሞ በኢትዮጵያ በኩል አፍሪካን ለመያዝ ብዙዎች የቋመጡለትን የበረራ መስመር የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲምቧሽበት አድርጋለች። ቱሪስት ሃገርም ናትና ሰፊ ገበያ እንዳያመልጠን? የአፍሪካውያንና ቻይና ግንኙነት መጥበቅ፤ የእኛ ትረምስ፤ የመንግሥት ዳተኝነትና የአሜሪካን ማሽሞንሞን የበጎ አይደለምና ሁሉንም እንዳናጣ? አሜሪካ የመገናኛ አውታሮቿን እንደ ቻይና ማዘመን ቀርቶ ያረጁትንም ስለማትጠግን አትሆነንምና ሁሉንም ወዳጅ ማድረግ እንጅ ቻይናን ማግለሉ ሌላው ቢቀር የአፍሪካ ህብረት ሌላ ሃገር ገንብታ ታሳርረናለች! ይህንም ቀደም ሲል ኢትዮጵያ የነበሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጥለው እንደሄዱ አሳይቻለሁ። አፍቃሪ አሜሪካ ለመሆናችንም አትራፊ ተቋማት የግል ለማድረግ መታሰቡ ነው። መርፌ አብልቶ ማረሻ ማስተፋት እንዲሉ ጥቂት ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ብንሸጥ ገዥው ብር ስለማይወስድ ቡና ዶላራችንን እንዳናስረክብ? ወጭ ቀነሶ ትርፍ ማሳደግ የሚልው የባለ ሃብቶች አሰራርም ብዙ ሠራተኛ ሰለሚያባርር ሥራ አጥነትን እንዳናበራክት? ከሁሉም በላይ ገንዘባቸው የሚመጣጠን ሃገሮችም ድርጅት ሸጠው አልተጠቀሙ እንኳን እኛ ድምበር የማይሻገር ብር ይዘን!

በሰው ቁስል እንጨት ሰደደበት እንዲሉ እኛ እርስ በርስ እንደ ዱባ ተቀራደን፤ እንደ ሥጋ ተከታተፈን፤ እንደ አገዳ ተከታክተን መጠፋፋቱ ሳያንሰን ነጮቹም ወዳጅና አጋዥ መስለው ቦርቡረውናል። አሁንም አያርፉልን። ለምሳሌ የእንግሊዝ ሠራተኛ ፖለቲካ ፓርቲ (labour party) ከራስ ጸጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ የሻብያ ደጋፊ እንደ ነበር Eritrea: Never Kneel Down, 1985, by James Firebrace with Stuart Holland MP Preface by Neil Kinnock (later labour leader) የሚል መጽሐፍ አለ። የሆላንድ ክርስቲያን እርዳታ ድርጅትም Without Troops & Tanks [Humanitarian Intervention, The Emergency Relief Desk and the Cross Border Operation into Eritrea and Tigray, 1994, by Mark Duffield and John prendergast እንደዚሁ። በአሁንስ እጃቸው የለም ማለት ይቻላል? ምን ለማን እዬሰሩ ነው ስለማንልም እርስበርስ ከማጨራረስ አይመለሱምና ከመጠንቀቅ ሌላ አማራጭ የለንም።

እናም አጥንተንና አስጠንተን አውቀንና አርመን ማደግና መበልጸግ ሲገባ ያለፍናቸው ችግሮቻችንንና የጥፋት ሃይሎች ተወያይተን እንድንማማርበት ያቀረብኩትን ጥፋትና የእኛን መዘናጋት እንዲህ ልቋጨው፡ -

ሀ) የተለያዩ ልማት አካባቢዎችን ተግባር ሳነሳ የኢትዮጵያ አንድነት ተፈጥሯዊ ነውና ደጋው እርሻ ቆላው አርባታ፤ ሰሜኑ ሰብል ደቡቡ ሥራሥራና ፍራፍሬ ሲያመርቱ በንግድ እንዲተሳሰሩ መሆኑን ልብ ል። አውሮፓውያን በጦርነት ተላልቀው የጋራ ገበያ በመመስረት የጣሊያንን ፓስታ፤ የፈረንሳይን ወይን ጠጅ፤ የሆላንድን የደረቀ አይብ፤ የስፔይንን ፍረፍሬና ዘይት ተለዋውጠው በሰላም እድገትና ብልጽግና ይኖራሉ። እኛ ግን ተፈጥሮ የለገሰንን ተባብሮ ማደግ አጥፍተን ልንጠፋ ተናንቀናል። እናም ሃገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ድምበር ተሻግረን በመገበያዬት ማደግ ከፈለግን ያለንን የተፈጥሮ የልውውጥ ፀጋ ከማጎልበትና ከማጠናከር ሌላ አማራጭ እንደሌ ልብ እንበል

ለ) የኢትዮጵያውያንን ሥራ ፈጣሪነትና ኢንቬስተርነት ሳነሣ ቁጥሩ እየጨመረ የመጣው ሥራ ፈላጊ ወጣት በአግባቡ ካልተያዘ ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ቦምብ ነውና ባለሥልጣናት የምታውቁለት ከሆነ ሥራ ፍጠሩለት እናንተ ካልሆነላችሁ እሱ ራሱ እንዲፈጥር አመቻቹለት አለያም ባለሙያ አሰባስባችሁ ያፈላልጉለት።

ሐ) ፖለቲከኞች የምር ፖለቲከኛ ከሆናችሁ ቋንቋችሁን ከተቻለ ዓለም አቀፋው ካልሆነ ብሔራዊ አድርጉት። አወቅን ብላችሁ በጎሣ ፖለቲካ ሕዝብ ለዘመናት የነበረውን ሰላምና አብሮ መኖር አታናጉበት። ዳሩ በተመሣሣይ ስምና ለአንድ ህዝብ ቆመናል ብላችሁ መብዛታችሁ እራሱ እናንተ ተበትናችሁ ሕዝብን ለመበተን እንዳልቦዘናችሁ አንካካድ። ለመሆኑ ሙያ፤ ልምዱ፤ መስፈርት ማሟላቱና መደራጀቱ ቢቀር የሕዝብ ተወካይ አድርጋችሁ ራሳችሁን ስተሾሙ ማን አውቋችሁና ማንንስ አውቃችሁ ነው?

መ) ድሃ በጉልበቱ ሃብታም በገንዘቡ በሚል መርህ ህብረተሰብ ስለሚያስተባብር ኢትዮጵያዊ ተቋም ለውጭ ወዳጆቼ ሳዎጋቸው መደነቅ አዘምናችሁ ሌሎች ቢማሩበት ይላሉ። አዎ! ትኩረት ያላገኘው፤ እየጠፋ ያለውና የባህል ፀጋ የሆነው ሙት የሚቀባበርበት፤ ሃዘንተኛ የሚጽናናበት፤ ሃበታም ገንዘቡን ድሃ ጉልበቱን የሚያስተባብርበት ሳይገለሉ የሚስተናገዱበት እድር። ሃበታም ገንዘቡን ሰጥቶ ሲሰተናገድ ድሃ ሴት ለተመሳሳይ መስተንግዶ ከሌሎች ጋር ቆሎ ተቆላልች፤ ቡና ታፈላለች፤ ታስተናግዳለች። ድሃ ወንም በገንዘብ ምትክ ከሌሎች ጋር ቀብር ይቆፍራል፤ ዕቃ ይሸክፋል፤ ያጓጉዛል። ግን እየተዳከም ነውና እንዳይጠፋ አዳብራን እንደግበት ሌላተምሮ ይጠቀምበት

ባለሥልጣናት ጎራ ለይታችሁ ጣት ከመቀሳሰሩ በአንድ አዳራሽ ተሰብስባችሁ በር ዝጉና የወሰደውን ጊዜ ወስዳችሁ ልዩንታችሁን ፍቱ። ካልፈታችሁ በባለ ሙያ የታገዘ ኮሚቴ ሰይሙና ይፍታው። ዳግም ላለመከዳዳትም ቃል ግቡ። የአማካሪንም ምንነትና ማንነት መፈተሽም ዓላማን ማሣካት እንደሆነ አትዘንጉ

) የጋሞ ሰው ግድያና መፈናቀል ሊያስከትል የሚችልውን መተላለቅ በሰላም በመፍታት የሃገር ሽማግሌ፤ ገዳ እድር፤ ለሰላም ያላቸውን አስተዋጽኦ አሳይተዋል። መሠረቱ ሕዝብ ነውና ከፍተኛ ባለሥልጣናት አካባቢ ተከፋፈላችሁ ወደ ህዝብ ውረዱና የምክርና መፍትሄ ግብአት ሸመቱ። ባትሰሙት እንጀ ሕዝብ በተለያዩ መገናኛዎች መንግሥት ብቻውን አይሰራውም፤ ችግሩን ወደ ታች ወርዶ ይመልከተው እያለ ነውና እረስበርስ መሿሿሙን ብቻ ሳይሆን ውክልናችሁንም ሕዝባዊ አድርጉት። ያጠፋሉ ስለማይባሉ በእናንተና በተገልጋይ መካከል ሁለት ፀጉር አብቅለው የሚዋሹ፤ ሙያና ዕውቀን ለጥፋት የሚያውሉና ሕዝብ የሚያስለቅሱ አካላት በሃገራችን በሽበሽ ነው።

) ካለፈው ብታጠኑና ብታስጠኑ የሚጠቅመው እንቅፋትንና ችግርንም እንጀ ጥፋት ብቻ አይሁን። የፈሰሰ ውሃ አይታፈስም እንዲሉ ጥፋ ያጠፋውን አጥፍቶ አልፏል። የጠፋን ያልጠፋ ማድረግ አይችልምና ባለፈው ላይ ጊዜ ማባከኑ መራራቁን ያሰፋ እንጀ አያጠበውምና ሌሎችን መወንጀሉን ላይ የሙጥኝ አትበሉ

) ከውጭ ውስጥም የሚነዛው የወሪና አሉባልታ መርዝ በሃገር ላይ ብዙ ጥፋት አድርሷል። በማድረስም ላይ ነው። ካለተገደበ የበለጥ ጥፋት ከማድረስ አይመለስምና ባለሙያ አሰባስባችሁ አደራጅታችሁ ማርከሻውን መልሰው ያርከፍክፉበት። እሾህን በእሹህ እንዲሉ ውሸቱን ውሸት እንደሆነ በተጨባጭና በወቅቱ በተገኘው መገልገያ ሁሉ አሰራጩ። በዚህም እራሳችሁን ብቻ ሳይሆን እንደ እሣት ራት የሚማገደውን ወጣት ትታደጋላችሁባለመሆኑም ነው በንጉሡ ድንጋይ ይወረውር የነበረ ወጣት በደርግ ያስወረወረው። በደርግ የወረወረው በኢህአዴግ ያስወረወረውዛሬ ድንጋይ የሚወረውረው ነገ ያስወረውራል። ምክንያቱም ድንጋይ መወርወር ዕውቀትና ሙያ አይጠይቅም በውሸት፤ አሉባልታ፤ ያልተጨበጠ ተስፋ ነውና የሚነዳው

) ለተከፈለው መስዋዕትነት፤ ለተዘረጋው የልማት አውታር የምታስቡና መጥፋቱ የሚያሳስባችሁ ሁሉ ቆሞ ከመመልከትና ጥፋቱ ስርአቱን ያጠፋዋል በሚል ከመጠበቅ የጋራ መፍትሄ ለማፈላለግ እውቀት፤ ጊዜ፤ ጉልበትና ገናዘባችሁን መስዋዕት አድርጉ። የጥፋት ትርፍ የለውምና። ያለበለዚያ የፉክክር ደጃፍ (መዝጊያ) ሳይዘጋ አደር እንዲሉ ሁሉንም ለዘራፊ ሰጥተን ሁላችንም ባዶ እእንቀራለን። ያወጣ ያውጣው መስዋዕትነት የከፈሉትንና ለልማቱ የደከሙትን ሁሉ ፍሬ አልባ ማድረግ ነውና ለመፍትሄ መረባረብ ዕድገቱን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ለመጭው ትውልድ በጎ አስቦ በጎ ማቆዬት ነውና

) የለውጡ ጠላቶች፤ የቀድሞ ባለ ጊዜዎች፤ ጥቅማቸው የተነካ፤ ወዘተ የሚለው ማሰበቢያ በጥናት ያልተደገፈ ከመሆኑም በተጨማሪ ሥልጣን ላይ ከወጣው ሁሉ ስንሰማው ኖረን ሰልችቶናልና በመረጃ አስደግፋት። ምክንያቱም ከላይ በግልጽ እንዳዬነው በግርግሩ ቀንደኛው የጥፋት ሃይል ሳይጋለጥ ያጠፋል። ደርግም፤ ኢህአዴግም በዚህ አባባል ነው ከጥፋት ያልዳኑትና ትክክለኛውን አጥፊ ለይቶ ለማደግና ለሠላም ወቀሳና ውንጀላው በጥናት ምርምር የተደገፈ አድርጉት

) ሰው ሁለት ዛፍ ላይ በአንድ ጊዜ አይወጣም ጠቅላይና ም/ጠቅላይ ሚኒስቴርም የሚኒስቴሮች ሰብሳቢ፤ የአስተዳደር ዳኛና የሁሉም ጥቅም አስከባሪ እንጀ በግል የምታስከብሩለት አካል ሊኖር አይገባም። በመሆኑም ጠቅላይ/ምክትር ሚኒስቴር በፓርቲያቸው ስብሰባ የጎሳቸውን ጥቅም እናስረክባልን ሲሉ ሚኒስቴሮች የእነሱን ቦታ እንዲጠይቁ ያነሳሳል። ምክንያቱም እነሱም እንደ እናንተ ጥቅሙን የሚጠብቁለት ጎሣ አለና። ስለዚህ በንግግርም ይሁን ተግባር ወደ መሃል ግቡና ለሁሉም ጥቅም ቆማችሁ በማሳዬት ሃላፊነትና ግዴታችሁን ተወጡ አለያም የሁሉንም ጥቅም ለሚያስከብር ቦታውን ልቀቁ። የሚጻፈውና የሚነበበው የሚታመን ከሆነ ሥልጣን የያዛችሁት በችሎታ ሣይሆን በጎሣችሁ ነው ይባላልና በተግባር አስተባብላችሁ ብታሳዩን?

ቸ) ስርአቱን ለመገርሰስ የኢትዮጵያን ልማትና ባለሙያ ስታሳድዱ ቆይታችሁ አሁን አሸነፍን በሚል ጮቤ የምትረግጡ ሁሉ 7 ሚሊዮን ህዝብ እርዳታ ያስፈልገዋል እዬተባለ ነውና ሸሚዛችሁን ጠቅለል፤ ሱሪያቻሁን ሸምለል አድርጉን ታደጉት። ልማታችሁንም አሳዩን። ለጥፋት ታስባስቡ የነበረውንም እርዳታ ለተፈናቀለውና ድሃ ወገን አውሉት። መንገድም አንጥፉለት፤ ኤሌትሪክ መስመርም ዘርጉለት፤ ንፁህ ውሃም አቅርቡለት፤ ጤናውንም ጠብቁለት።

) ጉቦ፤ ሙስና፤ ኪራይ ሰብሳቢ የሚለው ሌሎች የሚሉትን ለማለት ካልሆነ በስተቀር በሃገራችን አይሰራም። ምክንያቱም ከእርዳታና ብድር በጀት የሚመዘበር ነገር የለምና። በነዳጅ ሃብቷ የምትታወቀው ናይጀሪያ፤ በማዕድኗ በምትታወቀው ደቡብ አፍሪካና የቱሪስት ባለሃብቷ ኬንያ በሙስን እንደ እኛ አይንጫረሩም። ለምዝበራ የሚያመቸው የእነሱ እንጅ በብድራና እርዳታ በጀት የምትዳደር ሃገራችን አይደለችም። የምንወነጅለው ፍርፋሪ እየለቀመ ድሃ የሚያስለቅሰውን ከሆነ አብዝሃኛው ነውና እስርቤትም አይበቃን። ስለዚህ አስተዳደሩን፤ መዋቅሩንና ንብረት ፈጠራውን የሚያደናቅፉትን ተከታተሉ እንጅ ሌላው ወሬ ብቻ ነውና ሥልጣን ማሳያ አታድርጉት።

) ፌደራል አሰተዳደር ዓለም በስፋት የሚገለገልበት የአመራር ተቋም እንጅ የጎሣ ሸማ አይደለምና በየመንደሩ ለብሶ የሚንጫጫውን እርቃኑን አስቀሩትበተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አሳፍሩት። ሕዝብ የመንግሥትን መመሪያ አክብሮ የራሱን ኑሮ በራሱ አቅምና ችሎታ እንዲመራ የሚያግዝው መሣሪያውም ነውና። በመሆኑም አዲስ አበባና ፈረንጃ ሃገር የተሰገሰገውን ፀረ-ፌደራሊዝም ባለሙያ ተብዪና የበታች ባለሥልጣን ብዙ አታቅርቡት። ለባለሥልጣን ጆሮ ቅርብ በመሆኑ የሚያማክረው ስለጥፋት ብቻ ሆኖ የስርአቶች ሁሉ ዋና በሽታ ነውና። ቢቻል እሱ የሚለውን ባታዳምጡ ካልተቻለ ደግሞ የሚነግችሁን ሁሉ ብታመሳክሩ ቢያንስ እራሳችሁንም ሃገርንም ከመከራና ጥፋት ትታደጋላችሁና!!!

 

 

ቅን አስተሳሰብና በጎ ተግባር ከሁላችሁ ጋር ይሁን!

Back to Front Page