አዲሱ
ቦለቲካ
ክልል ነው
የበጠበጠን
ለግጭት ቅራኔ...
እዚህ ያደረሰን
ይፍረስና ክልል
...
በቋንቋ በባህል
... እንዲሁም በታሪክ
የተወቃቀረው
በአራት ቦታ ከፍለን
.. እንደዚህ እንበለው
ፀሀይ በምትወጣበት..
ተካለው የሚኖሩ
ምስራቄውች ናቸው..
እንዳይጠራጠሩ
ፀሀይ በምትጠልቅበት
.. የተከማችቱ
ምእራቦች ናቸው
.. ይወቁት በወቅቱ
ወደላይ የሰፈሩት..
የጥንት ተወላጆች
ስይመናቸዋል
...ብለን ሰሜኖች
ወደታች ይሻለናል
.. ብልው ለመረጡት
ደቡቦች በማለት
... ወርቅ ስም ሰጥተናል
ከሁሉም ቀርቶብን
መሀል ይሻለናል
.. ብለው ለሰፈሩ
መሀል ነዋሪዋች
.. ሁሉንም ወዳጆች
ፈላጭ ቆራጭዎች
ብለን ስም ሰጥተን...
መዝገቡን ዘግተናል
ኢዮብ ከጮማእምኒ
7-26-19