መሬቱም
ተቆጣ
ነዷል እንደ እሳት...
መሬቱ ነዷል
ፍም ጎርሶ ... ፍም
ይተፋል
ረመጥ ሆኗል ... ጠላትን
አስጠንቅቋል
ብሏል ...ትእግስቴ
ተሟጧል
ተናግሯል ብሎ...
አልምርም
እንደድሮው አልታገስም
... አልሸከምም
ይቅር አልልም
ብሎ... ደግሞ ተናግሯል
አልሟል ... አነጣጥሯል
ቂም ቋጥሯል ... መነጽሩን
ወልውሏል
አለ ልቤ ተሰብሯል
... በጥኑ አሞኛል
እንዲህ ብሏል..
አፍ አውጥቶ ተናግሯል
የተሰዋ በግፍ
የተገደለን... አልቀበልም
የሰማኣታት ጎጆ
... አልሆንም
አልከፍትም ቤቴን
... አላስገባም
ከብዶኛል አለ
... አልሸከምም
ሞልቷል አለ ... ቤቴ
ተጣቧል
አላለቅስም አላስተዛዝንም
እንባአልጠርግም
... አላጽናናም
አውቃለሁ አለ
... ማን እንዳዘዘ
ማን እንዳስፈጸመ
ማን እንደነበረ
... ማን እንደፈዘዘ
ማን እንደፈቀደ
ማን እንደ ሸፈነ
ከእንግዲህየፍትህን
ጭርሆ አልዘምርም
ህግመንግስት
ብዬ ... አላላዝንም
ስማቸውን በዝርዝር
... አውቃለሁ
መነጽሬን ቀይሬአለሁ
... ወዮ !!! ብያለሁ
ብሎ ተናገረ
...
ያመሬቱ ...የኛው
ፍም የጎረሰው
ኢዮብ
ከጮማ እምኒ
2-28-19