Back to Front Page

ሬስቶራንቱ ይቅርብኝ

ሬስቶራንቱ ይቅርብኝ

እንጀራን  በቅጡ ... ጠግቤ  የማላቀው
የጣልያን ፣ የፈረንሳይ… ሬስቶራንት ...
ከሆነማ  ህልሞ ... እርሶ  ቢገባዎት...
ፒዛና ፣ ቺዙንም ... ቁምነገር  የማልሰጠው
የሰፈሬን  ሻይ  ቤት ... ሂሳቡን  የማልችለው
በእምዬ  ሬስቶራንት ... መዐዛ  ምጠግበው
የጣሊያን፣ የፈረንሳይ … ሬስቶራንት...
ከሆነማ  ህልሞ ... ለካስም  እውነት ነው
እኔን  መርሳወቶ

በሰላም  ወጥቼ ... መግባቴን  የማላውቅ
መቐለን  ተሻግረዉ ... አስመራን  ማድነቅ
ሰላም  አለ  ብሎ ... ዲስኩርን  ማብዛት

የጣልያን፣  ፈረንሳይ …. ሬስቶራንት ...
ከሆነማ  ህልሞ ... እኔን  የማያቁኝ
እንጅራን  የምወድ ... ፒዛን  የማላደንቅ
ፈረንሳይ  ሬስቶራንት ... ፍጽም  የማይመቸኝ
ከ  ሽሮ  ያልወጣሁ ... ኢትዮጵያዊ  ነኝ

ይህንን  ሳያውቁ ... ሬስቶራንት  ማለሞ
መቐለን  እረስተው ... አስመራን  ማድነቆ
አሁን  ገና  ገባኝ ... መሪ  አለመሆኖ

እዮብ ከ ጮማ እምኒ

Back to Front Page

12-29-19