Back to Front Page


Share This Article!
Share
ያለጠንክራ ፍትህ እና ነፃነት ጠንካራ ህዝብ እና አገር አይኖርም።

ለጠንክራ ፍትህ እና ነፃነት ጠንካራ ህዝብ እና አገር አይኖርም።

በልኡል ገብረመድህን (አሜሪካ )

የካቲት   18/2011.

 

በመጀመሪያ በቀድሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በነበሩ ክብር አቶ አብዱራህማን አህመዲን “ለፈጣሪም ፣ ለመንግሰትም ፣ ለራሱም የማይመች ህዝብ “ በ 2/16/19 (በምዕራቡ ቀመር ) የተፃፈ መነሻ ላድርግ ።በግሌ በሁለት ምክንያት ለአቶ አብዱራህማን አህመዲን ያለኝ አክብሮት ልግለጽ ። አንዱ ምክንያት በኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት ለኢትዮጵያ ህዝብ ይነሰ ይብዛ ያበረከቱት አሰተዋጽኦ ሲሆን ሌላው ምክንያት ደግሞ ወንድም ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ።ለአቶ አብዱራህማን ተወካዮች ምክር ቤት ሥራ ላይ በነበሩበት ወቅት ላይ ውሰን ወቀሳዎች ቢኖሩኝም ማክበር ማስቀደም እንዳለብኝ አውቃለሁ ። ውድ ውንድሜ አብዱራህማን የላቀ ምስጋናዬ ባለህበት ይድረስህ ።

Videos From Around The World

የህዝብ ስህተት ምንድነው ?  Whatdoes the precise definition of public’s fault ?ጉዳዩ የፍልስፍና ጥያቄ ሊሆን ይችላል ። ለፈጣሪው የማይመች ህዝብ የሚለው አባባል ይጋሩት እንደሆነ እንጂ የወንድም አብዱራህማን ሓሳብ እንዳልሆነ አውቃለሁ ። ለመንግሥት የማይመች ህዝብ እንደሚኖር አያጠያይቅም ። ለራሱ የማይመች ህዝብ የሚለው አባባል እክል አለበት ። እንደተረዳሁት ከሆነ ጥቅምና ጉዳት ለይቶ የማያውቅ የሚል አገላለጽ ይነፃፀረው ይሆናል ። በእርግጥ ሐይማኖት/እምነት / ለፖለቲካ መነሻነት ይጠቅም ይሆነናል ። ነገር ግን ስለ አምልኮ /ሀይማኖት / ላይ ጊዜ አላጠፋም ። ሆኖም ከወንድሜ አብዱራህማን ጋር የማልስማማበት ጉዳይየኢትዮጵያ ህዝብ ለፈጣሪው ሆነ ለመሪው የሚመች አይደለም በሚለዉ አገላለጽ ልዩነት አለኝ ። ለዚህ መነሻ ይሆን ዘንድ የተጠቀሙበት ምክንያቶች ላይም አልስማማም ። የራሰ-ተኮር /Self Centered / እንዲሁም የጋራ እሴቶች ላይ ስምምነት የለም የሚሉ ምክንያቶች መነሻ ያደረገ አገላለጽ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለፈጣሪውና ለመሪው እንዳይታዘዝ ምክንያቶች ከሆኑ ጥልቀት ባለው ትንተና መሰራት ይኖርበታል ። በጥናት ላይ የተደገፈ ቢሆን የተሻለ መነሻ ሀሳብ ይሆናል የሚል እምነት አለኝ ። የጀርመን ህዝብ በአይሁዳውያን ላይ አስከፊና ጭካኔ አዘል ግድያ ፈፅመዋል ሲባል ሁሉም የጀርመን ህዝብ እንዳልሆነ ግምት ውሰጥ ቢገባ ። ምክንያቱም አዶልፍ ሒትለር (ናዚ) ወንጀል እንዲፈፅሙ የተጠቀመባቸው ሰዎች አብዛኛዎቹ ሥራ አጥ ጎደና አደር ወንጀሎች ነበር ።በእርግጥ ሥራ አጦች የህዝብ አካል ቢሆኑም ወንጀል ለመፈጸም በሂትለር አመራር የተመለመሉ ነበር ። ክፍያም ይከፈላቸው ነበር ።

       የኢትዮጵያ ህዝብ ራሰ-ተኮር በመሆኑ ለአስተዳደር ያስቸግራል የሚል አሰተያየት በከፊል እውነታነት እንዲኖረው ከተፈለገ ለዚህ መነሻ ምክንያት ሊበጅለት ይገባል ። በእኔ አሰተሳሰብ የራሰ ተኮር መነሻ ምክንያት የኢትዮጵያ መንግስት አወቃቀርና ተዛማጅ ችግሮች ይመስለኛል ። ምክያቱም በኢትዮጵያ በፍትሃዊነት የተመረጠ የህዝብ መንግስት ለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም ። ከንጉሡ እስከ ዘመነ ኢህአዴግ ድረስ ያለው የመንግስትነት ሁኔታ /Pattern / ብንቃኝ ተቀራራቢነት ያላቸው የመንግስት አሰተዳደር ችግሮች ለመረዳት አያዳግትም ። የኢትዮጵያ ህዝብ የኢኮኖሚ (የኑሮ )ሁኔታ ተመሳሳይነት ቢኖረውም በየጊዜው በሚቀያየር የመንግስት አሰተዳደር ጥገኛ ሆኖ የተወሰነ ሐብት የሚያካበቱ ጥቂት ሰዎች እንዳሉ ይገመታል ። ጥቂቶች የሚበለፅጉበት የመንግስት አሰተዳደር ሔዶ ሔዶ ህዝባዊ ጋሬጣዎች ያጋጥሙታል ። የመንግስትነት ሰልጣን ያገኘ መንግስት ህግና ሰርአት ላይ የተመሠረተ የአስተዳደር ዘይቤ ከመከተል ይልቅ ወገንተኝነት የበዛበት አሰተዳደር ይከተላል ። በመሆኑም ህዝብ በአስተዳደሩ ላይ እምነት ያጣል ። ቀጥሎም በመንግሥት አሰተዳደር ላይ ያምፃል። It is a natural phenomenon, perhaps more obvious that People start to disobey on government if the government starts to disobey the rule of law. በአንድ አገር የህዝብ ማህበረ-ኢኮኖሚ ጥያቄዎች የማያሰተናግድ የአስተዳደር ሰርአት በማይኖርበት ጊዜ ህዝቡ ለመሪዎቹ የሚመች ይሆናል ብሎ ማሰብ ያስቸግራል ። ህዝብና መንግስት መጣጣም ይኖርባቸዋል ።አድላዊ የመንግስት አሰተዳደር ህዝብ የራሱን የኑሮ ዘይቤ እንዲያበጅ ምክንያት ይሆናል ። አማራጭ ያጣ ህዝብ አይደለም የራሰ ተኮር አመለካከት ማበጀት ይቅርና ከዛ በላይ የመጥበብ አሰተሳሰብ ቢከተል ብዙም የሚያስደንቅ አይመስለኝም ።

በኢትዮጵያ የፍትህ እጦት ከሚገባው በላይ የጠለቀ ችግር አለበት ። የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈራው ፍትህ ሳይሆን ፍትህ አስፈፃሚ ሹማምንቶች ነው ። በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ተወዳጅ የሚባል ዳኛ ወይም አቃቤ ህግ ለመኖሩ እጠራጠራለሁ ። ምክንያቱም ህግና ፍትህ የሚያስፈፅሙ ሹማምንቶች የገዥው መንግስት መገልገያዎች ናቸው ። ህግና ህገ መንግሥቱ መሰረት አድርጎ ህዝብ የሚያገለግል ዳኞ ወይም አቃቤ ህግ አለ ብሎ ህዝብ አያምንም ። ያለ ምክንያትም አይደለም ። ይህ አመለካከት ችግር አይደለም ። እውነታነት ያለው ጉዳይ ነው ። It’s fact that there is public perception on to Judiciary neutrality in Ethiopia since Judicial judges and attorneys are potential government agents rather than to serve  the interest of the public in accordance with the rule of law and the constitution of the Nation . የህግ ልእልና በማይከበርበት አገር የተሟላ የህዝብ አገልግሎት ከመንግሥት ይገኛል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው ። የፍርድ እጦት በሚኖሩበት ጊዜ ህዝብ አማራጭ መንገድ ያበጃል ። ፍትህ በነፃነትና በህግ አግባብ ሳይሆን ፍትህን እንደሸቀጥ በገንዘብ መግዛት ይጀምራል ። በኢትዮጵያ የፍትህ ስርአቱ የአገሪቱ ህገ መንግስት ላይ ያተኮረ ወይም ለህገ መንግሥቱ ተገዢ ሆኖ  ካልተዋቀረ የመንግስት ብልሹ አሰተዳደር የሚቀርፍ አይሆንም ። ህግ የሁሉም ውሳኔዎች የባለቤትነት እንዲኖረው የፍርድ ቤት ዳኞች ከፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዱ ሆኖ መሾማቸው ለፍትህ ተቋም ወሳኝነት አለው ። የፍርድ መሸርሸር ካለ ህዝብ በፍርሃት እንጂ በነፃነት አይኖርም ። አስፈሪ እና ፈሪ ሆኖ መኖር ደግሞ ህዝብና መንግስት በዳይና ተበዳይ ሆኖ መኖር ማለት ነው ። ወንድሜ አብዱራህማን በኢትዮጵያ ምሑራን ላይ የሰነዘሩት ሓሳብ የምጋራው ይሆናል ። ምሑር ስንል ግን የትኛው ምሑር እንደሆነ ለጊዜው ባይገባኝም ኢትዮጵያ በርካታ የመንግስት አሰተዳደር አዋቂዎች እንዳሉ የሚያነጋግር አይደለም ። ሆኖም ግን ያወቀ የበሰለ የሚያስተናግድ መንግሥትና ስርአት ከሌላ የበቁ ኢትዮጵያዊ ምሑራን አገራዊ ፋይዳቸው አነሰተኛ ይሆናል ወይም ጭራሽኑ አሰተዋጽኦ አይኖራቸውም ። ዜጎች የሚያከብር ሰርአተ መንግስት በሌለበት አገር የምሁር አበርክቶ እምብዛም አይደለም ። የደርግ ሰርአት ፈርሶ የኢህአዴግ ሲተካ ስርአቱ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ላይ የወሰደው ፖለቲካዊ ውሳኔ መቸም የሚዘነጋ አይሆንም ። ከአርባ በላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ላይ የተፈፀመው ከሥራ የማስወገድ ተግባር አሳፋሪና አሳዛኝ ነበር ። በዚህ ምክንያት የኢህአዴግ ሰርአት ዘረኛ እንደሆነ በኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ተሰነገ። የሆነ ሆኖ ምሁራን በሁሉም ዘርፎች አገራዊ አበርክቶ እንዲያደርጉ የእኔም ጥሪ ነው ።ለአገር ጠቀሜታ ያላቸው ወቅታዊ ጥልቅ ምርምሮች ከምሁራን እንደሚጠበቅ ይገመታል ። በመሆኑም በኢኮኖሚ ሆነ በፖለቲካው የተሻለ አገር ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ የምሁራን ተሳተፎ ያሰፈልጋል ። አገር የተወሰኑ ፖለቲከኞች ሳትሆን የሁሉም ህዝቦች የጋራ ቤት ናት ። በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚታዩ ህውከቶች ጠቃሚነት የላቸውም ። ጎራ ለይቶ በዘር መነቋቆር ምን የሚሉት ስልጣኔ ነው ?።የከፍተኛ ተቋም ተማሪዎች ምክንያታዊ መንገድ ማበልጸግ ይኖርባቸዋል ። በፖለቲካ ቆማሪዎች እንደ መንጋ እንሰሳት መኮልኮል የለባቸውም ። ለሚያደርጉት ሁሉ ምክንያታዊ መነሻዎች ላይ የላቀ ትንተና ማድረግ ይኖርባቸዋል ። Students in higher level educational institution shall preserve their rational thinking beyond reasonableness . Rationality comes first for betterment. Reasons are the kind of major inputsto think in rational way. It must understand the real causes for such burning public issues for better solution than throw rain of rocks without understood the root causes of such hot issues . Higher level students have unfold moral obligation to their society to dig depth research help to avoid social disturbances in effective ways . Students shall avoid part of the problem rather a solution maker .

        የህዝብ ነፃነት የሚከበረው የፍትህ ነፃነት ሲከበር አንደሆነ እገምታለሁ ። በኢትዮጵያውያን ያልተለመደ ባህል ቢኖር መነጋገርና መደማመጥ ነው ። ችግሮች ሁሉ በመነጋገርና መደማመጥ ውሳኔ ባያገኙም ግጭት እንዲበርድ የሚኖረው ሚና ቀላል አይሆንም ። በጋራ መነጋገር ከቻልን ምናልባት ያሉብን የጋራ አገራዊ ችግሮች ከሚጠበቀው በታች ያነሱ ይሆናሉ ። የችግሮች ችግር ግን በጋራ መነጋገር ያለመቻል እንደሆነ ከግምት በላይ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም ። ወንድሜ አብዱራህማን ኢህአዴግ ውሰጠ ጠንካራ ነበር አሁን ግን ሳሰተዋል የሚል አሰተያየት አስፍሯል ። የጥንካሬና ሰሰነት ምክንያቶችም ለማሳየት ሞክሯል ። ኢህአዴግ በፊት ለሚቃወሙት ጠላት እንደነበረ አሁን ደግሞ ለሚቃወሙት ወዳጅ ሆነዋል የሚል ተከታይ ምክንያታዊ ለማንበብ ችያለሁ ። እዚህ ላይ ከወንድሜ አብዱራህማን የምለይበት ሓሳብ ሲጀምር ኢህአዴግ ጠንካራ ውሰጠ ዲሞክራሲ አልነበረውም ። አብዱራህማን አህመዲን የኢህአዴግ ጥንካሬ ምን ላይ እንደሆነ ዘርዘር አድርጎ አልገለፁም ።እኔ የማላውቃቸው የኢህአዴግ ውሰጠ ጥንካሬዎች ካሉ ወንድሜ እንዲያሰረዱኝ እጠይቃለሁ ። ኢህአዴግ ጠንካራ ሰርአት ነው ሰንል ምን ማለት ነው? ። በእኔ ምልከታ ኢህአዴግ አፋኝ ሰርአት አንደሆነ አውቃለሁ ። ይሀ ሲባል ኢህአዴግ ለኢትዮጵያ ያበረከተው በጎ ሥራ የለም እያልኩ አይደለም ። ኢህአዴግ ብዙ መልካም የልማት እንቅስቃሴዎች አከናውኗል ። ግን ደግሞ ማልማት ግዴታው ነበር ። ምክንያቱም ኢህአዴግ መንግስት ነበር ። ህዝቡን የሚመጥን ልማት ካልተሠራ በሰልጣን ላይ መቆየት አይችልም ። ሰለሆነም ማልማት የመንግስትም የህዝብም ግዴታ ነው ። እንደ እኔ እምነት የኢህአዴግ ሰርአት ኢትዮጵያን ችግር ውስጥ ዘፍቋታል የሚል የፀና እምነት አለኝ ።ለዚህ በርካታ ምክንያቶች ማጣቀስ ይቻላል ። ለአብነት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሙስና ተግባራዊ በስርአቱ አማካኝነት ተፈፅሟል ። የኢትዮጵያ የውጭ እዳ ሐያ አራት ቢሊዮን ዶላር ደርሰዋል ። መንግሰታዊ የልማት ድርጅቶች ዘይት አጥቶ መንገድ ላይ ቆመዋል። በርካታ ዜጎች ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ በሀይል እንዲፈናቀሉ ተደርጓል ። በዜጐች ላይ ሰብአዊ ጥሰቶች ተፈፅሟል ። ዜጎች ያለ ፍትህ ለእስር ተዳርጓል ። ዜጎች አገራቸው ትቶ እንዲሰደዱ በደህንነት ተቋም ይገደዱ ነበር ። ሰለሆነም የዜጎች መብት የሚደፈጥጥ መንግስት በምን የፖለቲካ ሒሳብ ጠንካራ ሰርአት ወይም መንግስት ሊሆን ይችላል ?።

በኢትዮጵያ የበርካታ ጎሳዎች ውህደት ውቅር አገር በመሆኗ የዘር ግጭት /Ethnic conflict /መነሳት አይደለም መሰማት ያልነበረበት ጉዳይ ነው ። በርካታ የዳበሩና የተፈተኑ የውስጥ ግጭት ባህላዊ አፈታት እሴቶች ያላት አገር የዘር ጥቃት በፍፁም መከሰት አልነበረበትም ። አሁን አሁን የዘር ጥላቻ /Ethnic hate/ እየተስፋፋ በመምጣት ላይ ነው ። ሰለሆነም ይህ መርና መርህ የለቀቀ ችግር በፆምና ፀሎት የሚፈታ አይመስለኝም ። ፍትህ የበላይነት መረጋገጥ አለበት ። እየታዩ ያሉ አስደንጋጭ ዘር መሠረት ያደረጉ ቅሰቀሳዎች ለመታደግ ሸምግልና ሳይሆን ተቋማዊ ፍርድ ነው ። ዜጎች በአገራቸው ተከብሮ እንዲኖሩ የህግ ከለላ ያስፈልጋቸዋል ። ዜጎች በነፃነት ከቦታ ቦታ ተዟዙሮ ለመኖርና ለመሥራት ተቋማዊ ፍትህ ያስፈልጋቸዋል ። Institutional justice is essential to all citizens of the land for free movement , to live in peace , and to possess property ownership where  ever and whenever they seek . people have nothing to trust but justice and freedom. Ethiopia shall need an absolute and definite free and fair judicial system govern by judiciary professionals not by political party affiliaters.  Having political afflicted people in the judiciary system is a neck bottle to the justice system and judiciary system failure comes after  sequentially . የፍትህ መረጋገጥ የሁሉም መፍትሔ ጫፍ ነው ። የአንድ ሰርአት ወይም መንግስት ወይም አገር ጥንካሬ መሰረት ጠንካራ ፍትህ ላይ የቆመ በመሆኑ ነው ። በአንድ አገር ጠንካራና ገለልተኛ የፍትሕ ተቋም ከተገነባ ተመጣጣኝና ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ይመጣል ፣ የተረጋጋ ሰላምና ማህበራዊ ትስስር ይጎለብታል ፣ ዜጎች በአገራቸው ጉዳይ ላይ በነፃነት ተሳትፎ ያደርጋሉ ።

ወንድሜ አቶ አብዱራህማን አህመዲን በ 2/23/19 (በምዕራቡ ቀመር )በአይጋ ፎረም የፊት ገፅ ላይ “ በኢትዮጵያ የተከሰተው ለውጥ ባለቤት ማን ነው ?” የሚል ጥያቄ አዘል አጭር ትንተና ፅፈዋል። ወንድም አብዱራህማን ባሰፈሩት ሓሳብ በከፊል እሰማማለሁ። ለውጥ ሲባል የስርአት ለውጥ እንደሆነ እገምታለሁ ። አቶ አብዱራህማን እንደገለፁት በኢትዮጵያ የመጣ ለውጥ እየበሰለ የመጣ የህዝብ ብሶት እንደሆነ እኔም የምስማማበት ጉዳይ ነው ። ኢህአዴግ  ከነ ጉድለቱ በርካታ መልካም ለውጦች ቢኖረውም መሳሳት የማይገባው አገራዊ ስህተቶች ፈፅመዋል። ገና ደርግ ከስልጣን መውረድ ማግስት አንሰቶ የተበላሸ የፖለቲካ አመለካከትና አሰተሳሰብ ቀውስ ውስጥ መግባት አልነበረበትም ። ኢህአዴግ በቀድሞ ሰርአት (ደርግ )ላይ ቂም ቋጥሮ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተዳደር ሰልጣን ሲይዝ የቂም በቀል ሴራውን ትቶ መሆን ነበረበት ። ኢህአዴግ ተራ ወደ ሆነ የጥላቻና ማጥላላት ተግባር ገባ ። በቀድሞ ሰርአት ተሳታፊ የነበረ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የደርግ ውዳቂ (ርዝራዠ) እያለ ህዝብ ማሸማቀቅ አልነበረበትም ። ወንጀል የፈፀመ በህግ አግባብ መጠየቅ ሲቻል ሰያሜ እያበጃጁ ማህበረሰብ ማሸማቀቅና ማጥላላት አገርና ህዝብ ከሚመራ የፖለቲካ ድርጅት የማይጠበቅ አስነዋሪ ተግባር ሆኖ አልፈዋል ።በአንድ አገር አንድ የመንግስት ሀላፊነት የአገሩ ዜጎች መብትና ደህንነት ማስጠበቅ ሆኖ ሳለ በፖለቲካ አሰተሳሰብ ልዩነቶች አሸባሪ ብሎ ሰያሜ ማበጀት አሰፈላጊ አልነበረም ። አሸባሪ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሳይሆን ራሱ መንግስት ነበር ሺብር የሚዘራ ። የኢህአዴግ መንግስት የመንግስትነት ሥራ ላይ አልነበረም ቢባል ፍትሀዊ አባባል ይመስለኛል ። ኢህአዴግ ለላቀ አገራዊ ለውጥ ከመስራት ለውድቀት የሚያግዙ ተግባሮች ላይ ሲሰራ ቆይተዋል።

         አሁን ኢትዮጵያ የፖለቲካና ሰርአት ለውጥ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች ። የኢህአዴግ ሰርአትም ፈርሰዋል። የፖለቲካና የስርአት ለውጥ ዋና ተዋናይ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድናቸው ። በዶክተር አብይ በተግባር የታዩ የፖለቲካ ለውጦች አበረታች መሆናቸው ብዙዎቹ የሚስማሙበት ጉዳይ ነው ። በእኔ እይታ የለወጡ መንፈስ ሐጎሰ ተነቅሎ ኢብሳ መተካት አይመስለኝም ። አሁን ያለው ለውጥ ባለቤት ማን ነው የሚለው አባባል ብዙም ትርጉም ያለው አይመስለኝም ። ለውጡ የማንም ይሁን ተፈላጊው የለውጡ ግብ ነው ። ግቡ ደግሞ ነፃነትና ዲሞክራሲ በዘላቂነት ማስፈን ላይ ያተኮረ ለውጥ ነው ።ኢትዮጵያ በአምባገነን መሪዎች መመራት የለባትም ። የኢትዮጵያ ህዝብ በጭቆና መኖር የማይፈቅድ ሆኖ ተነስተዋል ። የኢትዮጵያ ህዝብ ሊከፋፈል የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ። የለውጥ ቅልበሳ የሚያጋጥም አይመስለኝም ። በኢትዮጵያ ታሪክ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የተለየ የፖለቲካ ሓሳብ ያላቸው ፖለቲከኞች አንድ ላይ ተገናኝቶ መነጋገርና መወያየት የቻሉበት ጊዜ ላይ ደርሰዋል ። ይህ ታላቅ ስኬት ነው ። በኢትዮጵያ የስርአት ለውጥ ያሰፈልጋል ። ዜጎች በአገራቸው እንደ ባዳ የሚታዩበት ስርአት አክትሞ የዜጎች መብትና በጋራ ተጠቃሚነት የሚያጎላ የፖለቲካ ሰርአት መገንባት ጊዜ የሚሰጥ ጉዳይ አይደለም ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እየተወሰዱ ያሉ ሁሉም አቀፍ ለውጦች (Comprehensive Reforms ) ይበል የሚያስብሉ በመሆናቸው የህዝብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ። በኢትዮጵያ የዘር ፖለቲካዊ ነቀርሳ በመሆኑ በተግባር ተፈትኖ ወድቀዋል ። የብሔር ፖለቲካ በህገ መንግስት መታገድ አለበት የሚል የፀና እምነት አለኝ።የዶክተር አብይ የለውጥ ሒደት የአመለካከትና አሰተሳሰብ ችግሮች ቢያጋጥሙትም ህዝባዊነት የተላበሱ ለውጦች በመሆናቸው የኢትዮጵያ ህዝብ የተሻለ ነገን ማየት እንዲሚችል ለአፍታም ቢሆን ጥርጥር የለኝም ። አሁን የኢህአዴግ የብሔር ሰብሰብ ፖለቲካ ተንዶ አገራዊ ቅርፅ እንዲኖረው እንደሚደረግ ከተሰማ የከረመ ቢሆንም አሁን የተግባር ሽግግር ላይ ይገኛል ። ይህ የሚደገፍ ታላቅ ተግባር ተደርጎ መታየት ያለበት ይመስለኛል ። የኢህአዴግ ሰርአት አግላይ ሰርአት ስለነበር የራሱን አጋር ድርጅቶች አገራዊ አሰተዋጽኦ እንዳያደርጉ አግቶ

         በመጨረሻም ከፋ ለማ ወንድሜ አቶ አብዱራህማን አህመዲን በኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምክርቤቱ አባል ሆኖ ለኢትዮጵያ ህዝብ የዲሞክራሲ ተሰፋው እንዲያብብ ፣ ሰብአዊ መብት እንዲከበር ላደረጉት አሰተዋጽኦ ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ ። ጥሩ ሰራ ሰርቻለሁ ብሎ እንደሚያምኑም ተሰፋ አደርጋለሁ ። በቀጣይም ህዝባቸው እና አገራቸው በሚችሉት ሁሉ አሰተዋጽኦ እንደሚያደርጉ በመተማመን ይሆናል ። ቸር ያሰማን  !

 

Back to Front Page