Back to Front Page


Share This Article!
Share
የአቶ ደጉ አንዳርጋቸው መልቀቅ፤ ያማራ ክልል መግለጫና ጠመዝማዛው መንገድ

 

የአቶ ደጉ አንዳርጋቸው መልቀቅ፤ ያማራ ክልል መግለጫና ጠመዝማዛው መንገድ

 

ከበቀለ በርሃኑ 03/08/2019

 

ሰሞኑን ዶ/ር ዮሃንስ አበራ ህዝቡ ወደራሱ እየተመለሰ ነው የሚል እንድምታ ያለው ጽሁፍ አቅርበው ነበር። ብዙ ተስፈኛ ባልሆንም እንዳፈዎ ያድርግልን በሚል ስሜት ነበር የተቀበልኩት።

 

ዛሬ የ አማራ ክልል መንግስት/ ሸንጎ በክልሉና በትግራይ ህዝብ መካከል የነበረዉን፤ ያለዉንና ለዘለ-ዓለም የሚኖረዉን ህዝባዊ ግንኙነት ማንም ሊሽረው የማይችል ነገር መሆኑን ሲያበስር እጂግ ነበር በተስፋ የተሞላሁት።

 

ለዚህም አብዛኛዉ አመራር በዚህ አስቸጋሪ በሆነ ወቅት በዉስጡ ያሉትን ብቃት የሚያንሳቸወንና በጥላቻ የተሞሉትን ሃይሎች ግፊት በመግታት የሰላምና የወንድም/ እህት ህዝቦችን ፍላጎት በመገንዘብ ወደ ሰላም ጎራ መመልስ መቻሉ እጅግ የሚያስደስት ዜና ነው። ይህ ስሜት የተሰማኝ ገና ሁሉን ጉድ አመሻሽ ላይ ሰልሰማ ነበር።

 

Videos From Around The World

በዚሁ ልክ ድግሞ ለህዝብ ፍጆታ ዪመቻል በሚል ስሌት ዪሁን ስህተትን ላለመቀበል የሚደረግ የዉስጥ ትግል (posturing) የሚሉት የፈረንጂኛ ቃል ዪገልጸዋል መሰለኝ፤ የትግራይን መንግስት በጠብ አጫሪንት የሚከስ መግለጫ ብዙም ሳይዘገይ ሰማሁኝ።

 

ላባባሉ እውነትነት ቢኖረው ካማራው መንግስት ጋር ባብር ደስ ባለኝ። በተጨባጭ የምሰማዉና የማየው ግን ዘራፍ ባዩ ጎራ ከሚድያው ጀምሮ እስከ ነጭ ላባሹና ሸፍታው ጭምር ካማራ ክልል አካባቢ ነው። መንገድ የሚዘጉትና የህዝብ ለህዝብ ግኑኘቶችን ለመግታት የሚታትሩት ያሉት በናንተው ክልል ነው። ታዲያ ያ የተደናገረው መግለጫ ለምን ተለቀቀ?

 

አቶ ደጉ አንዳርጋቸው ከፋም በጀም ክልሉን ልብዙ ጊዜ መርተዋል። አሳቸውና የትግራዩ አባይ ወልዱ ለሁለቱ ድርጅቶች - እጅግ የተሳሰሩና የተቆራኙ ተብለው ለሚታሰቡ ድርጅቶች- መቃቃር የራሳቸዉን አሉታዊ ድርሻ ተጫዉተዋል። በዚሁ ልክ ደግሞ ያላቸው ልምድና ምናልባትም ህሊናቸው ስለምያስገደዳቸው የከረረዉን በማላላት በኩል በጎ ሚና ይጫወታሉ የሚል የተስፋ ጭላንጭል ነበርኝ።

 

ያ አልሆነም። በኔ ግምት አቶ ደጉ ተገለዋል። ዘራፍ ባዮች ወደፊት እየመጡ ነው። ተተኪው ዶ/ር ብዙም ባላውቃቸውም አንዴ የሰማሁት ንግግራቸው ግን ተስፋ-ሰጭ አልነበረም። ባንድ ንግግር ወይም አባባል መፍረድ አይቻልምና ከጊዜ ጋር ማየቱ የሚበጅ ይሆናል።

 

በሌላ በኩል ድግሞ ባገር ክህደት ታስሮ የነበረው ጀነራል የጸጥታ ሃላፊ ሆኖ መሾምና በከፍተኛ ሃላፊነት ማስቀመጥ የክልሉ ገዢ ፓርቲ ለሰላም ዝግጁነቱ እጂግ አጠራጣሪ ያደርገዋል። ይህ ጀነራል በዉስጡ የታመቀ የግል የበቀል ስሜት ስለምያሽከረክረው የሰላም አጋር መሆን ፈጽሞ የማይቻለው ሰው ነው። ገና ሲናገር ለሚያየው እሳት ጎርሶ -ፊቱ ደም ለብሶ ነው በተደጋጋሚ ያስተዋልኩት።

 

ሁኔታዎች ይህን እየመሰሉ ነው። አቶ ደጉ አንዱ የቲም ለማ ቁንጮ ቦታቸዉን ለቀዋል። (የቲሙ /ቡድኑ) እጣ ፈንታ እየተሰነበተ ዪታያል። ጠ/ሚኒስትሩ አንድ አፈንጋጭ አጀንዳ ይዘው እስኪመለሱ ድረስ ድምጻቸውን አጥፍተዋል።

 

ያማራው ፕርቲ መግለጫ ሌላም ሌላም ብሏል። የፈደራል መንግስቱን ሃይል ለመንጠቅ እየዳዳም ዪመስላል። ትግራይ ዉስጥ ያሉት ሌቦች ሰላም እያወኩ ነው ዪታገሱም ብሏል። ይህ የልብ እብጠት ማሳያ የሆነው ብዙ ፖለቲካዊ እንድምታ ባይኖረዉም፤ ዪህ ፓርቲ የዝቡ ጥያቄ፤ ፍላጎትና ምኞት ምን ያክል ከራዳሩ እንደራቁ ማሳያ ነው።

 

ያገራችን እጣ ፈንታ ምን ዪመስላል? እንድኔ ከሆነ ብዙም ስጋት የለኝም። ክዚህም ከዝያም ተጠራርተው የመጡት ሓይሎች ግራ ተጋብተዋል። ህዝቡ አንዲት ል ኡላዊት በዜግነት ላይ የተመሰረተች፤ የብሄረ ሰቦችን መብት ያስከበረች ፈደራላዊት ሃገር መመስረት ከኢትዮጵነት ጋር በምንም መልኩ እንደማይቃረን እየገባው ሲመጣ (ይህ አሁን የዝብ ግንዛቤ እየሳበ እየሄደ የመስለኛል) ጽንፈኞች ቦታ እያጡ የመጣሉ።

 

እስከዝያው ድረስ ግን ትግሉ አንዴ ቀዝቀዝ አንዴ ሞቅ እያለ መጓዙ አይቀርም። አዎንታዊ ሃይሎች አዎንታዊ እውነቶችን በማጎልበት፤ ላሉታዊ ሃይሎች ደግሞ ቀዳዳ ባለመክፈት ንቁ ሆነው መጠበቅ ዪኖርባቸዋል;

 

ሰላም ለህባችን

Back to Front Page