Back to Front Page


Share This Article!
Share
ህገመንግስታችንና ወታደራዊ መለዮአችንክቁንጮው እስከ ግርጌው ይከበር

ህገመንግስታችንና ወታደራዊ መለዮአችን ክቁንጮው እስከ ግርጌው ይከበር

 

Tignen Tidmek 2-28-19

ክጥሰቶች ሁሉ ጥሰት ህገ መንግስት ማክበርና የማስከበር ክፍተኛ ሃላፊነት ያለበት ቁንጮው አመራር ጥሶ ሲገኝ ነው : : በአሁኑ ወቅት በስመ መደመር ያለማቋረጥ በአገራችን ታይቶ በማይታወቅ ቅጽበት በህገመንግስት ላይ በማን አለብኝነት መረማመድ ፣ በሰው ህይወት መቀለድ ፣ ወዘተ እየታየ ያለበት ጊዜ ከሆነ ሰነባብተዋል : : ይህንን ኢ ህገመንግስታዊ ድርጊቶች በአገራችን ስለ መፈጸማቸው እንደሚከተለው ጥቂቶችን መጥቀስ ይቻላል : :

         የወሰን ኮሚሽን የማቋቋም ስልጣን የፌዴሬሽን ምክርቤት እያለ ክህገመንግስት ውጭ በተወካዮች ምክርቤት ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ተነጥቆ ኮሚሽን እንዲቋቋም ቁንጮው መሪ በህገመንግስት ላይ መረማመድ ፤

Videos From Around The World

         የዜጎች ህገመንግስታዊ የማንነት ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ባሻገር አፍኖ ይዞ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ጆሮዳባልበስ በማለት ለምሳሌ በአማራ ክልል የ ቅማንት ህዝብ የማንነቱን ጥያቄ በማንሳቱ የቅማንቶች ቤትና ንብረት ሲወድም ፣ ለእንግልትና ስደት ፣ በገፍ ለሞት እየተዳረጉ እያሉ ቁንጮው አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ጸጥ ረጭ ማለት፤

         በአገሪቱ ህገመንግስት መሰረት ማዕከላዊ መንግስት ከክልሎች በላይ ይህ ነው የሚባል የጎላ ስልጣን የለውም በተግባር እየታዘብነው ያለው ነገር ግን ማዕከላዊ መንግስት በክልሎች ጣልቃ የመግባት ባህሪያት በስፋት ሲሄድበት ነው ፤

         የዜጎች በሚልዮኖች መፈናቀል ቁንጮው አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ጆሮዳባልበስ ማለት፤

         ብሄርን መሰረት ያደረገ ጥቃት በአገሪቱ በስፋት እየተፈጸመ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ጆሮዳባልበስ ማለት፤

         ዜጎች በኣገራቸው በፈለጉት የመኖር መብት በስፋት ኣየተጣሰ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ጆሮዳባልበስ ማለት

         ወዘተ በየቀኑ የሚሰማ ዜና ከሆነ ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው: :

ቁንጮው መሪ ዶ/ር አብይ አሕመድ ያለፈውን የአገልግሎት ዘመናቸው ስንቃኝ ለዓመታት በውትድርና ሲያገለግሉ እነደነበሩና ከበርካታ ዓመታት በፊትም ከመከላከያ ሰራዊት አባልነት ተሰናብተው ወደ ፖለቲካዊ ዓለም እነደተቀላቀሉ የሚታወቅ ሃቅ ነው: : ወደ ፖለቲካ ዓለም ከገቡ በኃላም በኦህዴድ አባል በመሆን ኣሁንም የኦዴፓ አባል እንደሆኑና በመንግስት ከፍተኛ የስልጣን እርከኖች ላይም እንደነበሩ ይገለጻል : :

እንደሚታወቀው በቅርቡ የፖለቲካው መሳልል ተጠቅመው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ እነደተቆናጠጡ ለሁሉም ግልጽ ነው : : በዓለማችን ላይ በፖለቲካዊ ስርዓትና አሰራር የሚከተሉት አገራት አገሪቱን የሚያስተዳድር በህዝብ የተመረጠ ሲቪላዊ መንግስት ሲሆን መከላከያ ሃይል ደግሞ ያገሪቱን ህገመንግስት የሚያስከብር ፣ ከውጭም ከውስጥ የሚቃጣን ጥቃት የሚከላከል ፣ ያንድን አገር ህዝብ ድህንነትና ሰላም ማስከበር ዋና ተግባራት ናቸው : :

ሲቪላዊና በህዝብ የተመረጠ መንግስትም ሲቪል በመሆኑ ሲቪላዊ ባህሪያትና ስነምግባር ያለው እንዲሆንና ሆኖ ማየት ህዝቡ ሁሌም ይጠብቃል : : እንዲሁም ያንድን አገር መከላከያ ሰራዊትም በአለባበሱና ባህሪያቱ በመለዮው ባጠቃላይ ወታደራዊ ባህሪያት የተላበሰ ሰራዊት ሆኖ ማየት ህዝቡ ይጠብቃል : : እነዚህ ሁለት የህዝብ አካላት በየፊናቸው የሚያገለግሉትን ህዝብ ከነሱ ምን እንደሚጠብቅ በመገንዘብ ስነምግባራዊ የሆነና ስርዓት ባለው አኳሃን የእለት ተእለት ተግባራቸውን መፈጸም ይጠበቅባቸዋል : : ለምሳሌ አንድን በህዝብ የተመረጠ ሲቪላዊ መሪ በፓርላማ ወይም በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በሚቀርብበት ጊዜ ሲቪላዊ ፕሮቶኮል ኣሟልቶ እስከነ ኣለባበሱ ጭምር ሲቪል ሆኖ መቅረብ ይኖርበታል : : በተመሳሳይ ሁናቴም አንድ የመከላከያ ጀኔራል መግለጫ ወይም ማብራሪያ ለመስጠት በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት መቅረብ ካለበት እስከነ መዓርጉ የመከላከያ ሰራዊት ደንብ ልብስ ለብሶ መቅረብ ይጠበቅበታል : : እንደዚሁም አንድ ሲቪላዊ በህዝብ የተመረጠ ባለስልጣን ለአገራዊ ጉዳዮች ወደ ውጭ ኣገር በሚጓዝበት ወቅት ሲቪላዊ ፕሮቶኮል የአለባበስ ደንብ ተከትሎ ኣገሩን ወክሎ እንዲሄድ ይጠበቃል : : በተመሳሳይም ወታደራዊ ጄኔራሎችና መኮንኖች ለኣገራዊ ጉዳይ አገርን ወክለው ወደውጭ ኣገሮች በሚጓዙበት ሁኔታም በተመሳሳይ ወታደራዊ ፕሮቶኮልና የአለባበስ ደንብ ተከትሎ አገሩን ወክሎ እንዲሄድ ይጠበቃል : :

እንዲሁም አንድ የሲቪላዊ መንግስት መሪ በተለያየ ወቅት የአገሪቱን የመከላከያ ሃይል መጎብኘት ቢፈልግም ሲቪላዊ ሙሉ ልብስ መልበስ ባያስፈልግ እንኳን ሲቪልነቱን የማይቀይር ጃኬትና የመሳሰሉት ይለብሳል እንጂ መከላከያ ሰራዊት የሚለብሰውን ወታደራዊ ደንብ ልብስ ለብሶ በሰራዊት ፊት ላይ አይቀርብም : : እንግዲህ አንድ በህዝብ የተመረጠ ሲቪላዊ መንግስት በአለባበሱና ሌሎች ባህሪያቶቹ የመረጠውን ህዝብ በማክበር ህዝባዊና ሲቪላዊ ባህሪያት የተላበሰ መሆን እንዳለበት በጥቂቱም ቢሆን ለመግለጽ ተሞክሯል : : በዓለማችን በተጨባጭ የሚታወቁ ሲቪላዊ መሪዎች በተለያዩ የውስጥ ሃገርና የውጭ ሃገር ጉብኝት በሚያደርጉበት ጊዜ ሲቪላዊ የአባበስ ደንብና ፕሮቶኮል ጥቂቶቹን ለማየት እንሞክር : :

 

ከላይ እንደተገለጸው አንድ ሲቪላዊ መንግስት ምን መምሰል እንዳለበት መሰረት በማድረግ በአሁኑ ወቅት የአገራችን ሁኔታ በተለይ በአሁኑ ወቅት ያለው መሪ የሚያሳያቸው ባህሪያት በዓለም ላይና ከዚህ በፊት ከኣምባገነኑ የደርግ መንግስት በኃላ የነበሩ መሪዎች የአለባበስ ደንብ በማነጻጸር እንመልከት : :

         ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አንድም ቀን ወታደራዊ ልብስ ለብሰው ሲጎበኙ የታዩበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም

         ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝም እንዲሁ አንድም ቀን ወታደራዊ ልብስ ለብሰው ሲጎበኙ የታዩበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም

         ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ ከከፍተኛ የመከላከያ የሰራዊት አባላት በቢሮኣቸው ወይም በጠቅላይ ሚኒስቴር አዳራሽ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰብስበው ባካሄዱት የውይይት መድረክ በቴሌቪዥን ሲቪል ለብሰው ነበር የታዩት : :

         በደብረዘይት የመከላከያ ሰራዊት የምርቃት ፕሮግራምም ሲቪል ለብሰው ነበር የቀረቡት : :

         የቡሬንና የዛላንበሳን ድንበር ለመክፈት ኢትዮጵያን ወክለው ከኤርትራው ፕረዚደንት አቶ ኢሳያስ ኣፈወርቂ ጋር ዶ/ር አብይ ኣሕመድ ሲቪላዊ አለባበስ ሳይሆን በወታደራዊ ዩኒፎርም ሆኖ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከሚለብሰው ዩኒፎርም የተለየ ለብሰው ነበር የታዩት : :አቶ ኢሳያስም በተመሳሳይ በከፊል ወታደራዊ የሚመስል ዩኒፎርም ለብሰው የታዩ ሲሆን የአቶ ኢሳያስ ወደ ኤርትራ የፕሬዚዳንትነት አመጣጥበሲቪላዊ ወይም በወታደራዊ ሂደት ሁኔታሊያያዝ ስለሚችል ለጊዜው ቢቆይልን ይሻላል : :

         ባለፈው ታህሳስ ወር 2011 ዓም በአዲስ አበባ በቤተመንግስት አካባቢ የመከላከያ ሰራዊት ኮማንዶ ክፍል ባደረገው ትዕይንት ጊዜ ዶ/ር አብይ ኣሕመድ በወታደራዊ ዩኒፎርም ሆኖ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከሚለብሰው ዩኒፎርም የተለየ ለብሰው ነበር የታዩት : :

         በ7ኛው የመከላከያ ሃይል ቀን በአዳማ በየካቲት 2011 ዓም በተከበረበት ወቅትም በወታደራዊ ዩኒፎርም ሆኖ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከሚለብሰው ዩኒፎርም የተለየ ለብሰው ነበር ንግግር ሲያደርጉ የታዩት : :

ለንጽጽር ያክል ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ኢትዮጵያን በጊዚያዊ ወታደራዊ መንግስት ስም የአገሪቱ መሪ በነበሩበት ጊዜ ሲለብሱት የነበረው የኢትዮጵያ ወታደራዊ መንግስት ዩኒፎርም ሲሆን የይስሙላ ምርጫ ደርግ ካደረገም በኃላ የኢሰፓ ዩኒፎርምና አልፎ አልፎም ሲቪላዊ ሙሉ ልብስ ያዘወትሩ ነበር : : በኢህኣዴግ መራሹ ሃይል የደርግ ስርዓት ሲንኮታኮትና የመንግስትነት ጊዜኣቸው ሊያከትም ጥቂት ወራት በቀሩበት ወቅት ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ያየኢሰፓ ዩኒፎርማቸው ኣሽቀንጥረው እስከ የመጨረሻዋ ወደ ዝምባብዌ የፈረጠጡባት ጊዜበወታደራዊ ዩኒፎርም ነበር የዘለቁት : :

የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ኣብይ አሕመድ በተለይ ለመከላከያ ሰራዊት አባላት መለዮአችሁን ማክበር ኣለባችሁ ፣ ሰራዊቱ ለመለዮው መቆም አለበት እያሉ ሲናገሩ በተደጋጋሚ ይደመጣሉ : : ዶ/ር አብይ አሕመድ ግን በሲቪላዊና በህዝብ የተመረጡ የዓለማችን መሪዎች ከሚያደርጉት ሲቪላዊ የአለባበስ ባህሪ በጣም በወጣናበተለየ አኳሃን በወታደራዊ ዩኒፎርም በመቅረብ ብቻ ሳይሆን የተለየ ዩኒፎርም አድርገው (ቢያንስ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ወታደራዊ ዩኒፎርም) በተከበረውና የኢትዮጵያ አለኝታ በሆነው መከለከያ ሰራዊታችን ፊት ቆመው ስለመለዮ ሲናገሩማየት ሰውየው የብስለት ችግር ፣ የዕውቀት ማነስ ፣ የግዴለሽነትን ፣የማን አለብኝነትንና የፈላጭ ቆራጭ ባህሪ ካላቸው የመሪዎች ተርታ ያሰልፋቸዋል: : ይህ ሰው በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ የመሪነት ቦታ የተቆናጠጡሲቪላዊ መሪ ፣ የኢትዮጵያ ያልሆነ ወታደራዊ መለዮ ለባሽ መሪ (ዶ/ር አብይ አሕመድ) ለኢትዮጵያዊው መለዮ ለባሽመከላከያ ሰራዊት ስለመለዮ መናገርና ማውራት ፣ መሪው ራሱ (ዶ/ር አብይ አሕመድ) ምን ዓይነት መለዮ መልበስ እንዳለበት በውል ሳያውቅ፣ የራሱ ያልሆነ መለዮ ለብሶ በድፍረት በትክክል መለዮውን ለብሶ ላለው መከለከያ ሰራዊትናገና ከቅጥር ጀምሮ የመለዮ ምንነት ጠንቅቆ ለሚያውቅ አካል ስለመለዮ መናገር የመሪው ጨቅላነትን ከማጉላት በቀር ሌላ ሊባል የሚችል አይመስለኝም: : የአንድን አገር ሲቪላዊ መሪ ሲቪላዊ መለዮውን አስቀምጦ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ዋታደራዊ መለዮ ለብሶ በድፍረት በመከላከያ ሰራዊት ፊት ቆሞ ስለመለዮ መናገር እንደ መሪ የመሪነት ሚናአለማወቅና እራስህን በውል አለመገንዘብንያሳያል : ኢትዮጵያ ሲቪላዊ ባህሪያት የተላበሰ መሪ እንጂ ወታደራዊ ባህሪያት የተላበሰ መሪ አያሰፈልጋትም : : በአንድ አገር በህዝብ የተመረጠ ሲቪላዊ መሪ ሲቪል ሲቪል ሲሸት እንጂ ወታደር ወታደር መሽተት የለበትም : : ወታደርም እንደ ሚናው የወታደር አገር የመከላከል ወታደራዊ ቃና እነዲኖረው በህዝብ ዘንድ ይጠበቃል : :ሲቪላዊ መሪ ከሲቪላዊ ባህሪያት ወጥቶ በተደጋጋሚ ወታደራዊ ባህሪያት የመላበስ አባዜ ደርግን እንድናስታውስ ያደርገናልና : :

 

ስለዚህ በቁንጮው እየተደረገ ያለው የህገመንግስት ጥሰቶችና የሚና መደበላለቅ ታርመው አገሪቱንአገር ያሰኛትን ህገመንግስት ማስከበር አለበት ፣

ከጥሰቶች ሁሉ ጥሰት የህገመንግስት ጥሰት ስለሆነ ይህንን ክፍተኛ ወንጀል የፈጸሙ በየትኛውም የስልጣን እርክን የሚገኙ አካላትየኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ስለሆኑ የኢትዮጵያን ክብር ለመመለስና ታላቁን የህዝቦች ህገመንግስት በነበረበት ክብሩ እነዲኖር ጥሰት ፈጻሚዎችን አንድ ባንድ መጠየቅና ለፍርድ መቅረብ አለባቸው: :

ሲቪላዊ መንግስትም ሲቪላዊ መለዮውን አስቀምጦ መታደራዊ መለዮ መልበሱን ያቁም: : ሁሉም የመንግስት አካላት የየራሳቸው መለዮ ሰላላቸው የየራሳቸው ሚናና ድርሻ ጠንቅቀው ያውቃሉና : :

መከላከያ ሰራዊታችንም የህዝብ አብራክና ለህገመንግስት የቆመ እስከሆነ ድረስ ከህገመንግስት ውጭ ለሚሰጠው ትእዛዝ እንዲሁ ትእዛዝ ስለሆነ ብቻ መቀበልና መተግበር የለበትም: : ማንኛውም ከህገመንግስት ውጭ የሚያዝና የሚተገብር አካል የጊዜ ጉዳይ ይሆናል እንጂ ከመጠየቅ ኣንዳቸውም ሊያመልጡ አይችሉምና : :

ከየትኛውም በከፍተኛ አመራር የስልጣን እርከን ከሚገኝ አካል የሆነ ትእዛዝ ቢመጣም ትእዛዙ ኢ-ህገመንግስታዊ አለመሆኑን ሳያረጋግጥ መንቀሳቀስ የለበትም : : መከላከያ ሰራዊት የህዝብ አደራ የሚጠብቅ ሃይል እስከሆነ ድረስ የህገመንግስት ጥሰቶችን በአንክሮ መመልከት ኣለበት : :መከላከያ ሰራዊታችንም አንዱና ዋነኛው የቆመለት ዓላማ ህገ መንግስት ማክበርና ማስከበር ስለሆነ ለሚታዩ የህገመንግስት ጥሰቶች በኣንክሮ በመመልከት የህዝብ መሪ ነኝ በሚል ሽፋን የአገሪቱን ህገመንግስት እየጣሰ እያየ ዝም ብሎ መመልከት የለበትም : :

በቅርቡ እንደምናስታውሰው ኢ-ህገመንግስታዊ በሆነ አካሄድ ቤተመንግስት ገብተዋል ተብለው ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሁሉ በተመሳሳይም የህዝብ መሪ ነኝ በሚል ሽፋን የአገሪቱን ህገመንግስት በጠራራ ጸሃይ እየጣሰ ሲገኝ ይህንን ህገመንግስት ጣሽመሪአደብ እንዲገዛና በህገመንግስትና ህግ ብቻ እንዲመራመከላከያ ሰራዊት ክምንግዜም በላይ ህገመንግስት የማስከበር ተልዕኮውን የመወጣት ከፍተኛ ሃላፊነት ያለው መሆኑን መዘንጋት የለበትም : : ምክንያቱም ማንኛውም ሰው (መሪ ፣ተመሪ ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ፣ ዘበኛ ፣ ወዘተ) ክህገመንግስት በታች እንጂ ክህገመንግስት በላይ ሊሆን ከቶ አይችልም : :

በመከላከያ ሰራዊት የፖለቲካ አጀንዳ ማስረጽ በጣም አስነዋሪና ኢ-ህገመንግስታዊ መሆኑን ሁሉም የመከላከያ ሰራዊት አባል መገንዘብ አለበት : :አንድ መሪ ነኝ ባይ የፖለቲካ ዓላማ ይዞ መንቀሳቀስ ካለበትም በመከላከያ ሰራዊት ምህዳር ሳይሆን በህዝብ ላይ ነው : : ከዚህ ውጭ ግን መከላከያ ሰራዊቱ ነቅቶ እያንዳንዷን የጠቅላይ ሚኒስትሩ እንቅስቃሴ በሪፎርም ስም በመከላከያ ሰራዊታችን የፖለቲካ ጨዋታ እነዳይጫወት መመርመር ፣ መጠየቅ ፣ አሳማኝ ሆኖ ካልተገኘ ደግሞ መቃወም ይኖርበታል: : የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በውይይት ፣ በምክንያዊነት የሚያምንና ዴሞክራሲያዊ ዲሲፕሊን ያለው ሰራዊት ስለሆነ ይህንን ተቋማዊ ባህሉ እንዲሸረሸር ለማንኛውም ህግ ጣሽ አዛዥ ነኝ ባይ ከመስመሩና ከስርዓቱ እንዲወጣ ዕድል መሰጠት የለበትም : :

 

ቸር እንሰንብት !!!

Tignen Tidmek

tidmektignen@gmail.com

Back to Front Page