Back to Front Page


Share This Article!
Share
ኢትዮጵያ ወይም ዓለም አለቀ vs. መከባበር አልያም መለያየት

ኢትዮጵያ ወይም ዓለም አለቀ vs. መከባበር አልያም መለያየት

በታዲሱ አብርሃ 2-26-19

የፈረንጆች ሁለተኛው ሚሊኒየም ከመድረሱ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት፤ ሁለት የተለያዩ አበይት አስተሳሰቦች የሚያራምዱ በታወቁ የፖለቲካል ሳይንስ ፕሮፌሰሮች በፍራንሲስ ፋኩያማ እና በሳሙኤል ሀንቲንግተን 2 መፃህፍት ተፅፏል፡፡ የቀድሞ መምህር (ሀንቲንግተን) እና የቀድሞ ተማሪ (ፋኩያማ)፣ የያኔው የስራ ባልደረቦች በነዚህ መፃህፍት ምክንያት ከፍተኛ ዝናና ሰፊ ተደማጭነት አግኝተዋል፡፡

“The End of History and the Last Man” ወይም በግርድፉ “የታሪክ ማብቂያና የመጨረሻው የሰው ልጅ” የተሰኘው መፅሃፍ በ1992 ዓ.ም በፍራንሲስ ፋኩያማ የታተመ ሲሆን የመፅሃፉ አንድምታም የምዕራባውያን ሊበራል ዲሞክራሲና ነፃ ገበያ የሰው ልጅ የማህበራዊና ባህላዊ እድገት እንዲሁም የስነ-መንግስት ቅርፅ የመጨረሻ ጠርዝ ነው….በመሆኑም እድገት የሚሻ አካል (ግለሰብ፣ ቡድን፣ ሀገር ወዘተ) ሌላ አማራጭ የተዘጋ ስለሆነ በምዕራባውያን መንገድ ብቻ መጓዝ ይኖርባቸዋል የሚል ነው፡፡

Videos From Around The World

በቀድሞ ተማሪው የተሰነዘረ አስተሳሰብ ለመመከትም፤ ሳሙኤል ሀንቲንግተን በ1996 “Clash of Civilization and Remaking the New World Order” ወይም በግርድፉ የእድገት ግጭትና የዓለማችን ምሪት የሚል መፅሃፍ ለአንባብያን አድርሷል፡፡ የዚህ መፅሃፍ አንደምታም ከቀዝቃዛ ጦርነት በኋላ በዓለማችን የሚፈጠረው የእድገት ግጭት በሀገራት ወይም በርእዮተ-ዓለሞች መካከል ሳይሆን በባህሎች መካከል ነው… በመሆኑም ባህልና በሀይማኖት ዋና የግጭት መንስኤ በመሆናቸው፤ የዓለማችን የእይታና የትንተና ማእከል መሆን ይኖርበታል የሚል ነው፡፡

ለመንደርደሪያ ያህል ይህን ካልኩኝ፤ የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታም ሲታይ በሁለት አውድ በመክፈል በእነዚህ ሁለት አስተሳሶች መገምገም ወቅታዊና ተገቢ ነው፡፡ ይህም፡-

አንደኛው የአስተሳሰብ ጥግ፤ ኢትዮጵያ አንድ ናት፡፡ ታሪክዋ፣ ባህሏ፣ ሀይማኖቷም አንድ ነው፡፡ ያለን አማራጭም አንድና አንድ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ብቻ፡፡ ከዚህ የተነሳ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ልዩነት መጥበብ አለበት፡፡ የግለሰብ መብቶች ከቡድን መብቶች ይልቅ ቅድሚ መሰጠት አለባቸው፡፡ በሀገራችን ከማንነት ፖለቲካ ወጥተን በዜግነት ፖለቲካ ማትኮር ያስፈልገናል፡፡ የአስተዳደር ስርዓታችንም ወደ ተማከለና ወጥ አሰራርና አደረጃጀት መቀየር ይኖርበታል፡፡ የፌደራሊዝም ስርዓት በባህል ሳይሆን በመልከዓ-ምድራዊ አልያም መጥፋት አለበት….የሚሉ ሀሳቦችን ያካተተ ነው፡፡ ይህም በኔ እይታ ከፍራንሲስ ፋኩያማ ተውሼ “Ethiopianism in an End and the Last Man” (ኢትዮጵያነት ወይም ዓለም አለቀ) የሚል ርእስ ሰጥቸዋለሁ፡፡

ሁለተኛው የአስተሳሰብ ጥግ፤ በብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ማንነት ማእከል ያደረገ ነው፡፡ ሁሉም ነገር ለብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሰጠ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ወንዝና ሸንተረር አይደለችም፤ ኢትዮጵያ ማለት ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ማለት ነው፡፡ የህዝቦች የባህል ልዩነት የሀገሪቱ የአንድነት መሰረትና ውበት ነው፡፡ ከሁሉም በላይ በብሄሮች መካከል የሚፈጠረው ቅራኔ የሀገሪቱ ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ስለሆነ መከባበርና መቻቻል አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሙዝየም በመሆኗም የሀገራችን ፖለቲካ ማንነትን ማእከል ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡፡ ህዝቦች ራሳቸው በራሳቸው ማስተዳደር አለባቸው፡፡ ለዚህም ሲባል ብሄርን መሰረት ያደረገ ፌደራሊዝም አማራጭ የሌለው ስርዓት ነው፡፡ ተጨቁነናል፣ መብታችን አልተከበረም ካሉም የመገንጠል መብት ሊፈቀድላቸው ይገባል.. ወዘተ የሚሉ መሰረታዊ አስተሳሰቦች የሚራመዱበት ጎራ ነው፡፡ ይህም የሳሙኤል ሀንቲንግተን ንድፈ-ሀሳብ መሰረት በማድረግ “Cultural Tolerance in Ethiopia Unless Clash of Civilization” (መከባበር አልያም መለያየት) የሚል ርእስ ሰጥቸዋለሁ፡፡

በድምሩ ሲታይ በሀገራችን እየተንፀባረቁ ያሉ የአስተሳሰብ አክራሪነት ማስከን አስፈላጊ ነው፡፡ ጫፍና ጫፍ ተሁኖ ገመድ መጎተት መፍትሔ ሊሆን አይችልም፡፡ በሀሳብ፣ በተግባርና በቦታ ወደ መኸል ሰብሰብ ሰብሰብ ማለት አስፈላጊ ነው፡፡ እውነታ መፈለግና ወደ እውነታ መጠጋት አስፈላጊ ነው፡፡ ልዩነት በሀሳብ በማፋጨትና ወደ እውነታ መጠጋት ታላቅነትና ጀግንነት ነው፡፡ አሸናፊና ተሸናፊ የለውም፡፡ ተጠቃሚም ህዝብ ብሎም ሀገር ነው፡፡ የሀገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታም ቀደም ሲል ከቀረቡ ሁለት መሰረታዊ እሳቤችን ሲታይ በጣም የሚቀርበውና የሚያዋጣ የፕሮፌሰር ሳሙኤል ሀንቲንገቶን እይታ ነው፡፡ ተወደደም ተጠላም ሀገራችን የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሀገር ናት፡፡ በአራቱ አቅጣጫ የሚገኙ ህዝቦቻችን የጋራ ታሪክ እንዳላቸው ሁሉ፤ የየራሳቸው ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ፣ አኗኗር፣ልምድ፣ የአስተዳደር ዘቤ….ወዘተ አላቸው፡፡ የራሴ ነው የሚሉት ለማቀብ፣ ለማሳደግ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ማስተላለፍን ይፈልጋሉ፡፡ ሌሎች ባህላቸው እንዲያውቁላቸውና እንዲያከብሩላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ያንተ ተው የኔ ይሻልሃል የሚላቸው አይሹም፡፡ የኔ የተሻለ ነው፣ ያንተ መሻሻል አለበት ወይም ይቅርብህ እንዲባሉ አይፈልጉም፡፡

እውነታው ይህ ከሆነ ፍራስሲስ ፋኩያማ እንዳለው በአንድ የባህልና የእድገት አቅጣጫ (Uni-trajectory) መፍሰስ በኢትዮጵያ አይቻልም፡፡ ይልቁንስ እንደ ሳሙኤል ሀንቲንግቶን እይታ፤ በሀገራችን የሚፈጠረው ግጭት በሌላ ሳይሆን በብሄሮች መካከል በሚኖረው የማንነት አለመግባባት ነው፡፡ በብሄረሰቦች የባህል እሽቅድድም ከተፈጠረ ወደማያቧራ ቅራኔ መግባታችን አይቀርም፡፡ ስለሆነም ያለን አማራጭ ኢትዮጵያ ወይም ሞት ሳይሆን በፌደራሊዝም ስርዓት እስርስ በርሳችን መከባበር ነው፡፡ የሁሉም ባህር አክብረን፤ በልዩነታችን ተመምነን ወደ ፊት በመጓዝ መፃኢ ዕድላችን ብሩህ ማድረግ ነው፡፡ ከዚህ በዘለለ ግን የመጨረሻውና መጥፎ ዕድል መጠፋፋት ሳይሆን መለያየት ነው፡፡ ምክንያቱም ከመሞት መሰንበት ይሻላል፡፡    

Back to Front Page