|
ተንሸራቶ ይሁን ተደናቅፎ፣ ተገፍትሮ ይሁን በሰው ተጠልፎ፣ ወይም በውስጥ ደዌ ተለክፎ፣ በጭቃ ላይ ወድቆ፣ ተጨማልቆ፣ አይተውት ሲስቁ፣ ካፈረ በመውደቁ፣ ለምን እንደወደቀ፣ እራሱን ካልጠየቀ፣ ጥንቃቄ ካልወሰደ ፣ ሳይገባው ከሄደ፣ ስብራቱን ከደበቀ፣ እሱም በራሱ ከሳቀ፣ አለቀ ደቀቀ፡፡ ይልቅስ ካረፈበት ሆኖ ከመሬቱ፣ ማወቅ ይሻለዋል ምክንያቱ፡፡ ሰው አየኝ አላየኝ ብሎ ፣ ከሄደ ቶሎ ቶሎ ፣ መውደቅ መነሳት፣ ከመሰለው ውርደት፣ ሊሸፍን ከሞከረ፣ በድርጊቱ ካፈረ ፣ ሁኔታውን ካላመነ፣ ከካደ እንዳልገባው ከሆነ ፣ እንደገበቴ ውሃ አይኑ ከዋለለ፣ እይታውን ካላስተካከለ፣ ጨልሞበት ከተደናበረ፣ ለመነሳት ካልተውተረተረ፣ እውነታን ከቀበረ፣ የሆነ መስሎት ብልጣብልጥ የበለጠ ፣ ጉዳቱንና ህመሙን ካላዳመጠ፣ በደመነፍስ ተነስቶ ከሮጠ ፣ ወይ ድጋሚ ይወድቃል ፣ ወይ ቁስሉ ያመረቅዛል፣ አልያም በዛው ያሸልባል፡፡
ገጣሚ አበበች መስፍን 8-1-19
Back to Front Page |