Back to Front Page


Share This Article!
Share
የቄሮና የፋኖ ፖለቲካ :- በዓለም ላይ የሌለ ዕድሜ መሰረት ያደረገ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በኢትዮዽያ

የቄሮና የፋኖ ፖለቲካ :- በዓለም ላይ የሌለ ዕድሜ መሰረት ያደረገ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በኢትዮዽያ

(በፕሮግራም ወይም ምክንያታዊነት ባለው ዓላማ እንጂ ዕድሜ መሰረት ያደረገ ፖለቲካዊ ክፍፍል በዓለማችን ታይቶም ተሰምቶም ኣያውቅም)

Videos From Around The World

 

Tignen Tidmek 2-11-19

በዓለማችን የሚታየው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለዋወጠ ከወቅቱ ጋር እየተሻሻለ እየመጣ ከመሆኑም በላይ የለውጡ ፍጥነትም እየጨመረ በሚሄድበት ወቅት ነው የምንገኘው : : በ1960 ዎቹ በዓለማችን ላይ የነበረው ፖለቲካ ባብዛኛው በካፒታሊዝምና በሶሻሊዝም (ኮሚኒዝም) ጎራ ተከፋፍሎ የተጋጋለ እንቅስቃሴ ሲካሄድ ነበር : : በኣሁኑ ጊዜ ደግሞ ሶሻሊዝም (ኮሚኒዝም) እየተዳከመ የሚሄድበት ሁናቴና ባብዛኛው የካፒታሊዝምና ከፊል ካፒታሊዝም እንቅስቃሴዎች ጎልተው የሚታዩበት ጊዜ ላይ እንገኛለን : : በሌላ በኩልም የኣንድ ኣገር ኣወቃቀር ምን መምሰል ኣለበት በሚለው ጉዳይ ላይም ብዙ የተለያዩ ኣቋም ያላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች በዓለማችን ላይ እንዳሉ የሚታወቅ ጉዳይ ነው : : ጥቂቶቹን ለመገለጽ ያክል እንደ ፌደራሊዝም ፣ ኣሃዳዊ ፣ ወ ዘ ተ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያየ ኣስተያየት ከመያዛቸውም ባሻገር ግማሹ ኣንዱን ኣይነት ሲደግፍ ሌላው ግማሽ ደግሞ ሌላኛውን የፖለቲካው ኣቋም ሊደግፍ ይችላል : : እንዲሁም የተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል ያም ይህም የማይደግፍና ለፖለቲካ ብዙም ትኩረት የማይሰጥ ይሆናል : :

የትኛውም የፖለቲካ ሪኦተ ዓለም የሚከተል የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ድርጅት እንደ ፓርቲ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ እንዲቸርበት ብዙ ጥረት ያደርጋል : : ይህ የፖለቲካ ድርጅት እንደ ድርጅት የራሱ የሆነ ተልእኮና ራዕይ ሰንቆ በድርጅትነት እራሱን ኣዋቅሮ መንቀሳቀስ መሰረታዊ ተግባራት የኣንድ ፖለቲካዊ ፓርቲ ነው : : ታድያ እንደ ፓርቲ ፖለቲካዊ ስራዎቹን በስኬት ለመፈጸም ቢያንስ ቢያንስ ፓርቲው በሚንቀሳቀስበት ክልል ወይም ኣገር ሊመራው ለሚፈልገው ህዝብ በተለያዩ መንገዶች በመክፈል የትኛውን የህብረተሰብ ክፍል ማተኮር እነዳለበት ማወቅና ስትራቴጂ መንደፍ የግድ ይላል : :

የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚከተሉት ዴሞግራፊያዊና በባህሪያዊ ኣግባብ ህዘቡን በመከፋፈል ለያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍል በእንዴት መልኩ መድረስና ማሳመን እንዳለበት ስልት ኣውጥቶ ይንቀሳቀሳል : : በዚሁ ሂደት በኣገራችን ያሉትን የተወሰኑ የፖለቲካ ድርጅቶች እንኳን ብንወስድ በሚንቀሳቀሱበት ክልል (ኣገር) እነደሚከተለው በመከፋፈል የፖለቲካ ዓላማቸውን መተግበር ይችላሉ : :

 

የፖለቲካ ፓርቲ

ዕድሜ ክልል

መጠሪያው

በሌላ ቋንቋ

ህ ወ ሓ ት

ከ 18 ዓመት በታች

ህጻናትና ታዳጊ ወጣቶች

 

 

ከ 18 30 ዓመት

ወጣቶች

ቄሮ (በኦሮምኛ) ፣ መናእሰይ (በትግርኛ)

 

ከ 31 60 ዓመት

ኣዋቂዎች

 

 

ከ 60 ዓመት በላይ

ሽማግሌዎች

 

 

 

 

 

ዓ ረ ና

ከ 18 ዓመት በታች

ህጻናትና ታዳጊ ወጣቶች

 

 

ከ 18 30 ዓመት

ወጣቶች

ቄሮ (በኦሮምኛ) ፣ መናእሰይ (በትግርኛ)

 

ከ 31 60 ዓመት

ኣዋቂዎች

 

 

ከ 60 ዓመት በላይ

ሽማግሌዎች

 

 

 

 

 

ኣ ዴ ፓ

ከ 18 ዓመት በታች

ህጻናትና ታዳጊ ወጣቶች

 

 

ከ 18 30 ዓመት

ወጣቶች

ቄሮ (በኦሮምኛ) ፣ መናእሰይ (በትግርኛ)

 

ከ 31 60 ዓመት

ኣዋቂዎች

 

 

ከ 60 ዓመት በላይ

ሽማግሌዎች

 

 

 

 

 

ኦ ዴ ፓ

ከ 18 ዓመት በታች

ህጻናትና ታዳጊ ወጣቶች

 

 

ከ 18 30 ዓመት

ወጣቶች

ቄሮ (በኦሮምኛ) ፣ መናእሰይ (በትግርኛ)

 

ከ 31 60 ዓመት

ኣዋቂዎች

 

 

ከ 60 ዓመት በላይ

ሽማግሌዎች

 

 

 

 

 

ኦ ነ ግ

ከ 18 ዓመት በታች

ህጻናትና ታዳጊ ወጣቶች

 

 

ከ 18 30 ዓመት

ወጣቶች

ቄሮ (በኦሮምኛ) ፣ መናእሰይ (በትግርኛ)

 

ከ 31 60 ዓመት

ኣዋቂዎች

 

 

ከ 60 ዓመት በላይ

ሽማግሌዎች

 

 

 

 

 

ኦ ፌ ኮ

ከ 18 ዓመት በታች

ህጻናትና ታዳጊ ወጣቶች

 

 

ከ 18 30 ዓመት

ወጣቶች

ቄሮ (በኦሮምኛ) ፣ መናእሰይ (በትግርኛ)

 

ከ 31 60 ዓመት

ኣዋቂዎች

 

 

ከ 60 ዓመት በላይ

ሽማግሌዎች

 

 

 

 

 

ደ ህ ዴ ን

ከ 18 ዓመት በታች

ህጻናትና ታዳጊ ወጣቶች

 

 

ከ 18 30 ዓመት

ወጣቶች

ቄሮ (በኦሮምኛ) ፣ መናእሰይ (በትግርኛ)

 

ከ 31 60 ዓመት

ኣዋቂዎች

 

 

ከ 60 ዓመት በላይ

ሽማግሌዎች

 

ወ ዘ ተ

 

 

 

ፋኖ የሚለው ቃል የውጭ ኣገር የሰው ስም ስለሆነ ወጣት የሚለውን ቃል በፍጹም ሊተካ ስለማይችል እዚህ ላይ መጠቀሙ ትክክል መስሎ ኣልታየኝም

 

ከላይ ባለው የህብረተሰብ በዕድሜ ክፍፍል ካየን በትግራይ ክልል በሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ማለትም ህወሓት ና ዓረና ኣንዱ የህብረተሰብ ክፍል ወጣቶች ሲሆኑ በሁለቱም የፖለቲካ ድርጅቶች ዘንድ ኣሉ : : በሌላ ኣነጋገር በትግራይ የሚገኙ ወጣቶች ሓየት ብለን ከጠራናቸው ሓየት በ ህወሓት ኣለ ሓየት በዓረናም ኣለ

በገዳ ስርዓት ጊዜ በተለይ የኦሮሞን ማህበረሰብ ኣባ ገዳዎች የሚመሩት ማህበረሰብ ስለነበር የዚሁ ማህበረሰብ ኣንዱ ክፍል ደግሞ ቄሮ እነደሆነ በስፋት ሲነገር ይታያል : : በዚሁ የኣመራር ስርዓትም የሚከተል ህዝብም በህብረተሰቡ ውስጥ ከቄሮ በተጨማሪ በሌሎች የዕድሜ ክፍል የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉ ግልጽ ነው : : ዕድሜ መሰረት ተደርጎ ህብረተሰቡን የሚከፋፍልበት ዋና ምክንያት እያንዳንዱ የፖለቲካ ድርጅት የሚያራምደው የፖለቲካ ዓላማ በበለጠ ለማስረጽ የተለያዩ ስልቶች ለመጠቀም ያግዛል ከሚል እንጂ የዕድሜ ክልል በራሱ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ኣጀንዳ ሊሆን ኣይችልም : : ከላይ እንደተመለከተው በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱትን የፖለቲካ ድርጅቶች እንኳን ብንወስድ በያንዳንዱ የኦሮሚያ የፖለቲካ ድርጅት እንደ ኣንድ የህብረተሰብ ክፍል ወጣቱ በሁሉም ድርጅቶች ዘንድ ኣለ : : ይህም የወጣቱ ክፍል (ቄሮ) በኦዴፓ ያለው ቄሮ የኦዴፓን የፖለቲካ ዓላማ የሚደግፍ ፣ በኦነግ ስር ያለው ወጣት ኣባልና የህብረተሰብ ክፍል ደግሞ የኦነግ የፖለቲካ ሪኦተዓለም የሚደግፍ ቄሮ ይባላል : : ከዚህ የምንረዳው ነገር ቢኖር በእያንዳንዱ የፖለቲካ ድርጅት ያሉ ቄሮዎች ባላቸው የተለያየ የፖለቲካ ኣመለካከት ምክንያት እንዲሁ ቄሮ ስለሆኑ ብቻ ኣንድ ኣይነት የፖለቲካ ኣመለካከት ይኖራችዋል ብሎ መውሰድ ምክንያታዊ ሊሆን ኣይችልም : : በደፈናው የኦሮሞ ቄሮ የሚባል ልክ እንደ ከፋብሪካ የተፈበረከ ዕቃ ኣንድ ኣይነት የፖለቲካ ኣመለካከትና ኣቋም እንዳለው ኣስቦ መንቀሳቀስ በተጨማጭ መሬት ላይ ካለው እውነታ በጣም የራቀ ከመሆኑ ኣልፎ ፖለቲካዊ ኣንድነት የሌለው ፣ በዚሁ የዕድሜ ክልል የተለያየ ፖለቲካዊ የእምነት ቅይጥ ያለው ስብስብ ፣ ስለዚህ በዚህ የዕድሜ ክልል (ከ 18 30 ዓመት) ያለው የሰዎች ስብስብ የቄሮ የፖለቲካ ፓርቲ ሳይሆን የተለያየ ፖለቲካዊ ኣመለካከት ያለው የቄሮ መንጋ ነው የሚሆነው : : በእንደዚህ ዓይነት ስብስብ (መንጋ) እንደ ኣንድ የፖለቲካ ተቋም መውሰድ በዓለማችን ታይቶም ተሰምቶም ኣያውቅም : :

ፖለቲካዊ እምነት በዕድሜ ና በጾታ ኣይለይም : : በየትኛውም የዕድሜ ክልልና ጾታ የሚገኝ የህብረተሰብ ክፍል ለተመሳሳይ ፖለቲካዊ ዓላማ ሊሰለፍ እንደሚችል ሁሉ ለተለያየ ዓላማም ሊሰለፍ ይችላል : : ኣሁን በተደጋጋሚ እየሰማነው ያለው ጉዳይ ስናይ ግን ቄሮ በሚባል የዕድሜ ክልል የታጠረ ፖለቲካዊ ኣረዳድ ቄሮ ወንዶችን እንጂ ሴቶችን የማያካትት እንድምታ ያለው ፖለቲካዊ እምነት በዓለማችን ካለው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በእጅጉ የተለየ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ብቻ ያለ ኣስተሳሰብ ነው : :

በተመሳሳይ በኣማራ ክልልም ቄሮ በኦሮምያ በስፋት እንደሚነገረው ፋኖ የሚለው ቃል የኣማራን ወጣቶችን ለመግለጽ ኣንዳንድ ሰዎች ሲጠቀሙበት ይስተዋላሉ : : ክላይ ስለ ቄሮ የተገለጸው ለፋኖም በተመሳሳይ ይህን ዓይነት ስብስብ ይገልጸዋል : : ወጣቱ ሃይል እንደ ኣንድ ቡድን (category) ሊወሰድ የሚችለው ፖለቲካዊ ኣንድነት በማይፈልጉ ጉዳዮችና ሁኔታዎች ላይ፣ በልማት ፣ በውትድርና ፣ ኣደጋን በመከላከል ወዘተ ሊሳተፍ ስለሚችል በእንደነዚህ ጉዳዮች ላይ ቄሮ ፣ ወጣቶች ፣ ፋኖ ወዘተ ቢባል ሊያስኬድ ይችላል : : በፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ግን በኣንድ ጨፍልቆ እንዲሁ ቄሮ ወይም ፋኖ በመሆኑ ኣንድ ዓይነት የፖለቲካ ኣመለካከት ኣለው በማለት መስበክ ትክክል ሊሆን ኣይችልም : :

እንስሳት እንኳ ህጻናት ፣ ወጣቶች ፣ ኣዋቂ በማለት ኣይለያዩም : : እንስሳት ከጠላቶቻቸው ለመከላክል ወይም ለማጥቃት ፣ ሁሉም በየፊናው ለህጻናት ጥበቃ በመስጠት የመከላከሉንና የማጥቃቱን ስራ ኣብረው ይከውናሉ : : ስለዚህ ክእውነታ ውጭ ቄሮ ፣ ፋኖ እያልን ጾታንና ሌላው የዕድሜ ክልል ያለውን ህዝብ ያገለለ በዓለም ላይ የሌለ ፖለቲካ እያወራን የኢትዮጵያ ህዝብን ከማደናገር ብንቆጠብ የሚል ምክረ ሃሳብ ለማቅረብ በማሰብ ነው : : ኣመሰግናለሁ : :

ቸር እንሰንብት !!

Tignen Tidmek

tidmektignen@gmail.com

Back to Front Page