Back to Front Page

በመለስ አንደበት

በመለስ አንደበት


ስትዘክሩኝ ...

በለቅሶ፣ ሀዘን... ሳይሆን በምሬት 
ስትዘክሩኝ... ይህን አመት 
ለአንዴና ለመጨረሻ 
... እንድትስሙኝ ይሁን በእውነት

በአላማ የሄድኩበት 
ያላማራጭ ያቆምኩበት 
ጊዜዬ ደርሶ ... ጸጥ ያልኩበት
የዘላለም እንቅልፍ... የተኛሁበት
ያለተቃውሞ ... 
ቤትህ ጎጆህ ... ግባ በተባልኩበት 
ጸጥ ለጥ ... ብዬ ያረፍኩበት 
ሰምቼ ... እንዳልሰማሁ 
ተበድዬ ...እንዳልተበደልኩ 
ቤቴ ... ብዬ የኖርኩባት 
አሁን ግን ...
ያቺ ቤት ቆረቆረችኝ ... ፈረኋት ጠላኋት
ጎረበጠችኝ ፣ ቀዘቀዘችኝ 
አስፈራችኝ... እረፍት ነሳችኝ 
እና አደራ ... 
ውሰዱና ... ቀላቅሉኝ 

ቆፍረው አውጥተው ... ለውሻ ሊሰጡኝ 
ሲሳለቁ የነበሩ ... ሲረግሙኝ 
እነሱ ገብተው ... በምንስ ምክንያት ሊመቸኝ 

የተጋበዙቱ ... የተወደሱቱ 
የተከበሩቱ
የታቀፉ 
የተቆላለፉ 
የተሰባሰቡ ... ግን ... የሚጋፈፉ 
ምን ተቃውሞ አሰሙ ?

መጥተው ... ገብተው
አይተው ታዝበው 
ፊታቸው ሲደፋ 
የደከመ የለፋ
የአባይ ዋና ... አንጋፋ 
ታታሪው ኢንጂነር ... ሲቀጠፍ ሲጠፋ
ምን አሉ ... ምን አሉ እነሱ ? 

እነሱ .. ሲጠግቡ ፣ሲረሱ 
ሲወረዱ ... ሲያወድሙ ፣ ሲያፈረሱ 
ሲያስገድሉ ... ሲያቃጥሉ 
ዝም ጭጭ .. ሲሉ 
ማየቱና ... መታዘቡ ጎድቶኛልና በጽኑ ... 
አደራ... 
በቃ... ይብቃህ በሉኝ አሁኑኑ 

ከሰዐረ ፣ ገአዚና ኮርተር በኋላ... 
ብያለሁ ... በቃ ይብቃኝ 
ሰባት አመት ያለ ኪራይ ... የኖርኩባት
ሳትፈርስ ... በላዬ ላይ .. ተረከቧት 
ተንከባክቤ ... ያቆየኋት 
ቤቴን ... ጎጆዬን 
አሰናብቱኝ በሰላም ...,
ልወጣ ስለሆነ ... በፈቃዴ 
... ልቀላቀል ከጓዶቼ 

እና አደራ ... 
የምታስቡልኝ ፣ የምትዘክሩኝ 
ውሰዱና... ቀላቅሉኝ 
ላውጋ ፣ ላውራ ፣ ልሳቅ... ልደሰት 
ልቀላቀል ፣ ልጫወት 
ይሰማኝ ... ይሽተተኝ፣ ቤትነት 
ልላቀቅ ... ከብቸኝነት 
እስቲ ልታደስ... በአብሮነት ፣ በአንድነት 
ልጠይቅ ፣ ልጠየቅ 
ወቀሳ ሳይሆን ... ምሮታ 
መስመር ሳይሆን ... አላማ 
ቀረብ አርጉኝ ... ከአጋሮቼ 
ስለኑሮ ውድነት ...ሳይሆን ስለፖለቲካው
ስለ ጣልቃ ገብነት ... ሳይሆን ዘረኝነት 
ስለ ማፈናቀሉ ሳይሆን ... ስደተኝነት 
ብቻ...
እስቲ ውስዱኝ .. 
ከ ሰዐረ ጋር ... አገናኙኝ 
እስቲ ... እንሳቅ አብረን 
የዘላለም እረፍት .. ያንቀላፋን 
እስቲ ... ልጠይቀው ገዛኢን 
እሰቲ ...
ልቀፍው ፣ ልሳመው ... ኮርተርን 
እና ... 
ይሄን አመት... ስትዘክሩኝ
አደራ እንድትውሰዱ .. እንድትቀላቅሉኝ 
ብቻ ... ብቻዬን አትጣሉኝ 
ከጓዶቼ ጋር ... አስጠጉኝ 
ከብቸኝነት አላቁኝ 
አደራ ... 
አትጠይቁኝ ... ግን ውሰዱኝ 
አዳምጡኝ ... ቀላቅሉኝ 
ጓዶቼን ... ከልክ ካለፈ ናፈቁኝ ።

ኢዮብ ከጮማ እምኒ

Videos From Around The World


Back to Front Page